Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




ዮሐንስ 6:60 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

60 ከደቀ መዛ​ሙ​ር​ቱም ብዙ​ዎቹ ይህን ሰም​ተው፥ “ይህ ነገር የሚ​ያ​ስ​ጨ​ንቅ ነው፤ ማንስ ሊሰ​ማው ይች​ላል?” አሉ።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

60 ከደቀ መዛሙርቱ ብዙዎች ይህን ሲሰሙ፣ “ይህ የሚያስጨንቅ ቃል ነው፤ ማንስ ሊቀበለው ይችላል?” አሉ።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

60 ከደቀ መዛሙርቱም ብዙዎቹ በሰሙ ጊዜ “ይህ ንግግር ከባድ ነው፤ ማን ሊሰማው ይችላል?” አሉ።

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

60 ከደቀ መዛሙርቱ ብዙዎቹ ይህን በሰሙ ጊዜ፥ “ይህ አነጋገር ከባድ ነው፤ ማን ሊቀበለው ይችላል?” አሉ።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

60 ከደቀ መዛሙርቱም ብዙዎች በሰሙ ጊዜ፦ ይህ የሚያስጨንቅ ንግግር ነው፤

See the chapter Copy




ዮሐንስ 6:60
12 Cross References  

ስለ​ዚ​ህም ከደቀ መዛ​ሙ​ርቱ ወደ ኋላ​ቸው የተ​መ​ለሱ ብዙ​ዎች ናቸው፤ ከዚ​ያም ወዲህ አብ​ረ​ውት አል​ሄ​ዱም።


እን​ግ​ዲህ ቃሌን ለምን አታ​ስ​ተ​ው​ሉም? ቃሌን መስ​ማት ስለ​ማ​ት​ችሉ ነው።


ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም ያመ​ኑ​በ​ትን አይ​ሁድ እን​ዲህ አላ​ቸው፥ “እና​ን​ተም በቃሌ ጸን​ታ​ችሁ ብት​ኖሩ በእ​ው​ነት ደቀ መዛ​ሙ​ርቴ ናችሁ።


ለድሆችም ወንጌል ይሰበካል፤ በእኔም የማይሰናከለው ሁሉ ብፁዕ ነው።”


በመልእክቱም ሁሉ ደግሞ እንደ ነገረ ስለዚህ ነገር ተናገረ። በእነዚያ ዘንድ ለማስተዋል የሚያስቸግር ነገር አለ፤ ያልተማሩትና የማይጸኑትም ሰዎች ሌሎችን መጻሕፍት እንደሚያጣምሙ እነዚህን ደግሞ ለገዛ ጥፋታቸው ያጣምማሉ።


ስለ እር​ሱም የም​ን​ና​ገ​ረው ብዙ ነገር አለን፤ ጆሮ​ዎ​ቻ​ች​ሁም ስለ ፈዘዙ በቃል ልን​ተ​ረ​ጕ​መው ጭንቅ ነው።


ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስና ደቀ መዛ​ሙ​ር​ቱም ወደ ሰርጉ ታደሙ።


“እው​ነት እው​ነት እላ​ች​ኋ​ለሁ፤ ሙታን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ልጅ ቃል የሚ​ሰ​ሙ​በት ሰዓት ይመ​ጣል፤ እር​ሱም አሁን ነው፤ የሚ​ሰ​ሙ​ትም ይድ​ናሉ።


አይ​ሁ​ድም፥ “ይህ እን​በላ ዘንድ ሥጋ​ውን ሊሰ​ጠን እን​ዴት ይች​ላል?” ብለው እርስ በር​ሳ​ቸው ተከ​ራ​ከሩ።


ነገር ግን ከእ​ና​ንተ ውስጥ የማ​ያ​ምኑ አሉ፤” ጌታ​ችን ኢየ​ሱስ ከጥ​ንት ጀምሮ የማ​ያ​ም​ኑ​በት እነ​ማን እንደ ሆኑ፥ የሚ​ያ​ሲ​ዘ​ውም ማን እንደ ሆነ ያውቅ ነበ​ርና።


ወን​ድ​ሞ​ቹም ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስን እን​ዲህ አሉት- “ደቀ መዛ​ሙ​ር​ትህ የም​ት​ሠ​ራ​ውን ሥራ​ህን እን​ዲ​ያዩ ከዚህ ወጥ​ተህ ወደ ይሁዳ ሀገር ሂድ።


Follow us:

Advertisements


Advertisements