Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




ዮናስ 1:14 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

14 ሁሉም አንድ ሆነው ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጮኹ፤ “አቤቱ! አንተ እንደ ወደ​ድህ አድ​ር​ገ​ሃ​ልና ስለ​ዚህ ሰው ነፍስ አታ​ጥ​ፋን፤ ንጹሕ ደም​ንም አታ​ድ​ር​ግ​ብን።” አሉ።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

14 “እግዚአብሔር ሆይ፤ እባክህ በዚህ ሰው ነፍስ ምክንያት አታጥፋን፤ የዚህ ንጹሕ ሰው ደምም በእኛ ላይ አይሁን፤ እግዚአብሔር ሆይ፤ አንተ የወደድኸውን አድርገሃልና” ብለው ወደ እግዚአብሔር ጮኹ።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

14 ስለዚህ ወደ ጌታ ጮኹ፥ እንዲህም አሉ፦ “ጌታ ሆይ! እባክህ ስለዚህ ሰው ነፍስ እንዳንጠፋ እንለምንሃለን፥ ንጹሕንም ደም በእኛ ላይ አታድርግ፤ ጌታ ሆይ ደስ የሚያሰኝህን አድርገሃልና።”

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

14 ስለዚህ “ጌታ እግዚአብሔር ሆይ! የዚህ ሰው ሕይወት እንዲጠፋ ብናደርግ አታጥፋን፤ አንተ የፈቀድከውን ስላደረግህ ንጹሕ ደም እንዳፈሰስን አድርገህ አትቊጠርብን!” በማለት ወደ እግዚአብሔር ጮኹ።

See the chapter Copy




ዮናስ 1:14
15 Cross References  

ስላ​ደ​ረ​ገ​ልኝ ሁሉ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ምንን እከ​ፍ​ለ​ዋ​ለሁ?


ምድ​ርን በውኃ ላይ ያጸና፤ ምሕ​ረቱ ለዘ​ለ​ዓ​ለም ነውና፤


አቤቱ፥ ከግ​ብፅ ምድር የተ​ቤ​ዠ​ኸ​ውን ሕዝ​ብ​ህን እስ​ራ​ኤ​ልን ይቅር በል፤ በሕ​ዝ​ብ​ህም በእ​ስ​ራ​ኤል ላይ የን​ጹ​ሑን ደም በደል አት​ቍ​ጠር’ ብለው ይና​ገሩ፤ ስለ ደሙም ይሰ​ረ​ይ​ላ​ቸ​ዋል።


እንደ ፈቃዱ ምክር ሁሉን የሚ​ሠራ እንደ እርሱ አሳብ አስ​ቀ​ድ​መን የተ​ወ​ሰን በእ​ርሱ ርስ​ትን ተቀ​በ​ልን።


አዎን አባት ሆይ! ፈቃድህ በፊትህ እንዲህ ሆኖአልና።


ሰዎ​ቹም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን እጅግ ፈሩ፤ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም መሥ​ዋ​ዕት አቀ​ረቡ፤ ስእ​ለ​ት​ንም ተሳሉ።


መር​ከ​በ​ኞ​ቹም ፈሩ፤ እያ​ን​ዳ​ን​ዱም ወደ አም​ላኩ ጮኸ፤ መር​ከ​ቢ​ቱም እን​ድ​ት​ቀ​ል​ል​ላ​ቸው በው​ስ​ጥዋ የነ​በ​ረ​ውን ዕቃ ወደ ባሕር ጣሉት፤ ዮናስ ግን ወደ መር​ከቡ ውስ​ጠ​ኛው ክፍል ወርዶ ነበር፥ ተኝ​ቶም ያን​ኳ​ርፍ ነበር።


እንደ ወደ​ደም በእ​ርሱ የወ​ሰ​ነ​ውን፥ የፈ​ቃ​ዱን ምሥ​ጢር ገለ​ጠ​ልን።


አረ​ማ​ው​ያ​ንም እፉ​ኝቱ በጳ​ው​ሎስ እጅ ላይ ተን​ጠ​ል​ጥላ ባዩ ጊዜ እርስ በር​ሳ​ቸው፥ “ይህ ሰው ነፍሰ ገዳይ ይመ​ስ​ላል፤ ከባ​ሕር እንኳ በደ​ኅና ቢወ​ጣም በሕ​ይ​ወት ይኖር ዘንድ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፍርድ አል​ተ​ወ​ውም” አሉ።


አቤቱ፥ በመ​ከ​ራዬ ጊዜ አሰ​ብ​ኹህ፤ በጥ​ቂት መከ​ራም ገሠ​ጽ​ኸኝ።


የሰ​ውን ደም የሚ​ያ​ፈ​ስስ ሁሉ ስለ​ዚያ ደም ፈንታ ደሙ ይፈ​ስ​ሳል፤ ሰውን በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መልክ ፈጥ​ሬ​ዋ​ለ​ሁና።


ሰዎቹ ግን ወደ ምድሩ ሊመ​ለሱ አጥ​ብ​ቀው ቀዘፉ፤ ዳሩ ግን ባሕሩ እጅግ አብ​ዝቶ ይና​ወ​ጥ​ባ​ቸው ነበ​ርና አል​ቻ​ሉም።


ሰዎ​ችና እን​ስ​ሶ​ችም ማቅ ይል​በሱ፤ ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በአ​ን​ድ​ነት ይጩኹ፤ ሰዎ​ችም ሁሉ ከክፉ መን​ገ​ዳ​ቸ​ውና በእ​ጃ​ቸው ከአ​ለው ግፍ ይመ​ለሱ።


Follow us:

Advertisements


Advertisements