Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




ዮሐንስ 8:38 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

38 እኔ በአ​ባቴ ዘንድ ያየ​ሁ​ትን እና​ገ​ራ​ለሁ፤ እና​ን​ተም በአ​ባ​ታ​ችሁ ያያ​ች​ሁ​ትን ታደ​ር​ጋ​ላ​ችሁ።”

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

38 እኔ በአባቴ ዘንድ ያየሁትን እናገራለሁ፤ እናንተም ከአባታችሁ የሰማችሁትን ታደርጋላችሁ።”

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

38 እኔ በአባቴ ዘንድ ያየሁትን እናገራለሁ፤ እናንተም ደግሞ ከአባታችሁ የሰማችሁትን ታደርጋላችሁ።”

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

38 እኔ ከአባቴ ዘንድ ያየሁትን እናገራለሁ፤ እናንተ ግን ከአባታችሁ የሰማችሁትን ታደርጋላችሁ።”

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

38 እኔ በአባቴ ዘንድ ያየሁትን እናገራለሁ፤ እናንተም ደግሞ በአባታችሁ ዘንድ ያያችሁትን ታደርጋላችሁ።”

See the chapter Copy




ዮሐንስ 8:38
12 Cross References  

ከዚ​ህም በኋላ ጌታ​ችን ኢየ​ሱስ መልሶ እን​ዲህ አላ​ቸው፥ “እው​ነት እው​ነት እላ​ች​ኋ​ለሁ፤ ወልድ ከራሱ ብቻ ምንም ሊያ​ደ​ርግ አይ​ች​ልም፤ አብ ሲያ​ደ​ርግ ያየ​ውን ነው እንጂ፤ ወል​ድም አብ የሚ​ሠ​ራ​ውን ያንኑ እን​ዲሁ ይሠ​ራል።


እና​ን​ተስ ከአ​ባ​ታ​ችሁ ከሰ​ይ​ጣን ናችሁ፤ የአ​ባ​ታ​ች​ሁ​ንም ፈቃድ ልታ​ደ​ርጉ ትወ​ዳ​ላ​ችሁ፤ እርሱ ከጥ​ንት ጀምሮ ነፍሰ ገዳይ ነው፤ በእ​ው​ነ​ትም አይ​ቆ​ምም፤ በእ​ርሱ ዘንድ እው​ነት የለ​ምና፤ ሐሰ​ት​ንም በሚ​ና​ገ​ር​በት ጊዜ ከራሱ አን​ቅቶ ይና​ገ​ራል፤ ሐሰ​ተኛ ነውና፤ የሐ​ሰ​ትም አባት ነውና።


እና​ንተ ግን የአ​ባ​ታ​ች​ሁን ሥራ ትሠ​ራ​ላ​ችሁ።” እነ​ር​ሱም፥ “እኛ ከዝ​ሙት አል​ተ​ወ​ለ​ድ​ንም፤ ነገር ግን አንድ አባት አለን፤ እር​ሱም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ነው” አሉት።


እኔ ከራሴ አን​ዳች አደ​ርግ ዘንድ አል​ች​ልም፤ እንደ ሰማሁ እፈ​ር​ዳ​ለሁ እንጂ፤ ፍር​ዴም እው​ነት ነው፤ የላ​ከ​ኝን ፈቃድ እንጂ የእ​ኔን ፈቃድ አል​ሻ​ምና።


የማ​ይ​ወ​ደኝ ግን ቃሌን አይ​ጠ​ብ​ቅም፤ ይህም የም​ት​ሰ​ሙት ቃል የላ​ከኝ የአብ ቃል ነው እንጂ የእኔ ቃል አይ​ደ​ለም።


እኔ በአብ እን​ዳ​ለሁ አብም በእኔ እን​ዳለ አታ​ም​ን​ምን? እኔ የም​ነ​ግ​ራ​ችሁ ይህ ቃልም ከራሴ የተ​ና​ገ​ር​ሁት አይ​ደ​ለም፤ በእኔ ያለ አብ እርሱ ይህን ሥራ ይሠ​ራ​ዋል እንጂ።


ስለ እና​ንተ የም​ና​ገ​ረ​ውና የም​ፈ​ር​ደው ብዙ አለኝ፤ የላ​ከ​ኝም እው​ነ​ተኛ ነው፤ እኔ በእ​ርሱ ዘንድ የሰ​ማ​ሁ​ትን ለዓ​ለም እና​ገ​ራ​ለሁ።”


ባየ​ውና በሰ​ማው ይመ​ሰ​ክ​ራል፤ ነገር ግን ምስ​ክ​ር​ነ​ቱን የሚ​ቀ​በ​ለው የለም።


የሰ​ጠ​ኽ​ኝን ቃል ሰጥ​ቻ​ቸ​ዋ​ለ​ሁና፤ እነ​ር​ሱም ተቀ​ብ​ለው ከአ​ንተ እንደ ወጣሁ በእ​ው​ነት ዐወቁ፤ አን​ተም እንደ ላክ​ኸኝ አመኑ።


ዳሩ ግን ከፈሪሳውያንና ከሰዱቃውያን ብዙዎች ወደ ጥምቀቱ ሲመጡ ባየ ጊዜ፥ እንዲህ አላቸው “እናንተ የእፉኝት ልጆች፥ ከሚመጣው ቍጣ እንድትሸሹ ማን አመለከታችሁ?


Follow us:

Advertisements


Advertisements