Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




ኢያሱ 13:12 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

12 በባ​ሳን የነ​በ​ረ​ውን፥ በአ​ስ​ታ​ሮ​ትና በኤ​ን​ድ​ራ​ይን የነ​ገ​ሠ​ውን የዐ​ግን መን​ግ​ሥት ሁሉ፤ እር​ሱም ከረ​ዓ​ይት የቀረ ነበረ፤ እነ​ዚ​ህ​ንም ሙሴ አወ​ጣ​ቸው፤ ገደ​ላ​ቸ​ውም።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

12 ይህም በአስታሮትና በኤድራይ ሆኖ የገዛውን በባሳን ያለውን የዐግን መንግሥት በሙሉ ያጠቃልላል፤ ዐግም በሕይወት ከቀሩት ከመጨረሻዎቹ ከራፋይም ዘሮች አንዱ ነበር። እነዚህንም ሙሴ ድል አደረጋቸው፤ ምድራቸውንም ያዘ፤

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

12 በባሳን የነበረውን በአስታሮትና በኤድራይ የነገሠውን የዐግን መንግሥት ሁሉ፤ እርሱም ብቻ ከራፋይም የቀረ ነበረ፤ እነዚህንም ሙሴ ድል አድርጎ አስወጣቸው።

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

12 ከራፋይማውያን ተራፊ የነበረውን በአስታሮትና በኤድራይ የነገሠውን የባሳንን ንጉሥ የዖግን መንግሥት ሁሉ ይጨምራል። ሙሴም እነዚህን ድል አድርጎ አስወጣቸው።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

12 ባሳንንም ሁሉ እስከ ሰልካ ድረስ፥ በባሳን የነበረውን በአስታሮትና በኤድራይ የነገሠውን የዐግን መንግሥት ሁሉ፥ እርሱም ከራፋይም የቀረ ነበረ፥ እነዚህንም ሙሴ መታቸው አወጣቸውም።

See the chapter Copy




ኢያሱ 13:12
7 Cross References  

ከረ​ዓ​ይት ወገን የቀረ፥ በአ​ስ​ጣ​ሮ​ትና በኤ​ን​ድ​ራ​ይን የተ​ቀ​መ​ጠው፥


በሐ​ሴ​ቦን ተቀ​ምጦ የነ​በ​ረ​ውን የአ​ሞ​ሬ​ዎ​ና​ው​ያ​ንን ንጉሥ ሴዎ​ንን፥ በአ​ስ​ጣ​ሮ​ትና በኤ​ድ​ራ​ይን ተቀ​ምጦ የነ​በ​ረ​ው​ንም የባ​ሳ​ንን ንጉሥ ዐግን ከገ​ደ​ሉት በኋላ፥


የእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ግን ጌሴ​ሪ​ያ​ው​ያ​ንን፥ መከ​ጢ​ያ​ው​ያ​ን​ንና ከነ​ዓ​ና​ው​ያ​ንን አላ​ጠ​ፉ​አ​ቸ​ውም፤ እስከ ዛሬም ድረስ ጌሴ​ሪና መከጢ በእ​ስ​ራ​ኤል መካ​ከል ይኖ​ራሉ።


በባ​ሳ​ንም ያሉት የዐግ መን​ግ​ሥት ከተ​ሞች፥ አስ​ጣ​ሮ​ትና ኤድ​ራ​ይን ነበረ። እነ​ዚ​ህም ለም​ናሴ ልጅ ለማ​ኪር ልጆች ሆኑ፤ ለም​ናሴ ልጅ ለማ​ኪር ልጆች እኩ​ሌ​ታም በየ​ወ​ገ​ኖ​ቻ​ቸው ይህ ነበረ።


Follow us:

Advertisements


Advertisements