Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




ኢያሱ 22:23 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

23 አም​ላ​ካ​ች​ንን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን እን​ድ​ን​ክ​ደው፥ የሚ​ቃ​ጠ​ለ​ውን መሥ​ዋ​ዕ​ትና የእ​ህ​ልን ቍር​ባን እን​ድ​ና​ሳ​ር​ግ​በት፥ የደ​ኅ​ን​ነ​ት​ንም መሥ​ዋ​ዕት እን​ድ​ና​ቀ​ር​ብ​በት መሠ​ዊያ ሠር​ተን እንደ ሆነ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እርሱ ራሱ ይመ​ራ​መ​ረን፤

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

23 መሠዊያውን የሠራነው እግዚአብሔርን ከመከተል ወደ ኋላ ለማለት፣ የሚቃጠል መሥዋዕትና የእህል ቍርባን ልናሳርግበት ወይም የኅብረት መሥዋዕት ልናቀርብበት አስበን ከሆነ፣ ራሱ እግዚአብሔር ይበቀለን።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

23 ጌታን ከመከተል እንድንመለስ፥ የሚቃጠለውን መሥዋዕትና የእህል ቁርባን እንድናሳርግበት፥ የአንድነትንም መሥዋዕት እንድናቀርብበት ብለን መሠዊያ ሠርተን እንደሆነ ጌታ እርሱ ራሱ ይበቀለን፤

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

23 ለእግዚአብሔር የማንታዘዝ ከሆንንና የሠራነውን መሠዊያ የሚቃጠል መሥዋዕት፥ የእህል ቊርባን፥ ወይም የአንድነት መሥዋዕት ልናቀርብበት አስበን ከሆነ ራሱ እግዚአብሔር ይቅጣን፤

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

23 እግዚአብሔርን ከመከተል እንድንመለስ፥ የሚቃጠለውን መሥዋዕትና የእህል ቁርባን እንድናሳርግበት፥ የደኅንነትንም መሥዋዕት እንድናቀርብበት ብለን መሠዊያ ሠርተን እንደ ሆነ እግዚአብሔር እርሱ ራሱ ይበቀለን፥

See the chapter Copy




ኢያሱ 22:23
10 Cross References  

ዮና​ታ​ንም፥ “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከዳ​ዊት ጠላ​ቶች እጅ ይፈ​ል​ገው” ብሎ ከዳ​ዊት ቤት ጋር ቃል ኪዳን አደ​ረገ።


በስ​ሜም በሚ​ና​ገ​ረው ሁሉ ያን ነቢይ የማ​ይ​ሰ​ማ​ውን ሰው እኔ እበ​ቀ​ለ​ዋ​ለሁ።


ኀጢ​አ​ተ​ኛ​ውን፦ ኀጢ​አ​ተኛ ሆይ! በር​ግጥ ትሞ​ታ​ለህ ባልሁ ጊዜ፥ ኀጢ​አ​ተ​ኛ​ውን ከክፉ መን​ገዱ ታስ​ጠ​ነ​ቅቅ ዘንድ ባት​ና​ገር፥ ያ ኀጢ​አ​ተኛ በኀ​ጢ​አቱ ይሞ​ታል፤ ደሙን ግን ከእ​ጅህ እፈ​ል​ጋ​ለሁ።


ጕበ​ኛው ግን ጦር ሲመጣ ቢያይ፥ መለ​ከ​ቱ​ንም ባይ​ነፋ፥ ሕዝ​ቡ​ንም ባያ​ስ​ጠ​ነ​ቅቅ፥ ጦርም መጥቶ አንድ ሰው ከእ​ነ​ርሱ ቢወ​ስድ፥ እርሱ በኀ​ጢ​አቱ ተወ​ስ​ዶ​አል፤ ደሙን ግን ከጕ​በ​ኛው እጅ እፈ​ል​ጋ​ለሁ።


እኔ ኀጢ​አ​ተ​ኛ​ውን፥ “በእ​ር​ግጥ ትሞ​ታ​ለህ ባል​ሁት ጊዜ አን​ተም ባት​ነ​ግ​ረው፥ ነፍ​ሱም እን​ድ​ት​ድን ከክፉ መን​ገዱ ይመ​ለስ ዘንድ ለኀ​ጢ​አ​ተ​ኛው ባት​ነ​ግ​ረው፥ ያ ኀጢ​አ​ተኛ በኀ​ጢ​አቱ ይሞ​ታል፤ ደሙን ግን ከእ​ጅህ እፈ​ል​ጋ​ለሁ።


እን​ዲ​ሁም ንጉሡ ኢዮ​አስ አባቱ ኢዮ​አዳ ያደ​ረ​ገ​ለ​ትን ቸር​ነት አላ​ሰ​በም፤ ልጁ​ንም አዛ​ር​ያ​ስን አስ​ገ​ደ​ለው፤ እር​ሱም ሲሞት፥ “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይየው፤ ይፍ​ረ​ደ​ውም” አለ።


በዚ​ያን ጊዜ አም​ላ​ካ​ችሁ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ስሙ ይጠ​ራ​በት ዘንድ ወደ​ዚያ ወደ መረ​ጠው ስፍራ፥ እኔ የማ​ዝ​ዛ​ች​ሁን ሁሉ፥ የሚ​ቃ​ጠ​ለ​ውን መሥ​ዋ​ዕ​ታ​ች​ሁን፥ ቍር​ባ​ና​ች​ሁ​ንም፥ ዐሥ​ራ​ታ​ች​ሁ​ንም፥ ከእ​ጃ​ችሁ ሥራ ቀዳ​ም​ያ​ቱን የተ​መ​ረ​ጠ​ው​ንም መባ​ች​ሁን ሁሉ፥ ለአ​ም​ላ​ካ​ች​ሁም የተ​ሳ​ላ​ች​ሁ​ትን ሁሉ ውሰዱ።


ነገር ግን ደመ ነፍስ ያለ​በ​ትን ሥጋ አት​ብሉ፤


ይል​ቁ​ንም ከል​ባ​ችን ፍር​ሀት የተ​ነሣ፦ ነገ ልጆ​ቻ​ችሁ ልጆ​ቻ​ች​ንን፦ ከእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች አም​ላክ ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጋር ምን አላ​ችሁ? እን​ዳ​ይ​ሉ​አ​ቸው ስለ​ፈ​ራን ይህን የሠ​ራ​ነው ካል​ሆነ፥ እና​ንተ የሮ​ቤ​ልና የጋድ ልጆች፥ የም​ና​ሴም ነገድ እኩ​ሌታ፥


Follow us:

Advertisements


Advertisements