Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




ዮሐንስ 8:18 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

18 እኔ ስለ ራሴ ምስ​ክር ነኝ፤ የላ​ከኝ አብም ይመ​ሰ​ክ​ር​ል​ኛል።”

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

18 ስለ ራሴ የምመሰክር አንዱ እኔ ነኝ፤ ሌላውም ምስክሬ የላከኝ አብ ነው።”

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

18 ስለ እራሴ የምመሰክረው እኔ ነኝ፤ የላከኝም አብ ስለ እኔ ይመሰክራል።”

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

18 ስለዚህ እኔ ስለ ራሴ እመሰክራለሁ፤ የላከኝ አብም ስለ እኔ ይመሰክራል።”

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

18 ስለ ራሴ የምመሰክር እኔ ነኝ፥ የላከኝም አብ ስለ እኔ ይመሰክራል።”

See the chapter Copy




ዮሐንስ 8:18
16 Cross References  

ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም፥ “እው​ነት እው​ነት እላ​ች​ኋ​ለሁ፤ አብ​ር​ሃም ሳይ​ወ​ለድ እኔ አለሁ።” አላ​ቸው።


እኔ በአ​ባቴ ዘንድ ያየ​ሁ​ትን እና​ገ​ራ​ለሁ፤ እና​ን​ተም በአ​ባ​ታ​ችሁ ያያ​ች​ሁ​ትን ታደ​ር​ጋ​ላ​ችሁ።”


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም እንደ ራሱ ፈቃድ የመ​ን​ፈስ ቅዱ​ስን ጸጋ በመ​ስ​ጠት፥ በም​ል​ክ​ትና በድ​ንቅ ነገር፥ በልዩ ልዩ ተአ​ም​ራ​ትም መሰ​ከ​ረ​ላ​ቸው፤ ነገ​ራ​ቸ​ው​ንም አስ​ረ​ዳ​ላ​ቸው።


ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም እን​ዲህ አለው፥ “የእ​ው​ነ​ትና የሕ​ይ​ወት መን​ገድ እኔ ነኝ፤ በእኔ በኩል ካል​ሆነ በቀር ወደ አብ የሚ​መጣ የለም።


ቸር ጠባቂ እኔ ነኝ፤ የእኔ የሆ​ኑ​ትን መን​ጋ​ዎ​ችን አው​ቃ​ለሁ፤ የእኔ የሆ​ኑ​ትም ያው​ቁ​ኛል።


“ቸር ጠባቂ እኔ ነኝ፤ ቸር ጠባቂ ስለ በጎቹ ነፍ​ሱን ይሰ​ጣል።


እው​ነ​ተ​ኛዉ የበ​ጎች በር እኔ ነኝ፤ በእኔ በኩ​ልም የሚ​ገባ ይድ​ናል፤ ይገ​ባ​ልም ይወ​ጣ​ልም፤ መሰ​ማ​ር​ያም ያገ​ኛል።


እው​ነት እው​ነት እላ​ች​ኋ​ለሁ፤ ቃሌን የሚ​ጠ​ብቅ ለዘ​ለ​ዓ​ለም ሞትን አይ​ቀ​ም​ስም።”


እነ​ር​ሱም፥ “አንተ ማነህ?” አሉት፤ ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም እን​ዲህ አላ​ቸው፥ “በመ​ጀ​መ​ሪያ ነግ​ሬ​አ​ች​ኋ​ለሁ።


ዳግ​መ​ኛም ጌታ​ችን ኢየ​ሱስ፥ “የዓ​ለም ብር​ሃን እኔ ነኝ፤ የሚ​ከ​ተ​ለኝ የሕ​ይ​ወት ብር​ሃ​ንን ያገ​ኛል እንጂ በጨ​ለማ ውስጥ አይ​መ​ላ​ለ​ስም” ብሎ ተና​ገ​ራ​ቸው።


እኔና አብ አንድ ነን።”


ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም አላት፥ “ትን​ሣ​ኤና ሕይ​ወት እኔ ነኝ፤ የሚ​ያ​ም​ን​ብኝ ቢሞ​ትም ይነ​ሣል።


ነፍሰ ገዳይ ሁሉ በም​ስ​ክ​ሮች ቃል ይገ​ደ​ላል፤ በአ​ንድ ምስ​ክር ግን ማና​ቸ​ው​ንም ሰው መግ​ደል አይ​ገ​ባም።


Follow us:

Advertisements


Advertisements