Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




ኢያሱ 21:2 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

2 በከ​ነ​ዓን ምድር ባለ​ችው በሴሎ፥ “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በሙሴ እጅ የም​ን​ቀ​መ​ጥ​ባ​ቸ​ውን ከተ​ሞች፥ ለከ​ብ​ቶ​ቻ​ች​ንም መሰ​ማ​ሪ​ያ​ዎች ትሰ​ጡን ዘንድ አዝ​ዞ​አል” ብለው ተና​ገ​ሩ​አ​ቸው።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

2 በከነዓን ምድር በሴሎም፣ “እግዚአብሔር የምንኖርባቸውን ከተሞች፣ ከብቶቻችን ከሚሰማሩባቸው ቦታዎች እንድትሰጡን በሙሴ በኩል አዝዞልን ነበር” አላቸው።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

2 በከነዓን ምድር ባለችው በሴሎ እንዲህ ብለው ተናገሩአቸው፦ “ጌታ በሙሴ አማካይነት የምንቀመጥባቸውን ከተሞችና ለከብቶቻችን መሰማሪያቸውን እንዲሰጠን አዝዞአል።”

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

2 በዚያም በከነዓን ምድር በምትገኘው በሴሎ ወደ እነርሱ ፊት ቀርበው፦ “እግዚአብሔር በሙሴ አማካይነት የምንኖርባቸው ከተሞችና በዙሪያቸውም ለከብቶቻችን ግጦሽ የሚሆን መሬት እንዲሰጠን አዞአል” አሉአቸው።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

2 በከነዓን ምድር ባለችው በሴሎ፦ እግዚአብሔር በሙሴ እጅ የምንቀመጥባቸውን ከተሞች፥ ለከብቶቻችንም መሰምርያዎች ትሰጡን ዘንድ አዝዞአል ብለው ተናገሩአቸው።

See the chapter Copy




ኢያሱ 21:2
9 Cross References  

የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች ማኅ​በር ሁሉ በሴሎ ተሰ​በ​ሰቡ፤ በዚ​ያም የም​ስ​ክ​ሩን ድን​ኳን ተከሉ፤ ምድ​ሩም ጸጥ ብሎ ተገ​ዛ​ላ​ቸው።


ይህ​ንም ነገር ንኡሰ ክር​ስ​ቲ​ያን ይስ​ማው፤ መል​ካ​ሙ​ንም ነገር ሁሉ ከሚ​ያ​ስ​ተ​ም​ረው ይማር።


ወይም ለመንገድ ከረጢት ወይም ሁለት እጀ ጠባብ ወይም ጫማ ወይም በትር አትያዙ፤ ለሠራተኛ ምግቡ ይገባዋልና።


የሌ​ዋ​ው​ያ​ንን ከተ​ሞች፥ በከ​ተ​ሞ​ቻ​ቸ​ውም ያሉ ቤቶ​ቻ​ቸ​ውን ሌዋ​ው​ያን ለዘ​ለ​ዓ​ለም መቤ​ዠት ይች​ላሉ።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሙሴን እን​ዳ​ዘዘ እን​ዲሁ የእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች አደ​ረጉ፤ ምድ​ሪ​ቱ​ንም ተካ​ፈሉ።


የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች እንደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ትእ​ዛዝ ከር​ስ​ታ​ቸው እነ​ዚ​ህን ከተ​ሞ​ችና መሰ​ማ​ር​ያ​ቸ​ውን ለሌ​ዋ​ው​ያን ሰጡ​አ​ቸው።


Follow us:

Advertisements


Advertisements