Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




ኢያሱ 2:24 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

24 ኢያ​ሱ​ንም፥ “በእ​ው​ነት እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሀገ​ሩን ሁሉ በእ​ጃ​ችን አሳ​ልፎ ሰጥ​ቶ​አል፤ በዚ​ያች ምድር የሚ​ኖሩ አሕ​ዛብ ሁሉ ከእኛ የተ​ነሣ ደነ​ገጡ” አሉት።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

24 ለኢያሱም፣ “በርግጥ እግዚአብሔር ምድሪቱን በሙሉ በእጃችን አሳልፎ ሰጥቶናል፤ በዚያ የሚኖረውም ሕዝብ ሁሉ እኛን ከመፍራቱ የተነሣ ልቡ መቅለጡን አይተናል” አሉት።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

24 ኢያሱንም እንዲህ አሉት፦ “በእውነት ጌታ አገሩን ሁሉ በእጃችን አሳልፎ ሰጥቶአል፤ ከእኛም የተነሣ በአገሩ ውስጥ ያሉ ሰዎች ሁሉ በፍርሃት ቀልጠዋል።”

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

24 ለኢያሱም እንዲህ አሉት፦ “የምድሪቱ ነዋሪዎች በሙሉ እኛን በመፍራት ሐሞታቸው ስለ ፈሰሰ በእውነት እግዚአብሔር ምድሪቱን ሁሉ ለእኛ አሳልፎ ሰጥቶአል።”

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

24 ኢያሱንም፦ በእውነት እግዚአብሔር አገሩን ሁሉ በእጃችን አሳልፎ ሰጥቶአል፥ በአገሩም ውስጥ ያሉ ሰዎች ሁሉ በፊታችን ይቀልጣሉ አሉት።

See the chapter Copy




ኢያሱ 2:24
16 Cross References  

ድን​በ​ር​ህ​ንም ከኤ​ር​ትራ ባሕር እስከ ፍል​ስ​ጥ​ኤም ባሕር፥ ከም​ድረ በዳም እስከ ታላቁ እስከ ኤፍ​ራ​ጥስ ወንዝ ድረስ አሰ​ፋ​ለሁ፤ በም​ድር የሚ​ኖ​ሩ​ትን በእ​ጅህ እጥ​ላ​ለ​ሁና፤ ከአ​ን​ተም አስ​ወ​ጣ​ቸ​ዋ​ለሁ።


እን​ዲ​ህም ሆነ፤ በዮ​ር​ዳ​ኖስ ማዶ በባ​ሕር በኩል የነ​በ​ሩት የአ​ሞ​ራ​ው​ያን ነገ​ሥት ሁሉ፥ በባ​ሕ​ሩም አጠ​ገብ የነ​በሩ የፊ​ኒ​ቃ​ው​ያን ነገ​ሥት ሁሉ፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ፊት የዮ​ር​ዳ​ኖ​ስን ውኃ እስ​ኪ​ሻ​ገሩ ድረስ እን​ዳ​ደ​ረቀ በሰሙ ጊዜ፥ ልባ​ቸው ቀለጠ፤ ከእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች የተ​ነሣ አእ​ም​ሮ​አ​ቸ​ውን ሳቱ።


የዚህ ሕግ መጽ​ሐፍ ከአ​ፍህ አይ​ለይ፤ ነገር ግን የተ​ጻ​ፈ​በ​ትን ሁሉ ትጠ​ብ​ቅና ታደ​ርግ ዘንድ በቀ​ንም በሌ​ሊ​ትም አን​ብ​በው፤ የዚ​ያን ጊዜም መን​ገ​ድህ ይቀ​ና​ል​ሃል፤ አስ​ተ​ዋ​ይም ትሆ​ና​ለህ።


ያን ጊዜ የኤ​ዶም አለ​ቆች ሸሹ፤ የሞ​ዓ​ብ​ንም አለ​ቆች መን​ቀ​ጠ​ቀጥ ያዛ​ቸው፤ በከ​ነ​ዓን የሚ​ኖሩ ሁሉ ቀለጡ።


ሁለ​ቱም ጐል​ማ​ሶች ተመ​ለሱ፤ ከተ​ራ​ራ​ውም ወር​ደው ተሻ​ገሩ፤ ወደ ነዌም ልጅ ወደ ኢያሱ መጡ፤ የደ​ረ​ሰ​ባ​ቸ​ው​ንም ሁሉ አወ​ሩ​ለት።


በዚ​ያ​ችም ሌሊት እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፥ “በእ​ጅህ አሳ​ልፌ ሰጥ​ቻ​ቸ​ዋ​ለ​ሁና ተነ​ሥ​ተህ ወደ ሰፈር ውረድ።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ኢያ​ሱን አለው፥ “እነሆ፥ ኢያ​ሪ​ኮ​ንና ንጉ​ሥ​ዋን ጽኑ​ዓን፥ ኀያ​ላ​ን​ዋ​ንም በእ​ጅህ ሰጥ​ቼ​አ​ለሁ።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ኢያ​ሱን፥ “አት​ፍራ፤ አት​ደ​ን​ግጥ፤ ተዋ​ጊ​ዎ​ችን ሁሉ ከአ​ንተ ጋር ውሰድ፤ ተነ​ሥ​ተ​ህም ወደ ጋይ ውጣ፤ እነሆ፥ የጋ​ይ​ንም ንጉሥ፥ ሕዝ​ቡ​ንም ከተ​ማ​ው​ንም ምድ​ሩ​ንም በእ​ጅህ አሳ​ልፌ ሰጥ​ቼ​ሃ​ለሁ።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም፥ “ይሁዳ ይውጣ፤ እነሆ፥ ምድ​ሪ​ቱን በእጁ አሳ​ልፌ ሰጥ​ቼ​አ​ታ​ለሁ” አለ።


በሄ​ዳ​ች​ሁም ጊዜ ተዘ​ል​ለው ወደ ተቀ​መጡ ሕዝብ ትደ​ር​ሳ​ላ​ችሁ፤ ምድ​ሪ​ቱም ሰፊ ናት፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በም​ድር ካለው ነገር ሁሉ አን​ዳች የማ​ይ​ጐ​ድ​ል​ባ​ትን ስፍራ በእ​ጃ​ችሁ ሰጥ​ቶ​አል” አሉ።


Follow us:

Advertisements


Advertisements