Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




ዮሐንስ 6:9 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

9 “አም​ስት የገ​ብስ እን​ጀ​ራና ሁለት ዓሣ የያዘ ብላ​ቴና በዚህ አለ፤ ነገር ግን እነ​ዚህ ይህን ለሚ​ያ​ህል ሰው ምን ይበ​ቃሉ?”

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

9 “ዐምስት ትንንሽ የገብስ እንጀራና ሁለት ትንንሽ ዓሣ የያዘ አንድ ልጅ እዚህ አለ፤ ይህ ግን ለዚህ ሁሉ ሕዝብ እንዴት ይዳረሳል?”

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

9 “አምስት የገብስ እንጀራና ሁለት ዓሣ የያዘ ብላቴና በዚህ አለ፤ ነገር ግን ለዚህ ሁሉ ሰው ምን ይሆናል?”

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

9 “አምስት የገብስ እንጀራና ሁለት ዓሣ የያዘ አንድ ልጅ እዚህ አለ፤ ነገር ግን ይህ ለዚህ ሁሉ ሕዝብ ምን ይበቃል?”

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

9 አምስት የገብስ እንጀራና ሁለት ዓሣ የያዘ ብላቴና በዚህ አለ፤ ነገር ግን እነዚህን ለሚያህሉ ሰዎች ይህ ምን ይሆናል? አለው።

See the chapter Copy




ዮሐንስ 6:9
24 Cross References  

እርሱ ግን፥ “እና​ንተ የሚ​በ​ሉ​ትን ስጡ​አ​ቸው” አላ​ቸው፤ እነ​ር​ሱም፥ “ለዚህ ሁሉ ሕዝብ የሚ​በቃ ምግብ ልን​ገዛ ካል​ሄ​ድን ከአ​ም​ስት እን​ጀ​ራና ከሁ​ለት ዓሣ በቀር ሌላ በዚህ የለ​ንም” አሉት።


እርሱም “ስንት እንጀራ አላችሁ? ሂዱና እዩ፤” አላቸው። ባወቁም ጊዜ “አምስት፥ ሁለትም ዓሣ፤” አሉት።


እነርሱም “ከአምስት እንጀራና ከሁለት ዓሣ በቀር በዚህ የለንም፤” አሉት።


ለአምስቱ ሺህ አምስቱ እንጀራ፥ ስንት መሶብም እንዳነሣችሁ ትዝ አይላችሁምን?


አምስቱን እንጀራ ለአምስት ሺህ በቈረስሁ ጊዜ፥ ቍርስራሹ የሞላ ስንት መሶብ አነሣችሁ” እነርሱም “ዐሥራ ሁለት፤” አሉት።


የጌ​ታ​ችን የኢ​የ​ሱስ ክር​ስ​ቶ​ስን ቸር​ነ​ቱን ታው​ቃ​ላ​ችሁ፤ በእ​ርሱ ድህ​ነት እና​ንተ ባለ​ጸ​ጎች ትሆኑ ዘንድ እርሱ ባለ​ጸጋ ሲሆን፥ ስለ እና​ንተ ራሱን ድሃ አደ​ረገ።


ስንዴ፥ ገብ​ስም፥ ወይ​ንም፥ በለ​ስም፥ ሮማ​ንም ወደ ሞሉ​ባት፥ ወይ​ራም፥ ቅቤም፥ ማርም ወደ ሞሉ​ባት ምድር፥


በአራቱም እንስሶች መካከል ድምፅ “አንድ እርቦ ስንዴ በዲናር ሦስት እርቦ ገብስም በዲናር፥ ዘይትንና ወይንንም አትጕዳ” ሲል ሰማሁ።


ማር​ያ​ምም ጌታ​ችን ኢየ​ሱስ ወደ አለ​በት ስፍራ ደረ​ሰ​ችና በአ​የ​ችው ጊዜ ከእ​ግሩ በታች ሰግዳ፥ “ጌታዬ ሆይ፥ በዚህ ኑረህ ቢሆን ወን​ድሜ ባል​ሞ​ተም ነበር” አለ​ችው።


ማር​ታም ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስን እን​ዲህ አለ​ችው፥ “ጌታዬ ሆይ፥ በዚህ ኖረህ ቢሆን ወን​ድሜ ባል​ሞ​ተም ነበር።


ፊል​ጶ​ስም መልሶ እን​ዲህ አለው፥ “ከእ​ነ​ርሱ ለእ​ያ​ን​ዳ​ንዱ ጥቂት ጥቂት ይወ​ስዱ ዘንድ የሁ​ለት መቶ ዲናር እን​ጀራ አይ​በ​ቃ​ቸ​ውም።”


ይሁ​ዳና እስ​ራ​ኤል ነጋ​ዴ​ዎ​ችሽ ነበሩ፤ ስን​ዴ​ንም ይሸ​ም​ቱ​ልሽ ነበር፤ ሰሊ​ሆ​ት​ንና በለ​ሶ​ንን፥ ዘይ​ት​ንና የተ​ወ​ደደ ማርን፥ ርጢ​ን​ንም ከአ​ንቺ ጋር አንድ ይሆኑ ዘንድ ሰጡሽ።


ኤል​ሳ​ዕም፥ “የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቃል ስማ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ ነገ በዚህ ጊዜ በሰ​ማ​ርያ በር፥ ሁለት መስ​ፈ​ሪያ ገብስ በአ​ንድ ሰቅል አንድ መስ​ፈ​ሪያ መል​ካም ዱቄ​ትም በአ​ንድ ሰቅል ይሸ​መ​ታል” አለው።


እያ​ን​ዳ​ን​ዱም እንደ ደንቡ የን​ጉ​ሡን ሰረ​ገ​ላ​ዎች ለሚ​ስቡ ለፈ​ረ​ሶ​ችና ለሰ​ጋር በቅ​ሎ​ዎች ገብ​ስና ገለባ፥ እን​ዲ​ሁም ዕቃ​ዎ​ችን ወደ ስፍ​ራ​ቸው ያመጡ ነበር።


በላሙ ቅቤ፥ በበ​ጉም ወተት፥ ከፍ​የል ጠቦ​ትና ከላም፥ ከጊ​ደ​ሮ​ችና ከበ​ጎች ስብ ጋር፥ ከፍ​ትግ ስንዴ ጋር መገ​ባ​ቸው፤ የዘ​ለ​ላ​ው​ንም ደም የወ​ይን ጠጅ አድ​ር​ገው ጠጡ።


ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም ያን እን​ጀራ ይዞ አመ​ሰ​ገነ፤ ቈር​ሶም ለደቀ መዛ​ሙ​ርቱ ሰጣ​ቸው፤ ደቀ መዛ​ሙ​ር​ቱም ለተ​ቀ​መ​ጡት ሰዎች ሰጡ​አ​ቸው፤ ከዓ​ሣ​ውም እን​ዲሁ የፈ​ለ​ጉ​ትን ያህል ሰጡ​አ​ቸው።


ወደ ምድ​ርም በወ​ረዱ ጊዜ ፍሙ መርቶ፥ ዓሣም በላዩ ሆኖ፥ እን​ጀ​ራም ተሠ​ርቶ አገኙ።


ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም፥ “አሁን ከያ​ዛ​ች​ኋ​ቸው ዓሣ​ዎች አምጡ” አላ​ቸው።


ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም መጣና ኅብ​ስ​ቱን አን​ሥቶ ሰጣ​ቸው፤ ከዓ​ሣ​ውም እን​ዲሁ።


Follow us:

Advertisements


Advertisements