ኢያሱ 11:21 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)21 በዚያ ጊዜም ኢያሱ ሄደ፤ በተራራማውም ሀገር የሚኖሩ ኤናቃውያንን ከኬብሮንና ከዳቤር፥ ከአናቦትም፥ ከእስራኤልም ተራራ ሁሉ፥ ከይሁዳም ተራራ ሁሉ አጠፋቸው፤ ኢያሱም ከከተሞቻቸው ጋር ፈጽሞ አጠፋቸው። See the chapterአዲሱ መደበኛ ትርጒም21 በዚያ ጊዜ ኢያሱ ሄዶ በተራራማው አገር፣ ማለት በኬብሮን፣ በዳቤርና በዓናብ እንዲሁም በመላው የይሁዳና የእስራኤል ተራራማ አገሮች ያሉትን የዔናቅን ዘሮች ከነከተሞቻቸው በሙሉ ደመሰሳቸው። See the chapterመጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)21 በዚያን ጊዜም ኢያሱ መጣ፥ ከተራራማውም አገር ከኬብሮንም ከዳቤርም ከአናብም ከእስራኤልም ተራራማ ሁሉ ከይሁዳም ተራራማ ሁሉ የዔናቅን ልጆች ገደለ፤ ኢያሱም ከከተሞቻቸው ጋር ፈጽሞ አጠፋቸው። See the chapterአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም21 በዚህን ጊዜ ዘምቶ ረጃጅሞች የሆኑትን የዐናቅን ዘሮች ደመሰሰ፤ እነርሱም በኮረብታማው አገር በኬብሮን፥ በደቢር፥ በዐናብ፥ በይሁዳና በእስራኤል ኮረብታማ አገሮች የሚኖሩ ነበሩ። ኢያሱ እነዚህን ሕዝቦችና ከተሞቻቸውን ሁሉ ደመሰሰ። See the chapterመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)21 በዚያን ጊዜም ኢያሱ መጣ፥ ከተራራማውም አገር ከኬብሮንም ከዳቤርም ከአናብም ከእስራኤልም ተራራማ ሁሉ ከይሁዳም ተራራማ ሁሉ የዔናቅን ልጆች ገደለ፥ ኢያሱም ከከተሞቻቸው ጋር ፈጽሞ አጠፋቸው። See the chapter |