ኢያሱ 15:10 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)10 ድንበሩም ከበኣላ በባሕር በኩል ያልፋል፤ ከዚያም በኢያሪም ከተማ ደቡብ በኩልና በኪስሎን ሰሜን በኩል ወደ አሥራቱስ ድንበር ያልፋል፤ በፀሐይ ከተማም ላይ ይወርዳል፤ በሊባም በኩል ያልፋል። See the chapterአዲሱ መደበኛ ትርጒም10 ከዚያም ከበኣላ በምዕራብ በኩል አድርጎ ወደ ሴይር ይታጠፍና ክሳሎን ተብሎ በሚጠራው በይዓሪም ኰረብታ ሰሜናዊ ተረተር ዐልፎ ቍልቍል ወደ ቤትሳሚስ በመውረድ ወደ ተምና ይሻገራል። See the chapterመጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)10 ድንበሩም ከበኣላ በምዕራብ በኩል ወደ ሴይር ተራራ ዞረ፤ ክሳሎን ወደምትባል ወደ ይዓርም ተራራ ወገን በሰሜን በኩል አለፈ፤ ወደ ቤት ሳሚስ ወረደ፥ በተምና በኩልም አለፈ። See the chapterአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም10 ድንበሩም በበዓላ ዙሪያ በስተምዕራብ በኩል ወደ ኤዶም ተራራ ይዞራል፤ በይዓሪም ወይም ክሳሎን ተብሎ ወደሚጠራው ተራራ ቊልቊለት በኩል አድርጎ ያልፋል፤ ወደ ቤትሼሜሽም ይወርዳል፤ በቲምናም በኩል ያልፋል። See the chapterመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)10 ድንበሩም ከበኣላ በምዕራብ በኩል ወደ ሴይር ተራራ ዞረ፥ ክሳሎን ወደምትባል ወደ ይዓርም ተራራ ወገን በሰሜን በኩል አለፈ፥ ወደ ቤትሳሚስ ወረደ፥ በተምና በኩልም አለፈ። See the chapter |