Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




ዮሐንስ 4:39 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

39 “የሠ​ራ​ሁ​ትን ሁሉ ነገ​ረኝ” ብላ የመ​ሰ​ከ​ረ​ችው ሴት ስለ ነገ​ረ​ቻ​ቸ​ውም ከዚ​ያች ከሰ​ማ​ርያ ከተማ ብዙ​ዎች አመ​ኑ​በት።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

39 ሴቲቱም፣ “ያደረግሁትን ሁሉ ነገረኝ” ብላ ስለ መሰከረች፣ ከዚያች ከተማ ብዙ ሳምራውያን በርሱ አመኑ።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

39 ሴቲቱም “ያደረግሁትን ሁሉ ነገረኝ፤” ብላ በመሰከረችው ቃል መሠረት፥ ከዚያች ከተማ፥ ብዙ የሰማርያ ሰዎች በእርሱ አመኑ።

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

39 ሴትዮዋ “የሠራሁትን ነገር ሁሉ ነገረኝ” ብላ በመሰከረችው መሠረት ከዚያ ከተማ ብዙዎቹ የሰማርያ ሰዎች አመኑ።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

39 ሴቲቱም፦ ያደረግሁትን ሁሉ ነገረኝ ብላ ስለ መሰከረችው ቃል ከዚያች ከተማ የሰማርያ ሰዎች ብዙ አመኑበት።

See the chapter Copy




ዮሐንስ 4:39
11 Cross References  

“የሠ​ራ​ሁ​ትን ሁሉ የነ​ገ​ረ​ኝን ሰው ታዩ ዘንድ ኑ፤ እንጃ፥ እርሱ ክር​ስ​ቶስ ይሆን?”


ያዕ​ቆብ ለልጁ ለዮ​ሴፍ በሰ​ጠው በወ​ይን ቦታ አቅ​ራ​ቢያ ወደ አለ​ችው ሲካር ወደ​ም​ት​ባ​ለው የሰ​ማ​ርያ ከተማ ደረሰ።


ስለ​ዚህ ከአ​ይ​ሁ​ድም ወደ ማር​ታና ወደ ማር​ያም መጥ​ተው የነ​በሩ ብዙ ሰዎች ጌታ​ችን ኢየ​ሱስ ያደ​ረ​ገ​ውን አይ​ተው በእ​ርሱ አመኑ።


ሴቲ​ቱ​ንም፥ “እኛ ራሳ​ችን ይህ በእ​ው​ነት የዓ​ለም መድ​ኀ​ኒት ክር​ስ​ቶስ እንደ ሆነ ሰም​ተ​ንና ተረ​ድ​ተን ነው እንጂ በአ​ንቺ ቃል ያመ​ን​በት አይ​ደ​ለም” አሏት።


እነዚህን ዐሥራ ሁለቱን ኢየሱስ ላካቸው፤ አዘዛቸውም፤ እንዲህም አለ “በአሕዛብ መንገድ አትሂዱ፤ ወደ ሳምራውያንም ከተማ አትግቡ፤


ደቀ መዛ​ሙ​ርቱ ምግብ ሊገዙ ወደ ከተማ ሄደው ነበ​ርና።


ከከ​ተ​ማም ወጥ​ተው ወደ እርሱ ሄዱ።


እኔም ያል​ደ​ከ​ማ​ች​ሁ​በ​ትን እን​ድ​ታ​ጭዱ ላክ​ኋ​ችሁ፤ ሌሎች ደከሙ፤ እና​ን​ተም በድ​ካ​ማ​ቸው ገባ​ችሁ።”


ሳም​ራ​ው​ያ​ንም ሁሉ ወደ እርሱ መጥ​ተው በእ​ነ​ርሱ ዘንድ እን​ዲ​ኖር ማለ​ዱት፤ ሁለት ቀንም ያህል በዚያ ተቀ​መጠ።


ሁለቱ ደቀ መዛ​ሙ​ር​ቱም እን​ዲህ ሲል ሰም​ተው ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስን ተከ​ተ​ሉት።


Follow us:

Advertisements


Advertisements