Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




ኢያሱ 2:16 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

16 እር​ስ​ዋም፥ “የሚ​ከ​ተ​ሉ​አ​ችሁ እን​ዳ​ያ​ገ​ኙ​አ​ችሁ ወደ ተራ​ራው ሂዱ፤ የሚ​ከ​ተ​ሉ​አ​ች​ሁም እስ​ከ​ሚ​መ​ለሱ ድረስ በዚያ ሦስት ቀን ተሰ​ው​ራ​ችሁ ተቀ​መጡ፤ በኋ​ላም መን​ገ​ዳ​ች​ሁን ትሄ​ዳ​ላ​ችሁ” አለ​ቻ​ቸው።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

16 እርሷም፣ “የሚከታተሏችሁ ሰዎች እንዳያገኟችሁ ወደ ኰረብቶቹ ሂዱ፤ እነርሱ እስኪመለሱም ድረስ ሦስት ቀን በዚያ ተሸሸጉ፤ ከዚያ በኋላ መንገዳችሁን ትቀጥላላችሁ” አለቻቸው።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

16 እርሷም እንዲህ አለቻቸው፦ “አሳዳጆቹ እንዳያገኙአችሁ ወደ ተራራው ሂዱ፤ አሳዳጆቹም እስኪመለሱ ድረስ በዚያ ሦስት ቀን ተሰውራችሁ ተቀመጡ፤ ከዚያም በኋላ መንገዳችሁን ትሄዳላችሁ።”

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

16 እንዲህም ስትል መከረቻቸው፤ “ወደ ኮረብታማው አገር ሂዱ፤ ይህ ካልሆነ ግን የንጉሡ መልእክተኞች ሊያገኙአችሁ ይችላሉ፤ በዚያም እነርሱ እስኪመለሱ እስከ ሦስት ቀን ድረስ ተደብቃችሁ ቈዩ፤ ከዚያን በኋላ ጒዞአችሁን መቀጠል ትችላላችሁ።”

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

16 እርስዋም፦ አሳዳጆቹ እንዳያገኙአችሁ ወደ ተራራው ሂዱ፥ አሳዳጆቹም እስኪመለሱ ድረስ በዚያ ሦስት ቀን ተሰውራችሁ ተቀመጡ፥ ኋላም መንገዳችሁን ትሄዳላችሁ አለቻቸው።

See the chapter Copy




ኢያሱ 2:16
6 Cross References  

እንደዚሁም ጋለሞታይቱ ረዓብ ደግሞ መልእክተኞቹን ተቀብላ በሌላ መንገድ በሰደደቻቸው ጊዜ በሥራ አልጸደቀችምን?


ዳዊ​ትም በም​ድረ በዳ በጠ​ባቡ በማ​ሴ​ሬም ይኖር ነበር፥ በአ​ው​ክ​ሞ​ዲስ ውስ​ጥም በዚፍ ተራራ ምድረ በዳ ተቀ​መጠ፤ ሳኦ​ልም ሁል​ጊዜ ይፈ​ል​ገው ነበር፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ግን በእጁ አሳ​ልፎ አል​ሰ​ጠ​ውም።


አቤቱ፥ አድ​ነኝ፥ ደግ ሰው አል​ቆ​አ​ልና፥ ከሰው ልጆ​ችም መተ​ማ​መን ጐድ​ሎ​አ​ልና።


እነ​ር​ሱም ወጥ​ተው ወደ ተራ​ራው ሄዱ፤ የሚ​ከ​ተ​ሉ​አ​ቸ​ውና የሚ​ፈ​ል​ጉ​አ​ቸ​ውም እስ​ኪ​መ​ለሱ ሦስት ቀን በዚያ ተቀ​መጡ፤ በመ​ን​ገ​ዱም አላ​ገ​ኙ​አ​ቸ​ውም።


ቤቷም በከ​ተማ ቅጥር የተ​ጠጋ ነበ​ረና፥ እር​ስ​ዋም በቅ​ጥሩ ላይ ተቀ​ምጣ ነበ​ርና በመ​ስ​ኮቱ በገ​መድ አወ​ረ​ደ​ቻ​ቸው።


Follow us:

Advertisements


Advertisements