ኢያሱ 20:9 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)9 በማኅበሩ ፊት እስኪቆምና እስኪመረመር ድረስ ባለደሙ እንዳይገድለው ሳያውቅ ሰውን የገደለ ወደዚያ እንዲማፀን፥ ለእስራኤል ልጆች ሁሉ፥ በመካካላቸውም ለሚቀመጥ መጻተኛ የተመረጡ ከተሞች እነዚህ ናቸው። See the chapterአዲሱ መደበኛ ትርጒም9 ሳያስበው በድንገት ሰው የገደለ ማንኛውም እስራኤላዊ ወይም በመካከላቸው የሚኖር ማንኛውም መጻተኛ ወደ ተለዩት ከተሞች መሸሽ ይችላል፤ በማኅበሩ ፊት ከመቆሙ አስቀድሞም በደም ተበቃዩ መገደል የለበትም። See the chapterመጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)9 በማኅበሩ ፊት እስኪቆም ድረስ በደም ተበቃዩ እጅ እንዳይሞት ሳያውቅ ሰውን የገደለ ወደዚያ እንዲሸሽ፥ ለእስራኤል ልጆች ሁሉ በመካከላቸውም ለሚቀመጥ መጻተኛ የተለዩ ከተሞች እነዚህ ናቸው። See the chapterአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም9 ለእስራኤል ሕዝብና በመካከላቸውም ለሚኖሩ መጻተኞች መማጸኛ ይሆኑ ዘንድ የተመረጡ ከተሞች እነዚህ ነበሩ፤ ማንም ሰው በድንገተኛ አጋጣሚ ሰው ቢገድል፥ በሸንጎ ሳይፈረድበት እንዳይገደል ከእነዚያ ከተሞች ወደ አንዲቱ ሄዶ ሊበቀለው ከሚፈልገው ሰው እጅ ያመልጣል። See the chapterመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)9 በማኅበሩ ፊት እስኪቆም ድረስ በደም ተበቃዩ እጅ እንዳይሞት ሳያውቅ ሰውን የገደለ ወደዚያ እንዲሸሽ፥ ለእስራኤል ልጆች ሁሉ በመካከላቸውም ለሚቀመጥ መጻተኛ የተለዩ ከተሞች እነዚህ ናቸው። See the chapter |