Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




ኢያሱ 21:45 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

45 እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ለእ​ስ​ራ​ኤል ቤት ከተ​ና​ገ​ረው መል​ካም ነገር ሁሉ ተፈ​ጸመ እንጂ ምንም አል​ቀ​ረም።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

45 እግዚአብሔር ለእስራኤል ቤት ከሰጠው መልካም የተስፋ ቃል አንዳችም አልቀረም፤ ሁሉም ተፈጽሟል።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

45 ጌታ ለእስራኤል ቤት ከተናገረው መልካም ነገር ሁሉ ተፈጸመ እንጂ ምንም አልቀረም።

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

45 በዚህም ዐይነት እግዚአብሔር ለእስራኤል ቤት የገባው ቃል ኪዳን ሁሉ ተፈጸመ እንጂ አንድም የቀረ የለም።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

45 እግዚአብሔር ለእስራኤል ቤት ከተናገረው መልካም ነገር ሁሉ ተፈጸመ እንጂ ምንም አልቀረም።

See the chapter Copy




ኢያሱ 21:45
13 Cross References  

“እንደ ተና​ገ​ረው ተስፋ ሁሉ ለሕ​ዝቡ ለእ​ስ​ራ​ኤል ዕረ​ፍ​ትን የሰጠ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይመ​ስ​ገን፥ በባ​ሪ​ያው በሙሴ ቃል ከተ​ና​ገ​ረው ከመ​ል​ካም ቃል ሁሉ ያጐ​ደ​ለው አን​ድም ቃል የለም።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እንደ ሰው የሚ​ታ​ለል አይ​ደ​ለም። እንደ ሰው ልጅም የሚ​ዛ​ት​በት አይ​ደ​ለም፤ እርሱ ያለ​ውን አያ​ደ​ር​ገ​ው​ምን? አይ​ና​ገ​ረ​ው​ምን? አይ​ፈ​ጽ​መ​ው​ምን?


የሚጠራችሁ የታመነ ነው፤ እርሱም ደግሞ ያደርገዋል።


ከልጁ ከጌ​ታ​ችን ከኢ​የ​ሱስ ክር​ስ​ቶስ ጋር አንድ ትሆኑ ዘንድ የጠ​ራ​ችሁ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የታ​መነ ነው።


የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቃል ሐሰት ሊሆን አይ​ቻ​ልም፤ በእ​ርሱ ለተ​ማ​ፀን ተጠ​ብ​ቆ​ልን ባለ ተስ​ፋ​ች​ንም ማመ​ንን ላጸ​ናን ለእኛ ታላቅ ደስታ አለን።


የቀ​ድ​ሞ​ውን ነገር ከጥ​ንት ተና​ግ​ሬ​አ​ለሁ፤ ከአ​ፌም ወጥ​ቶ​አል፤ ድን​ገ​ትም ያደ​ረ​ግ​ሁት ምስ​ክር ሆኖ​አል፤ እር​ሱም ተፈ​ጽ​ሞ​አል።


ሳሙ​ኤ​ልም አደገ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ከእ​ርሱ ጋር ነበረ፤ ከቃ​ሉም አን​ዳች በም​ድር ላይ አይ​ወ​ድ​ቅም ነበር።


እር​ሱም አለ፥ “ለአ​ባቴ ለዳ​ዊት በአፉ የተ​ና​ገረ፥ በእ​ጁም የፈ​ጸመ የእ​ስ​ራ​ኤል አም​ላክ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይመ​ስ​ገን።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም የተ​ና​ገ​ረ​ውን ቃል አጸና፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ተስፋ እንደ ሰጠ በአ​ባቴ በዳ​ዊት ፋንታ ተነ​ሣሁ፤ በእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ዙፋን ላይ ተቀ​መ​ጥሁ፤ ለእ​ስ​ራ​ኤ​ልም አም​ላክ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ስም ቤት ሠራሁ።


ለባ​ሪ​ያህ ለአ​ባቴ ለዳ​ዊት የሰ​ጠ​ኸ​ውን ተስፋ የጠ​በ​ቅህ፥ በአ​ፍህ ተና​ግ​ረህ፥ እንደ ዛሬ ቀንም በእ​ጅህ ፈጸ​ም​ኸው።


ልቡም በፊ​ትህ የታ​መነ ሆኖ አገ​ኘ​ኸው፤ የከ​ነ​ዓ​ና​ዊ​ው​ንና የኬ​ጤ​ዎ​ና​ዊ​ውን፥ የአ​ሞ​ሬ​ዎ​ና​ዊ​ው​ንም፥ የፌ​ር​ዜ​ዎ​ና​ዊ​ው​ንም፥ የኢ​ያ​ቡ​ሴ​ዎ​ና​ዊ​ው​ንም፥ የጌ​ር​ጌ​ሴ​ዎ​ና​ዊ​ው​ንም ምድር ለእ​ር​ሱና ለዘሩ ትሰጥ ዘንድ ከእ​ርሱ ጋር ቃል ኪዳን አደ​ረ​ግህ፤ አን​ተም ጻድቅ ነህና ቃል​ህን አጸ​ናህ።


Follow us:

Advertisements


Advertisements