Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




ዮሐንስ 8:40 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

40 አሁ​ንም በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዘንድ የሰ​ማ​ሁ​ትን እው​ነት የም​ነ​ግ​ራ​ች​ሁን ሰው ልት​ገ​ድ​ሉኝ ትሻ​ላ​ችሁ፤ አብ​ር​ሃ​ምስ እን​ዲህ አላ​ደ​ረ​ገም።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

40 ከእግዚአብሔር ሰምቼ እውነቱን የነገርኋችሁን እኔን ለመግደል ቈርጣችሁ ተነሥታችኋል፤ አብርሃም ግን እንዲህ አላደረገም።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

40 ነገር ግን አሁን ከእግዚአብሔር የሰማሁትን እውነት የምነገራችሁን እኔን ልትገድሉኝ ትፈልጋላችሁ፤ አብርሃም እንዲህ አላደረገም።

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

40 እኔ ከእግዚአብሔር የሰማሁትን እውነት ነገርኳችሁ፤ እናንተ ግን ልትገድሉኝ ትፈልጋላችሁ፤ አብርሃም እንዲህ አላደረገም።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

40 ነገር ግን አሁን ከእግዚእብሔር የሰማሁትን እውነት የነገርኋችሁን ሰው ልትገድሉኝ ትፈልጋላችሁ፤ አብርሃም እንዲህ አላደረገም።

See the chapter Copy




ዮሐንስ 8:40
13 Cross References  

ስለ እና​ንተ የም​ና​ገ​ረ​ውና የም​ፈ​ር​ደው ብዙ አለኝ፤ የላ​ከ​ኝም እው​ነ​ተኛ ነው፤ እኔ በእ​ርሱ ዘንድ የሰ​ማ​ሁ​ትን ለዓ​ለም እና​ገ​ራ​ለሁ።”


ነገር ግን በሥጋ ልማድ የተ​ወ​ለ​ደው በመ​ን​ፈ​ሳዊ ግብር የተ​ወ​ለ​ደ​ውን በዚያ ጊዜ እን​ዳ​ሳ​ደ​ደው ዛሬም እን​ዲሁ ነው።


እው​ነ​ቱን ስለ ነገ​ር​ኋ​ችሁ ባላ​ጋራ ሆን​ኋ​ች​ሁን?


ዘንዶውም በሴቲቱ ላይ ተቈጥቶ የእግዚአብሔርን ትእዛዛት የሚጠብቁትን የኢየሱስም ምስክር ያላቸውን ከዘርዋ የቀሩትን ሊዋጋ ሄደ፤


ጅራቱም የሰማይን ከዋክብት ሲሶ እየሳበ ወደ ምድር ጣላቸው። ዘንዶውም ሴቲቱ በወለደች ጊዜ ሕፃንዋን እንዲበላ ልትወልድ ባላት ሴት ፊት ቆመ።


ለተ​ገ​ዘ​ሩ​ትም አባት ይሆን ዘንድ ነው፤ ነገር ግን ለተ​ገ​ዘ​ሩት ብቻ አይ​ደ​ለም፤ እርሱ አባ​ታ​ችን አብ​ር​ሃም ሳይ​ገ​ዘር እንደ አመነ ሳይ​ገ​ዘሩ የአ​ባ​ታ​ችን የአ​ብ​ር​ሃ​ምን የሃ​ይ​ማ​ኖ​ቱን ፍለጋ ለሚ​ከ​ተሉ ደግሞ ነው እንጂ።


አባ​ታ​ችሁ አብ​ር​ሃም የእ​ኔን ቀን ያይ ዘንድ ተመኘ፤ አይ​ቶም ደስ አለው።”


ነፍ​ሴ​ንም የሚ​ሹ​አት በረ​ቱ​ብኝ፥ መከ​ራ​ዬ​ንም የሚ​ፈ​ልጉ ከን​ቱን ተና​ገሩ፥ ሁል​ጊ​ዜም ያጠ​ፉኝ ዘንድ በሽ​ን​ገላ ይመ​ክ​ራሉ።


ከዚህ በኋ​ላም ጌታ​ችን ኢየ​ሱስ በገ​ሊላ ይመ​ላ​ለስ ነበረ፤ ወደ ይሁዳ ምድ​ርም ሊሄድ አል​ወ​ደ​ደም፤ አይ​ሁድ ሊገ​ድ​ሉት ይሹ ነበ​ርና።


Follow us:

Advertisements


Advertisements