Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




ዮሐንስ 7:32 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

32 ፈሪ​ሳ​ው​ያ​ንም ሕዝቡ በእ​ርሱ ምክ​ን​ያት እንደ አጕ​ረ​መ​ረሙ ሰሙ፤ የካ​ህ​ናት አለ​ቆ​ችና ፈሪ​ሳ​ው​ያ​ንም ይይ​ዙት ዘንድ ሎሌ​ዎ​ቻ​ቸ​ውን ላኩ።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

32 ፈሪሳውያን፣ ሕዝቡ ስለ እርሱ በጕምጕምታ የሚነጋገረውን ነገር ሰሙ፤ የካህናት አለቆችና ፈሪሳውያንም እንዲይዙት የቤተ መቅደስ ጠባቂዎችን ላኳቸው።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

32 ፈሪሳውያን ሕዝቡ ስለ እርሱ እንደዚህ ሲያንጐራጉሩ ሰሙ፤ የካህናት አለቆችና ፈሪሳውያንም ሊይዙት ዘቦችን ላኩ።

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

32 ሰዎቹ ስለ ኢየሱስ በሹክሹክታ ሲነጋገሩ ፈሪሳውያን ሰሙ፤ ስለዚህ የካህናት አለቆችና ፈሪሳውያን ኢየሱስን ለማስያዝ የቤተ መቅደስ ዘብ ጠባቂዎችን ላኩ።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

32 ፈሪሳውያን ሕዝቡ ሰለ እርሱ እንደዚህ ሲያንጐራጕሩ ሰሙ፤ የካህናት አለቆችም ፈሪሳውያም ሊይዙት ሎሌዎችን ላኩ።

See the chapter Copy




ዮሐንስ 7:32
13 Cross References  

ከዚ​ህም በኋላ የቤተ መቅ​ደሱ ሹም ከሎ​ሌ​ዎቹ ጋር ሔዶ አባ​ብሎ አመ​ጣ​ቸው፤ በግ​ድም አይ​ደ​ለም፤ በድ​ን​ጋይ እን​ዳ​ይ​ደ​በ​ድ​ቧ​ቸው ሕዝ​ቡን ይፈሩ ነበ​ርና።


ይሁ​ዳም ከካ​ህ​ናት አለ​ቆ​ችና ከፈ​ሪ​ሳ​ው​ያን ወታ​ደ​ሮ​ችን ተቀ​በለ፤ ሎሌ​ዎ​ቻ​ቸ​ው​ንም በረ​ዳ​ት​ነት ወሰደ፤ ፋኖ​ስና የችቦ መብ​ራት፥ የጦር መሣ​ሪ​ያም ይዞ ወደ​ዚያ ሄደ።


ፈሪ​ሳ​ው​ያ​ንም እርስ በር​ሳ​ቸው፥ “የም​ታ​ገ​ኙት ምንም ጥቅም እን​ደ​ሌለ ታያ​ላ​ች​ሁን? እነሆ፥ ዓለም ሁሉ ተከ​ት​ሎ​ታል” ተባ​ባሉ።


“እናንተ ግብዞች ጻፎችና ፈሪሳውያን! መንግሥተ ሰማያትን በሰው ፊት ስለምትዘጉ ወዮላችሁ፤ እናንተ አትገቡም፤ የሚገቡትንም እንዳይገቡ ትከለክላላችሁ።


ሳኦ​ልም ዳዊ​ትን ያመ​ጡት ዘንድ መል​እ​ክ​ተ​ኞ​ችን ላከ፤ የነ​ቢ​ያ​ት​ንም ጉባኤ አገኙ፤ ሳሙ​ኤ​ልም አለ​ቃ​ቸው ሆኖ በመ​ካ​ከ​ላ​ቸው ቆሞ ነበረ፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም መን​ፈስ በሳ​ኦል መል​እ​ክ​ተ​ኞች ላይ ወረደ፤ እነ​ር​ሱም ትን​ቢት ይና​ገሩ ጀመር።


ፈሪሳውያን ግን ወጥተው እንዴት አድርገው እንዲያጠፉት ተማከሩበት።


ጴጥሮስ ግን እስከ ሊቀ ካህናቱ ግቢ ድረስ ሩቅ ሆኖ ተከተለው፤ የነገሩንም ፍጻሜ ያይ ዘንድ ወደ ውስጥ ገብቶ ከሎሌዎቹ ጋር ተቀመጠ።


ስለ​ዚ​ህም ሊይ​ዙት ወደው ነበር፤ ነገር ግን እጁን በእ​ርሱ ላይ ያነሣ የለም፤ ጊዜዉ ገና አል​ደ​ረ​ሰም ነበ​ርና።


ከእ​ነ​ር​ሱም መካ​ከል ወደ ፈሪ​ሳ​ው​ያን ሄደው የከ​ሰ​ሱት ነበሩ፤ ጌታ​ችን ኢየ​ሱስ ያደ​ረ​ገ​ው​ንም ሁሉ ነገ​ሩ​አ​ቸው።


Follow us:

Advertisements


Advertisements