Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




ዮሐንስ 6:71 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

71 ይህ​ንም ስለ ስም​ዖን ልጅ ስለ አስ​ቆ​ሮ​ታ​ዊው ይሁዳ ተና​ገረ፤ እርሱ ያሲ​ዘው ዘንድ አለ​ውና፤ እር​ሱም ከዐ​ሥራ ሁለቱ አንዱ ነበር።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

71 የአስቆሮቱ የስምዖን ልጅ ይሁዳ፣ ከዐሥራ ሁለቱ አንዱ ቢሆንም፣ ኋላ አሳልፎ ስለሚሰጠው ስለ እርሱ መናገሩ ነበር።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

71 ስለ ስምዖን ልጅ ስለ አስቆሮቱ ይሁዳ መናገሩ ነበር፤ ከዐሥራ ሁለቱ አንዱ ሲሆን፥ አሳልፎም የሚሰጠው እርሱ ነበርና ነው።

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

71 ይህንንም ያለው ስለ ስምዖን ልጅ ስለ አስቆሮታዊው ይሁዳ ነበር፤ ይሁዳ ምንም እንኳ ከዐሥራ ሁለቱ አንዱ ቢሆን ኢየሱስን አሳልፎ የሚሰጥ እርሱ ስለ ነበር ነው።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

71 ስለ ስምዖንም ልጅ ስለ አስቆሮቱ ይሁዳ ተናገረ፤ ከአሥራ ሁለቱ አንዱ የሆነ እርሱ አሳልፎ ይሰጠው ዘንድ አለውና።

See the chapter Copy




ዮሐንስ 6:71
19 Cross References  

ከብዙ ጊዜ በፊት ለዚህ ፍርድ የተጻፉ አንዳንዶች ሰዎች ሾልከው ገብተዋልና፤ ኀጢአተኞች ሆነው የአምላካችንን ጸጋ በሴሰኝነት ይለውጣሉ፤ ብቻውን ንጉሣችንንና ጌታችንንም የሆነውን ኢየሱስ ክርስቶስን ይክዳሉ።


እር​ሱ​ንም በተ​ወ​ሰ​ነው በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ምክ​ርና በቀ​ደ​መው ዕው​ቀቱ እና​ንተ አሳ​ል​ፋ​ችሁ በኃ​ጥ​ኣን እጅ ሰጣ​ች​ሁት፤ ሰቅ​ላ​ች​ሁም ገደ​ላ​ች​ሁት።


ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም መልሶ፥ “ይህ እኔ እን​ጀራ በወጥ አጥ​ቅሼ የም​ሰ​ጠው ነው” አለው፤ ያን ጊዜም እን​ጀራ በወጥ አጥ​ቅሶ ለስ​ም​ዖን ልጅ ለአ​ስ​ቆ​ሮ​ታ​ዊው ይሁዳ ሰጠው።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን አል​ሁት፥ “አንተ አም​ላኬ ነህ፤ ለምን ረሳ​ኸኝ? ጠላ​ቶቼ ሲያ​ስ​ጨ​ን​ቁኝ ለምን ተው​ኸኝ? ለም​ንስ አዝኜ እመ​ለ​ሳ​ለሁ?” ጠላ​ቶቼ ሁሉ አጥ​ን​ቶ​ቼን እየ​ቀ​ለ​ጣ​ጠሙ ሰደ​ቡኝ።


የዐሥራ ሁለቱም ሐዋርያት ስም ይህ ነው፤ መጀመሪያው ጴጥሮስ የተባለው ስምዖን ወንድሙ እንድርያስም፥ የዘብዴዎስ ልጅ ያዕቆብም ወንድሙ ዮሐንስም፥


ቀነናዊውም ስምዖን ደግሞም አሳልፎ የሰጠው የአስቆሮቱ ይሁዳ።


ከዐሥራ ሁለቱም አንዱ የአስቆሮቱ ይሁዳ አሳልፎ ሊሰጠው ወደ ካህናት አለቆች ሄደ።


ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስና ደቀ መዛ​ሙ​ር​ቱም ወደ ሰርጉ ታደሙ።


ነገር ግን ከእ​ና​ንተ ውስጥ የማ​ያ​ምኑ አሉ፤” ጌታ​ችን ኢየ​ሱስ ከጥ​ንት ጀምሮ የማ​ያ​ም​ኑ​በት እነ​ማን እንደ ሆኑ፥ የሚ​ያ​ሲ​ዘ​ውም ማን እንደ ሆነ ያውቅ ነበ​ርና።


ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም መልሶ እን​ዲህ አላ​ቸው፥ “እኔ እና​ን​ተን ዐሥራ ሁለ​ታ​ች​ሁን መር​ጫ​ችሁ የለ​ምን? ነገር ግን ከእ​ና​ንተ አንዱ ሰይ​ጣን ነው።”


ከደቀ መዛ​ሙ​ርቱ አንዱ የነ​በረ ያሲ​ዘው ዘንድ ያለው የስ​ም​ዖን ልጅ አስ​ቆ​ሮ​ታ​ዊው ይሁዳ ግን እን​ዲህ አለ።


ራት ሲበ​ሉም አሳ​ልፎ ይሰ​ጠው ዘንድ በስ​ም​ዖን ልጅ በአ​ስ​ቆ​ሮቱ ሰው በይ​ሁዳ ልብ ሰይ​ጣን አደረ።


ጌታ​ችን ኢየ​ሱስ በመጣ ጊዜ ዲዲ​ሞስ የሚ​ሉት ከዐ​ሥራ ሁለቱ ደቀ መዛ​ሙ​ርት አንዱ ቶማስ ከደቀ መዛ​ሙ​ርቱ ጋር አል​ነ​በ​ረም።


Follow us:

Advertisements


Advertisements