Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




ዮሐንስ 7:14 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

14 በበ​ዓሉ ቀኖች እኩ​ሌ​ታም ጌታ​ችን ኢየ​ሱስ ወደ መቅ​ደስ ወጥቶ ያስ​ተ​ምር ጀመረ።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

14 በበዓሉም አጋማሽ ኢየሱስ ወደ ቤተ መቅደስ ወጥቶ ያስተምር ጀመር።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

14 በበዓሉ እኩሌታ ኢየሱስ ወደ መቅደስ ወጥቶ ያስተምር ነበር።

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

14 በበዓሉም አጋማሽ ላይ ኢየሱስ ወደ ቤተ መቅደስ ሄዶ ያስተምር ጀመር።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

14 አሁንም በበዓሉ እኩሌታ ኢየሱስ ወደ መቅደስ ወጥቶ ያስተምር ነበር።

See the chapter Copy




ዮሐንስ 7:14
16 Cross References  

ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም በመ​ቅ​ደስ ሲያ​ስ​ተ​ምር ቃሉን ከፍ አድ​ርጎ እን​ዲህ አለ፥ “እኔን ታው​ቁ​ኛ​ላ​ችሁ፤ ከወ​ዴ​ትም እንደ ሆንሁ ታው​ቃ​ላ​ችሁ፤ እኔ ራሴ የመ​ጣሁ አይ​ደ​ለ​ሁም፤ ነገር ግን እና​ንተ የማ​ታ​ው​ቁት የላ​ከኝ እው​ነ​ተኛ አለ።


ዘወ​ት​ርም በመ​ቅ​ደስ ያስ​ተ​ምር ነበር፤ የካ​ህ​ናት አለ​ቆች፥ ጻፎ​ችና የሕ​ዝብ ታላ​ላ​ቆ​ችም ሊገ​ድ​ሉት ይሹ ነበር።


ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም መልሶ እን​ዲህ አለው፥ “እኔ ለዓ​ለም በግ​ልጥ ተና​ገ​ርሁ፤ አይ​ሁድ ሁሉ በሚ​ሰ​በ​ሰ​ቡ​በት በም​ኵ​ራ​ብም፥ በቤተ መቅ​ደ​ስም ሁል​ጊዜ አስ​ተ​ማ​ርሁ፤ በስ​ው​ርም የተ​ና​ገ​ር​ሁት አን​ዳች ነገር የለም።


በጥ​ዋ​ትም ገስ​ግሦ ዳግ​መኛ ወደ ቤተ መቅ​ደስ ገባ፤ ሕዝ​ቡም ሁሉ ወደ እርሱ ተሰ​በ​ሰቡ፤ እር​ሱም ተቀ​ምጦ ያስ​ተ​ም​ራ​ቸው ጀመር።


በኋ​ለ​ኛ​ዪቱ በታ​ላ​ቅዋ የበ​ዓል ቀንም ጌታ​ችን ኢየ​ሱስ ቆመና ድም​ፁን ከፍ አድ​ርጎ እን​ዲህ አለ፥ “የተ​ጠማ ወደ እኔ ይም​ጣና ይጠጣ።


የአ​ይ​ሁ​ድም የዳስ በዓ​ላ​ቸው ደርሶ ነበር።


ከዚ​ህም በኋላ ጌታ​ችን ኢየ​ሱስ ያን የዳ​ነ​ውን ሰው በቤተ መቅ​ደስ አገ​ኘ​ውና፥ “እነሆ፥ ድነ​ሃል፤ ግን ከዚህ የባሰ እን​ዳ​ያ​ገ​ኝህ ዳግ​መኛ እን​ዳ​ት​በ​ድል ተጠ​ን​ቀቅ” አለው።


በዚያን ሰዓት ኢየሱስ ለሕዝቡ “ወንበዴን እንደምትይዙ ሰይፍና ጐመድ ይዛችሁ ልትይዙኝ ወጣችሁን? በመቅደስ ዕለት ዕለት እያስተማርሁ ከእናንተ ጋር ስቀመጥ ሳለሁ አልያዛችሁኝም።


ኢየሱስም ወደ መቅደስ ገባና በመቅደስ የሚሸጡትንና የሚገዙትን ሁሉ አስወጣ፤ የገንዘብ ለዋጮችንም ገበታዎች የርግብ ሻጮችንም ወንበሮች ገለበጠና


እነሆ፥ መልእክተኛዬን እልካለሁ፥ መንገድንም በፊቴ ያስተካክላል፣ እናንተም የምትፈልጉት ጌታ በድንገት ወደ መቅደሱ ይመጣል፣ የምትወዱትም የቃል ኪዳን መልእክተኛ፥ እነሆ፥ ይመጣል፥ ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር።


“በሁ​ለ​ተ​ኛ​ውም ቀን ዐሥራ ሁለት በሬ​ዎ​ችን፥ ሁለት አውራ በጎ​ችን፥ ነውር የሌ​ለ​ባ​ቸ​ውን ዐሥራ አራት የአ​ንድ ዓመት ተባት የበግ ጠቦ​ቶ​ችን፥


“በሦ​ስ​ተ​ኛ​ውም ቀን ዐሥራ አንድ በሬ​ዎች፥ ሁለት አውራ በጎች፥ ነውር የሌ​ለ​ባ​ቸ​ውን ዐሥራ አራት የአ​ንድ ዓመት ተባት የበግ ጠቦ​ቶች፥


ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም በቤተ መቅ​ደስ ሲያ​ስ​ተ​ም​ራ​ቸው በሙ​ዳየ ምጽ​ዋት አጠ​ገብ ይህን ተና​ገ​ራ​ቸው፤ ነገር ግን አል​ያ​ዙ​ትም፤ ጊዜው ገና አል​ደ​ረ​ሰም ነበ​ርና።


Follow us:

Advertisements


Advertisements