Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




ዮሐንስ 9:21 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

21 አሁን ግን እን​ዴት እን​ደ​ሚ​ያይ ዐይ​ኖ​ቹ​ንም ማን እንደ አበ​ራ​ለት አና​ው​ቅም፤ እር​ሱን ጠይ​ቁት፤ ዐዋቂ ነውና፤ ስለ ራሱም መና​ገር ይች​ላ​ልና።”

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

21 አሁን ግን እንዴት ማየት እንደ ቻለና ዐይኖቹን ማን እንደ ከፈተለት እኛ አናውቅም። ሙሉ ሰው ስለ ሆነ፣ ስለ ራሱ መናገር ይችላልና እርሱን ጠይቁት።”

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

21 ዳሩ ግን አሁን እንዴት ማየት እንደቻለ አናውቅም፤ ወይም ዐይኖቹን ማን እንደ ከፈተለት እኛ አናውቅም፤ እርሱን ጠይቁት፤ እርሱ ሙሉ ሰው ነው፤ እርሱ ስለ እራሱ መናገር ይችላል፤” አሉ።

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

21 ነገር ግን አሁን እንዴት እንደሚያይና ዐይኖቹንም ማን እንደአበራለት አናውቅም፤ እርሱን ጠይቁት፤ እርሱ በዕድሜው ሙሉ ሰው ስለ ሆነ ስለ ራሱ መናገር ይችላል።”

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

21 ዳሩ ግን አሁን እንዴት እንዳየ አናውቅም፥ ወይም ዓይኖቹን ማን እንደ ከፈተ እኛ አናውቅም፤ ጠይቁት እርሱ ሙሉ ሰው ነው፤ እርሱ ስለ ራሱ ይናገራል” አሉ።

See the chapter Copy




ዮሐንስ 9:21
7 Cross References  

ወላ​ጆ​ቹም መል​ሰው እን​ዲህ አሉ፥ “ይህ ልጃ​ችን እንደ ሆነ፥ ዕዉር ሆኖም እንደ ተወ​ለደ እና​ው​ቃ​ለን።


ወላ​ጆቹ አይ​ሁ​ድን ስለ ፈሩ ይህን አሉ፥ “እርሱ ክር​ስ​ቶስ ነው ብሎ በእ​ርሱ የሚ​ያ​ምን ቢኖር ከም​ኵ​ራብ ይውጣ” ብለው አይ​ሁድ ተስ​ማ​ም​ተው ነበ​ርና።


ስለ​ዚ​ህም ወላ​ጆቹ፥ “ዐዋቂ ነውና እር​ሱን ጠይ​ቁት” አሉ።


ከዚ​ህም በኋላ ጌታ​ችን ኢየ​ሱስ ከእ​ርሱ ጋር ሲሄድ ሰዎች ያጨ​ና​ን​ቁት ነበር፤ ከዐ​ሥራ ሁለት ዓመ​ትም ጀምሮ ደም ይፈ​ስ​ሳት የነ​በ​ረች ሴት መጣች፤ ገን​ዘ​ብ​ዋ​ንም ሁሉ ለባ​ለ​መ​ድ​ኀ​ኒ​ቶች ሰጥታ ጨርሳ ነበር፤ ነገር ግን ሊያ​ድ​ናት የቻለ ማንም አል​ነ​በ​ረም።


በዚ​ያም ከታ​መመ ሠላሳ ስም​ንት ዓመት የሆ​ነው አንድ ሰው ነበር።


እነ​ር​ሱም፥ “ዐይ​ኖ​ችህ እን​ዴት ተገ​ለጡ?” አሉት።


በዚ​ያም ኤንያ የተ​ሰኘ ሰውን አገኘ፤ እር​ሱም ታሞ በአ​ልጋ ከተኛ ስም​ንት ዓመት ሆኖት ነበረ፤ ሽባ ነበ​ርና።


Follow us:

Advertisements


Advertisements