Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




ኢያሱ 12:2 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

2 በሐ​ሴ​ቦን የተ​ቀ​መ​ጠው፥ በአ​ር​ኖ​ንም ሸለቆ አጠ​ገብ ካለ​ችው ከአ​ሮ​ዔር፥ ከሸ​ለ​ቆ​ውም መካ​ከል ጀምሮ የገ​ለ​ዓ​ድን እኩ​ሌታ እስከ ኢያ​ቦቅ ወንዝ እስከ አሞን ልጆች ዳርቻ ድረስ፤

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

2 መቀመጫውን በሐሴቦን አድርጎ የገዛው የአሞራውያን ንጉሥ ሴዎን፣ ከአርኖን ሸለቆ ዳርቻ ላይ ካለችው ከአሮዔር ማለት ከሸለቆው መካከል አንሥቶ፣ የአሞናውያን ወሰን እስከ ሆነው እስከ ያቦቅ ወንዝ ድረስ ገዝቷል፤ ይህም የገለዓድን እኩሌታ ይጨምራል።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

2 በሐሴቦን የተቀመጠው የአሞራውያን ንጉሥ ሴዎን፥ ይገዛ የነበረው በአርኖን ሸለቆ አጠገብ ካለችው ከአሮዔር፥ ከሸለቆውም መካከል ጀምሮ የገለዓድን እኩሌታ እስከ ያቦቅ ወንዝ እስከ አሞን ልጆች ዳርቻ ድረስ ሲሆን፥

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

2 በሐሴቦን ሆኖ የሚገዛው የአሞራውያን ንጉሥ ሲሖን ነበር፤ ግዛቱም የገለዓድን እኩሌታ በማጠቃለል፥ በአርኖን ሸለቆ ዳርቻ ከምትገኘው ከዓሮዔር ተነሥቶ በዚያ ሸለቆ መካከል ያለችውን የዐሞናውያን ወሰን እስከሆነው እስከ ያቦቅ ወንዝ ይደርስ ነበር፤

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

2 በሐሴቦን የተቀመጠው፥ በአርኖንም ሸለቆ አጠገብ ካለችው ከአሮዔር፥ ከሸለቆውም መካከል ጀምሮ የገለዓድን እኩሌታ እስከ ያቦቅ ወንዝ እስከ አሞን ልጆች ዳርቻ ድረስ፥

See the chapter Copy




ኢያሱ 12:2
12 Cross References  

በዚ​ያ​ችም ሌሊት ተነሣ፥ ሁለ​ቱን ሚስ​ቶ​ቹ​ንና ሁለ​ቱን ዕቁ​ባ​ቶ​ቹን ዐሥራ አን​ዱ​ንም ልጆ​ቹን ይዞ የያ​ቦ​ቅን ወንዝ ተሻ​ገረ።


እስ​ራ​ኤ​ልን ከመ​ካ​ከ​ላ​ቸው ያወጣ፤ ምሕ​ረቱ ለዘ​ለ​ዓ​ለም ነውና፤


“መን​ግ​ሥ​ታ​ት​ንና አሕ​ዛ​ብን ዕድል ፈንታ አድ​ር​ገህ ሰጠ​ሃ​ቸው፤ የሐ​ሴ​ቦ​ንን ንጉሥ የሴ​ዎ​ንን ምድር፥ የባ​ሳ​ን​ንም ንጉሥ የዐ​ግን ምድር ወረሱ።


ከአ​ር​ኖ​ንም እስከ ያቦቅ ድረስ፥ ከም​ድረ በዳ​ውም እስከ ዮር​ዳ​ኖስ ድረስ የአ​ሞ​ሬ​ዎ​ና​ው​ያ​ንን አው​ራጃ ሁሉ ወረሱ።


የአ​ሞ​ንም ልጆች ንጉሥ የዮ​ፍ​ታ​ሔን መል​እ​ክ​ተ​ኞች፥ “እስ​ራ​ኤል ከግ​ብፅ በወጣ ጊዜ ከአ​ር​ኖን ጀምሮ እስከ ያቦ​ቅና እስከ ዮር​ዳ​ኖስ ድረስ ምድ​ሬን ስለ ወሰደ ነው፤ አሁ​ንም በሰ​ላም መል​ሱ​ልኝ” ብሎ መለ​ሰ​ላ​ቸው።


እስከ ናባ​ውና እስከ በኣ​ል​ሜ​ዎን ድረስ በአ​ሮ​ዔር የተ​ቀ​መ​ጠው የኢ​ዩ​ኤል ልጅ የሰ​ማዕ ልጅ የዖ​ዛዝ ልጅ ቤላ፤


በአ​ሮ​ዔር የም​ት​ኖሪ ሆይ! በመ​ን​ገድ አጠ​ገብ ቆመሽ ተመ​ል​ከቺ፤ የሸ​ሸ​ው​ንና ያመ​ለ​ጠ​ውን፦ ምን ሆኖ​አል? ብለሽ ጠይ​ቂው።


በሐ​ሴ​ቦን ተቀ​ምጦ የነ​በ​ረ​ውን የአ​ሞ​ሬ​ዎ​ና​ው​ያ​ንን ንጉሥ ሴዎ​ንን፥ በአ​ስ​ጣ​ሮ​ትና በኤ​ድ​ራ​ይን ተቀ​ምጦ የነ​በ​ረ​ው​ንም የባ​ሳ​ንን ንጉሥ ዐግን ከገ​ደ​ሉት በኋላ፥


Follow us:

Advertisements


Advertisements