Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




ኢያሱ 22:32 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

32 የካ​ህ​ኑም የአ​ል​ዓ​ዛር ልጅ ፊን​ሐስ ከእ​ር​ሱም ጋር የማ​ኅ​በሩ አለ​ቆች ከሮ​ቤል ልጆ​ችና ከጋድ ልጆች፥ ከም​ና​ሴም ነገድ እኩ​ሌታ ዘንድ ከገ​ለ​ዓድ ሀገር ወደ ከነ​ዓን ሀገር ወደ እስ​ራ​ኤል ልጆች ተመ​ለሱ፤ ወሬም አመ​ጡ​ላ​ቸው።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

32 ከዚያም የካህኑ የአልዓዛር ልጅ ፊንሐስና መሪዎቹ፣ ከሮቤልና ከጋድ ወገኖች ጋራ በገለዓድ ምድር ከተነጋገሩ በኋላ፣ ወደ ከነዓን ተመልሰው፣ ሁኔታውን ለእስራኤላውያን ነገሩ።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

32 የካህኑም የአልዓዛር ልጅ ፊንሐስና አለቆቹ ከሮቤል ልጆችና ከጋድ ልጆች ዘንድ ከገለዓድ አገር ወደ ከነዓን አገር ወደ እስራኤል ልጆች ተመለሱ፥ ወሬም ይዘውላቸው መጡ።

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

32 ከዚህም በኋላ የካህኑ የአልዓዛር ልጅ ፊንሐስና መሪዎቹ በገለዓድ ከሚገኙት ከሮቤልና ከጋድ ሕዝቦች ዘንድ በከነዓን ምድር ወደሚገኙት ወደ እስራኤል ሕዝብ ተመልሰው በመምጣት፥ ያገኙትን ማስረጃ አቀረቡ፤

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

32 የካህኑም የአልዓዛር ልጅ ፊንሐስና አለቆቹ ከሮቤል ልጆችና ከጋድ ልጆች ዘንድ ከገለዓድ አገር ወደ ከነዓን አገር ወደ እስራኤል ልጆች ተመለሱ፥ ወሬም አመጡላቸው።

See the chapter Copy




ኢያሱ 22:32
4 Cross References  

የካ​ህ​ኑም የአ​ል​ዓ​ዛር ልጅ ፊን​ሐስ ለሮ​ቤል ልጆ​ችና ለጋድ ልጆች ለም​ና​ሴም ነገድ እኩ​ሌታ፥ “ይህን መተ​ላ​ለፍ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ላይ አላ​ደ​ረ​ጋ​ች​ሁ​ምና እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በመ​ካ​ከ​ላ​ችን እን​ዳለ ዛሬ እና​ው​ቃ​ለን፤ አሁን የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ልጆች ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እጅ አድ​ና​ች​ኋል” አላ​ቸው።


ነገ​ሩም የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ልጆች ደስ አሰኘ፤ ለእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች በነ​ገ​ሩ​አ​ቸው ጊዜ የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ልጆች አም​ላክ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን አመ​ሰ​ገኑ፤ ከዚ​ያም ወዲያ የሮ​ቤል ልጆ​ችና የጋድ ልጆች፥ የም​ና​ሴም ነገድ እኩ​ሌታ የተ​ቀ​መ​ጡ​ባ​ትን ምድር ያጠፉ ዘንድ ለመ​ው​ጋት አን​ወ​ጣም ተባ​ባሉ።


Follow us:

Advertisements


Advertisements