ኢያሱ 16:3 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)3 ወደ ምዕራብም እስከ የፍሌጣውያን ዳርቻ እስከ ታችኛው ቤቶሮን ዳርቻ ድረስ ይወርዳል፤ መውጫውም በባሕሩ አጠገብ ነበረ። See the chapterአዲሱ መደበኛ ትርጒም3 በዚያም በምዕራብ በኩል ቍልቍል ወደ የፍሌጣውያን ግዛት እስከ ታችኛው ቤትሖሮን ምድር ይወርድና ወደ ጌዝር ዘልቆ ባሕሩ ላይ ይቆማል። See the chapterመጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)3 ወደ ምዕራብም እስከ የፍሌጣውያን ድንበር እስከ ታችኛው ቤትሖሮን ድንበር እስከ ጌዝር ድረስ ወረደ፥ መጨረሻውም በባሕሩ አጠገብ ነበረ። See the chapterአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም3 ከዚያም በምዕራብ በኩል ወደሚገኙት ወደ ያፍሌጣውያን ይዞታ በመዝለቅ እስከ ታችኛው ቤትሖሮን ይደርሳል፤ ከዚያም ወደ ጌዜር ያልፍና መጨረሻው የሜድትራኒያን ባሕር ይሆናል። See the chapterመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)3 ወደ ምዕራብም እስከ የፍሌጣውያን ዳርቻ እስከ ታችኛው ቤትሖሮን ዳርቻ እስከ ጌዝር ድረስ ወረደ፥ መውጫውም በባሕሩ አጠገብ ነበረ። See the chapter |