Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




ዮሐንስ 5:21 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

21 አብ ሙታ​ንን እን​ደ​ሚ​ያ​ስ​ነ​ሣ​ቸው፥ ሕይ​ወ​ት​ንም እን​ደ​ሚ​ሰ​ጣ​ቸው እን​ዲሁ ወል​ድም ለሚ​ወ​ድ​ዳ​ቸው ሕይ​ወ​ትን ይሰ​ጣል።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

21 ምክንያቱም አብ ሙታንን እንደሚያስነሣ፣ ሕይወትንም እንደሚሰጥ፣ ወልድም ደግሞ ለሚፈቅደው ሁሉ ሕይወትን ይሰጣል።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

21 አብ ሙታንን እንደሚያስነሣቸው፥ ሕይወትም እንደሚሰጣቸው፥ እንዲሁ ወልድ ደግሞ ለሚወዳቸው ሕይወትን ይሰጣቸዋል።

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

21 አብ የሞቱትን እንደሚያስነሣና ሕይወትን እንደሚሰጣቸው፥ ወልድም እንዲሁ ለፈለገው ሰው ሕይወትን ይሰጠዋል።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

21 አብ ሙታንን ይንደሚያነሣ ሕይወትም እንደሚሰጣቸው፥ እንዲሁ ወልድ ደግሞ ለሚወዳቸው ሕይወትን ይሰጣቸዋል።

See the chapter Copy




ዮሐንስ 5:21
14 Cross References  

ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስን ከሙ​ታን ለይቶ ያስ​ነ​ሣው የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መን​ፈስ ካደ​ረ​ባ​ችሁ ኢየ​ሱስ ክር​ስ​ቶ​ስን ከሙ​ታን ለይቶ ያስ​ነ​ሣው እርሱ አድ​ሮ​ባ​ችሁ ባለ መን​ፈሱ ለሟች ሰው​ነ​ታ​ችሁ ሕይ​ወ​ትን ይሰ​ጣ​ታል።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እንደ ሆንሁ፥ ከእ​ኔም በቀር አም​ላክ እን​ደ​ሌለ ዕወቁ፤ ዕወቁ። እኔ እገ​ድ​ላ​ለሁ፤ አድ​ን​ማ​ለሁ፤ እኔ እገ​ር​ፋ​ለሁ፤ ይቅ​ርም እላ​ለሁ፤ ከእ​ጄም የሚ​ያ​መ​ልጥ የለም።


ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም አላት፥ “ትን​ሣ​ኤና ሕይ​ወት እኔ ነኝ፤ የሚ​ያ​ም​ን​ብኝ ቢሞ​ትም ይነ​ሣል።


እን​ዴ​ትስ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሙታ​ንን እን​ደ​ሚ​ያ​ስ​ነ​ሣ​ቸው በእ​ና​ንተ ዘንድ የማ​ይ​ታ​መን ሆኖ ይቈ​ጠ​ራል?


ሥጋ በለ​በ​ሰው ሁሉ ላይ ሥል​ጣ​ንን እንደ ሰጠ​ኸው መጠን ለሰ​ጠ​ኸው ሁሉ የዘ​ለ​ዓ​ለም ሕይ​ወ​ትን ይሰ​ጣ​ቸው ዘንድ።


የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ንጉሥ ደብ​ዳ​ቤ​ውን ባነ​በበ ጊዜ ልብ​ሱን ቀድዶ፥ “ሰውን ከለ​ምጹ እፈ​ውስ ዘንድ ይህ ሰው ወደ እኔ መስ​ደዱ እኔ በውኑ ለመ​ግ​ደ​ልና ለማ​ዳን የም​ችል አም​ላክ ነኝን? ተመ​ል​ከቱ፥ የጠብ ምክ​ን​ያት እን​ደ​ሚ​ፈ​ል​ግ​ብኝ ተመ​ል​ከቱ” አለ።


በብ​ላ​ቴ​ና​ውም ላይ ሦስት ጊዜ እፍ አለ​በት፤ ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም፥ “አቤቱ አም​ላኬ ሆይ፥ የዚህ ብላ​ቴና ነፍስ ወደ እርሱ ትመ​ለስ ዘንድ እለ​ም​ን​ሃ​ለሁ” ብሎ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ጠራው።


ሕይ​ወ​ትን የሚ​ሰጥ መን​ፈስ ነው፤ ሥጋ ግን አን​ዳች አይ​ጠ​ቅ​ምም፤ ይህም እኔ የም​ነ​ግ​ራ​ችሁ ቃል መን​ፈስ ነው፤ ሕይ​ወ​ትም ነው።


መጽ​ሐፍ እን​ዲሁ ብሎ​አ​ልና የመ​ጀ​መ​ሪ​ያው ሰው አዳም በነ​ፍስ ሕያው ሆኖ ተፈ​ጠረ፤ ሁለ​ተ​ኛው አዳም ግን ሕይ​ወ​ትን የሚ​ሰጥ መን​ፈስ ነው።


Follow us:

Advertisements


Advertisements