ኢያሱ 16:6 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)6 ድንበሩም ወደ ምዕራብ ወደ አካስሞን በቴርማ ሰሜን ያልፋል፤ ወደ ምሥራቅም ወደ ቲናስና ሴላስ ይዞራል፥ ከምሥራቅም ወደ ኢያኖክ ያልፋል። See the chapterአዲሱ መደበኛ ትርጒም6 እስከ ባሕሩ ይዘልቃል። በስተሰሜን ደግሞ ከሚክምታት ተነሥቶ በምሥራቅ በኩል ወደ ተአናት ሴሎ ይታጠፍና ከዚያ በማለፍ እስከ ኢያኖክ ምሥራቅ ይዘልቃል። See the chapterመጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)6 ከዚያም ተነሥቶ ድንበሩ ወደ ባሕሩ በኩል ወጣ፤ በሰሜን በኩል ሚክምታት ይገኝ ነበር፤ ድንበሩም ወደ ምሥራቅ ወደ ተአናትሴሎ ዞረ፥ ወደ ኢያኖክ በምሥራቅ በኩል አለፈ፥ See the chapterአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም6 ከዚያም አልፎ እስከ ሜዲቴራኒያን ባሕር ይደርሳል፤ ሰሜናዊ ድንበራቸውም ሚክመታት ነው፤ ከዚያም ተነሥቶ ወደ ታአናት ሺሎ ታጥፎ በምሥራቅ በኩል በማለፍ ወደ ያኖሐ ይሄዳል። See the chapterመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)6 ድንበሩም ወደ ምዕራብ ወደ ሚክምታት በሰሜን በኩል ወጣ፥ ድንበሩም ወደ ምሥራቅ ወደ ተአናትሴሎ ዞረ፥ ወደ ኢያኖክ በምሥራቅ በኩል አለፈ፥ See the chapter |