Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




ዮሐንስ 9:1 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

1 ከዚ​ያም ሲያ​ልፍ ዕዉር ሆኖ የተ​ወ​ለ​ደ​ውን ሰው አየ።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

1 በመንገድ ሲያልፍም ከተወለደ ጀምሮ ዐይነ ስውር የሆነ ሰው አየ።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

1 ሲያልፍም ከመወለዱ ጀምሮ ዐይነ ስውር ሆኖ የተወለደውን ሰው አየ።

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

1 ኢየሱስ በመንገድ ሲያልፍ ዕውር ሆኖ የተወለደ ሰው አየ።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

1 ሲያልፍም ከመወለዱ ጀምሮ ዕውር የሆነውን ሰው አየ።

See the chapter Copy




ዮሐንስ 9:1
12 Cross References  

ሊደ​በ​ድ​ቡ​ትም ድን​ጋይ አነሡ፤ ጌታ​ችን ኢየ​ሱስ ግን ተሰ​ወ​ራ​ቸው፤ ከቤተ መቅ​ደ​ስም ወጣ፤ በመ​ካ​ከ​ላ​ቸ​ውም አልፎ ሄደ።


ደቀ መዛ​ሙ​ር​ቱም፥ “መም​ህር ሆይ፥ ይህ ሰው ዕዉር ሆኖ የተ​ወ​ለ​ደው በማን ኀጢ​ኣት ነው? በራሱ ነውን? ወይስ በወ​ላ​ጆቹ?” ብለው ጠየ​ቁት።


በዚ​ያን ጊዜም የዕ​ው​ሮች ዐይ​ኖ​ቻ​ቸው ይገ​ለ​ጣሉ፤ የደ​ን​ቆ​ሮ​ዎ​ችም ጆሮ​ዎች ይሰ​ማሉ።


ኢየሱስም ከዚያ ሲያልፍ ሁለት ዕውሮች “የዳዊት ልጅ ሆይ! ማረን፤” ብለው እየጮሁ ተከተሉት።


እነሆም፥ ሁለት ዕውሮች በመንገድ ዳር ተቀምጠው፥ ኢየሱስ እንዲያልፍ በሰሙ ጊዜ “ጌታ ሆይ! የዳዊት ልጅ፥ ማረን” ብለው ጮኹ።


አባቱንም “ይህ ከያዘው ስንት ዘመን ነው?” ብሎ ጠየቀው። እርሱም “ከሕፃንነቱ ጀምሮ ነው፤


ከዚ​ህም በኋላ ጌታ​ችን ኢየ​ሱስ ከእ​ርሱ ጋር ሲሄድ ሰዎች ያጨ​ና​ን​ቁት ነበር፤ ከዐ​ሥራ ሁለት ዓመ​ትም ጀምሮ ደም ይፈ​ስ​ሳት የነ​በ​ረች ሴት መጣች፤ ገን​ዘ​ብ​ዋ​ንም ሁሉ ለባ​ለ​መ​ድ​ኀ​ኒ​ቶች ሰጥታ ጨርሳ ነበር፤ ነገር ግን ሊያ​ድ​ናት የቻለ ማንም አል​ነ​በ​ረም።


በዚ​ያም ከታ​መመ ሠላሳ ስም​ንት ዓመት የሆ​ነው አንድ ሰው ነበር።


ይህ የድ​ኅ​ነት ምል​ክት ለተ​ደ​ረ​ገ​ለት ለዚያ ሰው ከአ​ርባ ዓመት ይበ​ል​ጠው ነበ​ረና።


በዚ​ያም ኤንያ የተ​ሰኘ ሰውን አገኘ፤ እር​ሱም ታሞ በአ​ልጋ ከተኛ ስም​ንት ዓመት ሆኖት ነበረ፤ ሽባ ነበ​ርና።


በል​ስ​ጥ​ራ​ንም እግሩ የሰ​ለለ፥ ከእ​ና​ቱም ማኅ​ፀን ጀምሮ ሽባ የሆነ፥ ከቶም ሂዶ የማ​ያ​ውቅ አንድ ሰው ተቀ​ምጦ ነበር።


አረ​ማ​ው​ያ​ንም እፉ​ኝቱ በጳ​ው​ሎስ እጅ ላይ ተን​ጠ​ል​ጥላ ባዩ ጊዜ እርስ በር​ሳ​ቸው፥ “ይህ ሰው ነፍሰ ገዳይ ይመ​ስ​ላል፤ ከባ​ሕር እንኳ በደ​ኅና ቢወ​ጣም በሕ​ይ​ወት ይኖር ዘንድ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፍርድ አል​ተ​ወ​ውም” አሉ።


Follow us:

Advertisements


Advertisements