Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




ዮሐንስ 6:32 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

32 ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም እን​ዲህ አላ​ቸው፥ “እው​ነት እው​ነት እላ​ች​ኋ​ለሁ፤ ያን እን​ጀራ ከሰ​ማይ የሰ​ጣ​ችሁ ሙሴ አይ​ደ​ለም፤ አባቴ ከሰ​ማይ የእ​ው​ነት እን​ጀ​ራን ሰጥ​ቶ​አ​ች​ኋል እንጂ።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

32 ኢየሱስም እንዲህ አላቸው፤ “እውነት እላችኋለሁ፤ ከሰማይ እንጀራ የሰጣችሁ ሙሴ አይደለም፤ እውነተኛውን እንጀራ ከሰማይ የሚሰጣችሁ ግን አባቴ ነው፤

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

32 ኢየሱስም “እውነት እውነት እላችኋለሁ፤ እውነተኛ እንጀራ ከሰማይ የሚሰጣችሁ አባቴ ነው እንጂ ከሰማይ እንጀራ የሰጣችሁ ሙሴ አይደለም፤

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

32 በዚህ ጊዜ ኢየሱስ እንዲህ አላቸው፦ “እውነት፥ እውነት እላችኋለሁ፤ ከሰማይ የወረደውን እንጀራ የሰጣችሁ ሙሴ አይደለም፤ እውነተኛውን እንጀራ ከሰማይ የሚሰጣችሁ አባቴ ነው፤

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

32 ኢየሱስም፦ እውነት እውነት እላችኋለሁ፥ እውነተኛ እንጀራ ከሰማይ የሚሰጣችሁ አባቴ ነው እንጂ ከሰማይ እንጀራ የሰጣችሁ ሙሴ አይደለም፤

See the chapter Copy




ዮሐንስ 6:32
14 Cross References  

“እው​ነ​ተኛ የወ​ይን ሐረግ እኔ ነኝ፤ ተካ​ዩም አባቴ ነው።


ከሰ​ማይ የወ​ረደ እን​ጀራ ይህ ነው፤ አባ​ቶ​ቻ​ችሁ በል​ተ​ውት እን​ደ​ሞ​ቱ​በት ያለ መና አይ​ደ​ለም፤ ይህን እን​ጀራ የሚ​በላ ግን ለዘ​ለ​ዓ​ለም ሕያው ሆኖ ይኖ​ራል።”


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሙሴን፥ “በሕጌ ይሄዱ ወይም አይ​ሄዱ እንደ ሆነ እኔ እን​ድ​ፈ​ት​ና​ቸው፥ እነሆ፥ ከሰ​ማይ እን​ጀ​ራን አዘ​ን​ብ​ላ​ች​ኋ​ለሁ፤ ሕዝ​ቡም ወጥ​ተው ለዕ​ለት ለዕ​ለት የሚ​በ​ቃ​ቸ​ውን ይሰ​ብ​ስቡ።


ነገር ግን ቀጠ​ሮው በደ​ረሰ ጊዜ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ልጁን ላከ፤ ከሴ​ትም ተወ​ለደ፤ የኦ​ሪ​ት​ንም ሕግ ፈጸመ።


ሥጋዬ እው​ነ​ተኛ መብል ነውና፤ ደሜም እው​ነ​ተኛ መጠጥ ነውና።


ከእ​ርሱ የበላ ሁሉ እን​ዳ​ይ​ሞት ከሰ​ማይ የወ​ረደ እን​ጀራ ይህ ነው።”


አይ​ሁ​ድም ስለ እርሱ አን​ጐ​ራ​ጐሩ፤ “ከሰ​ማይ የወ​ረደ የሕ​ይ​ወት እን​ጀራ እኔ ነኝ” ብሎ​አ​ቸ​ዋ​ልና።


ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም እን​ዲህ አላ​ቸው፥ “የሕ​ይ​ወት እን​ጀራ እኔ ነኝ፤ ወደ እኔ የሚ​መጣ ከቶ አይ​ራ​ብም፤ በእኔ የሚ​ያ​ም​ንም ለዘ​ለ​ዓ​ለም አይ​ጠ​ማም።


የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ጀራ ከሰ​ማይ የሚ​ወ​ርድ፤ ለዓ​ለ​ምም ሕይ​ወ​ትን የሚ​ሰጥ ነውና።”


ለሰው ሁሉ የሚ​ያ​በ​ራው እው​ነ​ተ​ኛው ብር​ሃ​ንስ ወደ ዓለም የመ​ጣው ነው።


ሙሴም፥ “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ያን​ጐ​ራ​ጐ​ራ​ች​ሁ​በ​ትን ማን​ጐ​ራ​ጐ​ራ​ች​ሁን ሰም​ቶ​አ​ልና በመሸ ጊዜ ትበሉ ዘንድ ሥጋን፥ በማ​ለ​ዳም ትጠ​ግቡ ዘንድ እን​ጀ​ራን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይሰ​ጣ​ች​ኋል፤ እኛም ምን​ድን ነን? ማን​ጐ​ራ​ጐ​ራ​ችሁ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ላይ ነው እንጂ በእኛ ላይ አይ​ደ​ለም” አለ።


የእግዚአብሔርም ልጅ እንደ መጣ፥ እውነተኛም የሆነውን እናውቅ ዘንድ ልቡናን እንደ ሰጠን እናውቃለን፤ እውነተኛም በሆነው በእርሱ አለን፥ እርሱም ልጁ ኢየሱስ ክርስቶስ ነው። እርሱ እውነተኛ አምላክና የዘላለም ሕይወት ነው።


አባ​ቶ​ቻ​ች​ንስ ‘ሊበሉ እን​ጀራ ከሰ​ማይ ሰጣ​ቸው’ ተብሎ እንደ ተጻፈ በም​ድረ በዳ መና በሉ።


Follow us:

Advertisements


Advertisements