Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




ዮሐንስ 9:2 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

2 ደቀ መዛ​ሙ​ር​ቱም፥ “መም​ህር ሆይ፥ ይህ ሰው ዕዉር ሆኖ የተ​ወ​ለ​ደው በማን ኀጢ​ኣት ነው? በራሱ ነውን? ወይስ በወ​ላ​ጆቹ?” ብለው ጠየ​ቁት።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

2 ደቀ መዛሙርቱም፣ “ረቢ፤ ይህ ሰው ዐይነ ስውር ሆኖ እንዲወለድ ኀጢአት የሠራ ማን ነው? እርሱ ራሱ ወይስ ወላጆቹ?” ብለው ጠየቁት።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

2 ደቀ መዛሙርቱም “መምህር ሆይ! ይህ ሰው ዐይነ ስውር ሆኖ እንዲወለድ ኃጢአትን የሠራው ማን ነው? እርሱ ነው ወይስ ወላጆቹ?” ብለው ጠየቁት።

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

2 ደቀ መዛሙርቱ ኢየሱስን “መምህር ሆይ፥ ይህ ሰው ዕውር ሆኖ የተወለደው በማን ኃጢአት ነው? በራሱ ኃጢአት ነውን ወይስ በወላጆቹ?” ሲሉ ጠየቁት።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

2 ደቀ መዛሙርቱም፦ “መምህር ሆይ፥ ይህ ሰው ዕውር ሆኖ እንዲወለድ ኃጢአት የሠራ ማን ነው? እርሱ ወይስ ወላጆቹ?” ብለው ጠየቁት።

See the chapter Copy




ዮሐንስ 9:2
9 Cross References  

ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም መልሶ እን​ዲህ አላ​ቸው፥ “ይህች መከራ ስለ አገ​ኘ​ቻ​ቸው እነ​ዚህ ገሊ​ላ​ው​ያን ከገ​ሊላ ሰዎች ሁሉ ይልቅ ተለ​ይ​ተው ኀጢ​ኣ​ተ​ኞች የሆኑ ይመ​ስ​ሉ​አ​ች​ኋ​ልን?


እነ​ር​ሱም መል​ሰው፥ “ራስህ በኀ​ጢ​ኣት የተ​ወ​ለ​ድህ አንተ እኛን ታስ​ተ​ም​ረ​ና​ለ​ህን?” አሉት፤ ወደ ውጭም አወ​ጡት።


አረ​ማ​ው​ያ​ንም እፉ​ኝቱ በጳ​ው​ሎስ እጅ ላይ ተን​ጠ​ል​ጥላ ባዩ ጊዜ እርስ በር​ሳ​ቸው፥ “ይህ ሰው ነፍሰ ገዳይ ይመ​ስ​ላል፤ ከባ​ሕር እንኳ በደ​ኅና ቢወ​ጣም በሕ​ይ​ወት ይኖር ዘንድ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፍርድ አል​ተ​ወ​ውም” አሉ።


አት​ስ​ገ​ድ​ላ​ቸው፤ አታ​ም​ል​ካ​ቸ​ውም፤ እኔ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አም​ላ​ክህ ቀና​ተኛ አም​ላክ ነኝና። በሚ​ጠ​ሉኝ እስከ ሦስ​ተ​ኛና አራ​ተኛ ትው​ልድ ድረስ የአ​ባ​ቶ​ችን ኀጢ​አት በል​ጆች ላይ የማ​መጣ፤


እነርሱም “አንዳንዱ መጥምቁ ዮሐንስ፥ ሌሎችም ኤልያስ፥ ሌሎችም ኤርምያስ ወይም ከነቢያት አንዱ ነው፤” ይላሉ አሉት።


በገበያም ሰላምታና ‘መምህር ሆይ! መምህር ሆይ!’ ተብለው እንዲጠሩ ይወዳሉ።


እናንተ ግን ‘መምህር’ ተብላችሁ አትጠሩ፤ መምህራችሁ አንድ ስለ ሆነ እናንተም ሁላችሁ ወንድማማች ናችሁ።


በዚ​ህም ጊዜ ደቀ መዛ​ሙ​ርቱ፥ “መም​ህር ሆይ፥ እህል ብላ” ብለው ለመ​ኑት።


ከዚ​ያም ሲያ​ልፍ ዕዉር ሆኖ የተ​ወ​ለ​ደ​ውን ሰው አየ።


Follow us:

Advertisements


Advertisements