Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




ኢያሱ 17:13 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

13 የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች በረ​ቱ​ባ​ቸው፤ ከነ​ዓ​ና​ው​ያ​ን​ንም ገዙ​አ​ቸው፤ ነገር ግን ፈጽ​መው አላ​ጠ​ፉ​አ​ቸ​ውም።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

13 እስራኤላውያን በበረቱ ጊዜ ግን ከነዓናውያንን የጕልበት ሥራ እንዲሠሩ አስገደዷቸው እንጂ ከዚያ ፈጽመው አላባረሯቸውም ነበር።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

13 የእስራኤልም ልጆች በጸኑ ጊዜ ከነዓናውያንን የጉልበት ሥራ እንዲሠሩ አደረጉአቸው፥ ፈጽመውም አላሳደዱአቸውም።

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

13 እስራኤላውያን በኀይል እየበረቱ ቢሄዱም እንኳ ከነዓናውያንን ሁሉ አላባረሩአቸውም፤ ነገር ግን የጒልበት ሥራ እንዲሠሩላቸው ያስገድዱአቸው ነበር።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

13 የእስራኤልም ልጆች በጸኑ ጊዜ ከነዓናውያንን የጉልበት ግብር አስገበሩአቸው፥ ፈጽመውም አላሳደዱአቸውም።

See the chapter Copy




ኢያሱ 17:13
13 Cross References  

በጋ​ዜ​ርም የተ​ቀ​መ​ጡ​ትን ከነ​ዓ​ና​ው​ያ​ንን ኤፍ​ሬም አላ​ጠ​ፋ​ቸ​ውም፤ እስከ ዛሬም ድረስ ከነ​ዓ​ና​ው​ያን በኤ​ፍ​ሬም መካ​ከል ተቀ​ም​ጠ​ዋል፤ ገባ​ርም ሆኑ።


በሚ​ያ​ስ​ች​ለኝ በክ​ር​ስ​ቶስ ሁሉን እች​ላ​ለሁ።


ነገር ግን በጌታችንና በመድኃኒታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋና እውቀት እደጉ። ለእርሱ አሁንም እስከ ዘላለምም ቀን ድረስ ክብር ይሁን፤ አሜን።


እን​ግ​ዲ​ህስ ወዲህ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርና በኀ​ይሉ ጽናት በርቱ።


በሳ​ኦል ቤትና በዳ​ዊት ቤት መካ​ከል ለብዙ ጊዜ ጦር​ነት ሆነ፤ የዳ​ዊት ቤት እየ​በ​ረታ፥ የሳ​ኦል ቤት ግን እየ​ደ​ከመ የሚ​ሄድ ሆነ።


አሞ​ሬ​ዎ​ና​ው​ያ​ንም ድብና ቀበ​ሮ​ዎች በሚ​ኖ​ሩ​በት በመ​ር​ስ​ኖ​ኖስ ተራራ መቀ​መጥ ጀመሩ፤ ነገር ግን የዮ​ሴፍ ወገን እጅ በአ​ሞ​ሬ​ዎ​ና​ው​ያን ላይ ጸናች፤ ገባ​ርም አደ​ረ​ጉ​አ​ቸው።


ንፍ​ታ​ሌ​ምም የቤ​ት​ሳ​ሚ​ስ​ንና የቤ​ቴ​ኔ​ስን ሰዎች አላ​ጠ​ፋ​ቸ​ውም፤ በም​ድ​ሩም በተ​ቀ​መ​ጡት በከ​ነ​ዓ​ና​ው​ያን መካ​ከል ተቀ​መጡ፤ ነገር ግን በቤ​ት​ሳ​ሚ​ስና በቤ​ቴ​ኔስ የሚ​ኖሩ ሰዎች ገባ​ሮች ሁኑ​ላ​ቸው።


ዛብ​ሎ​ንም በቄ​ድ​ሮ​ንና በአ​ማን የሚ​ኖ​ሩ​ትን ሰዎች አላ​ጠ​ፋ​ቸ​ውም፤ ነገር ግን ከነ​ዓ​ና​ው​ያን በመ​ካ​ከ​ላ​ቸው ተቀ​መጡ፤ ግብ​ርም የሚ​ገ​ብ​ሩ​ላ​ቸው ሆኑ።


እስ​ራ​ኤ​ልም በበ​ረቱ ጊዜ ከነ​ዓ​ና​ው​ያ​ንን ገባ​ሮች አደ​ረ​ጉ​አ​ቸው፤ ነገር ግን ፈጽ​መው አላ​ጠ​ፏ​ቸ​ውም።


ዕረ​ፍ​ትም መል​ካም መሆ​ን​ዋን፥ ምድ​ሪ​ቱም የለ​ማች መሆ​ን​ዋን በአየ ጊዜ ምድ​ርን ያር​ሳት ዘንድ ትከ​ሻ​ውን ዝቅ አደ​ረገ፤ በሥ​ራም ገበሬ ሆነ።


የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች ያጠ​ፉ​አ​ቸው ዘንድ ያል​ቻ​ሉ​ትን፥ ልጆ​ቻ​ቸ​ውን ሰሎ​ሞን እሰከ ዛሬ ድረስ ገባ​ሮች አድ​ርጎ መለ​መ​ላ​ቸው።


Follow us:

Advertisements


Advertisements