Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




ዮሐንስ 4:18 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

18 ቀድሞ አም​ስት ባሎች ነበ​ሩሽ፤ ዛሬ አብ​ሮሽ ያለው ግን ባልሽ አይ​ደ​ለም፤ ይህ​ንስ እው​ነት አልሽ።”

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

18 በርግጥ ዐምስት ባሎች ነበሩሽ፤ አሁን ከአንቺ ጋራ ያለውም ባልሽ ስላልሆነ፣ የተናገርሽው እውነት ነው።”

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

18 አምስት ባሎች ነበሩሽና፤ አሁን ከአንቺ ጋር ያለው ባልሽ አይደለም፤ በዚህስ እውነቱን ተናገርሽ፤” አላት።

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

18 አምስት ባሎች ነበሩሽ፤ አሁንም ከአንቺ ጋር ያለው ሰው ባልሽ አይደለም፤ ስለዚህ እውነቱን ተናግረሻል።”

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

18 አምስት ባሎች ነበሩሽና፥ አሁን ከአንቺ ጋር ያለው ባልሽ አይደለም፤ በዚህስ እውነት ተናገርሽ አላት።

See the chapter Copy




ዮሐንስ 4:18
16 Cross References  

ሚስት ባል​ዋን እን​ደ​ም​ት​ከዳ እን​ዲሁ የእ​ስ​ራ​ኤል ቤት ከዱኝ” ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።


እርስዋም ባልዋን ፈትታ ሌላ ብታገባ ታመነዝራለች፤” አላቸው።


ስለ​ዚህ ባልዋ በሕ​ይ​ወት ሳለ ለሌላ ወንድ ብት​ሆን አመ​ን​ዝራ ትሆ​ና​ለች፤ ባልዋ ቢሞት ግን ከሕግ ነፃ ወጥ​ታ​ለች፤ ለሌላ ወንድ ብት​ሆ​ንም አመ​ን​ዝራ አት​ባ​ልም።


ከባ​ልዋ ገን​ዘብ ተቀ​ብላ የም​ታ​መ​ነ​ዝር ሴትን ትመ​ስ​ያ​ለሽ።


ደግሞም የምዋቹ ስም ከወንድሞቹ መካከል ከአገሩም ደጅ እንዳይጠፋ፥ የምዋቹን ስም በርስቱ ላይ እንዳስነሣ የመሐሎንን ሚስት ሞዓባዊቱን ሩትን ሚስት ትሆነኝ ዘንድ ወሰድሁአት፣ እናንተም ዛሬ ምስክሮች ናችሁ አላቸው።


“በባ​ልዋ ላይ ለበ​ደ​ለ​ችና ራስ​ዋን ላረ​ከ​ሰች ሴት የቅ​ን​ዐት ሕግ ይህ ነው፤


እነ​ር​ሱም፥ “እኅ​ታ​ች​ንን እንደ አመ​ን​ዝራ አድ​ር​ገው ለምን አዋ​ረ​ዷት?” አሉት።


የሀ​ገሩ አለቃ የኤ​ዊ​ያ​ዊው ሰው የኤ​ሞር ልጅ ሴኬም አያት፤ ወሰ​ዳ​ትም፤ ከእ​ር​ስ​ዋም ጋር ተኛ፤ አስ​ነ​ወ​ራ​ትም።


በዚ​ያች ሌሊ​ትም አቤ​ሜ​ሌክ ተኝቶ ሳለ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በሕ​ልም ወደ እርሱ መጣ፤ እን​ዲ​ህም አለው፥ “እነሆ፥ አንተ ስለ ወሰ​ድ​ሃት ሴት ትሞ​ታ​ለህ፤ እር​ስዋ ባለ ባል ናትና።”


መጋ​ባት በሁሉ ዘንድ ክቡር ነው፥ ለመ​ኝ​ታ​ቸ​ውም ርኵ​ሰት የለ​ውም፤ ሴሰ​ኞ​ች​ንና አመ​ን​ዝ​ሮ​ችን ግን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይፈ​ር​ድ​ባ​ቸ​ዋል።


ሴቲ​ቱም፥ “ባል የለ​ኝም” ብላ መለ​ሰ​ች​ለት፤ ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም እን​ዲህ አላት፥ “ባል የለ​ኝም በማ​ለ​ትሽ መል​ካም ተና​ገ​ርሽ።


ሴቲ​ቱም እን​ዲህ አለ​ችው፥ “ጌታዬ፥ አንተ ነቢይ እንደ ሆንህ አያ​ለሁ።


“ስለ​ዚህ ዘማ ሆይ! የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቃል ስሚ።


ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም፥ “ሂደሽ ባል​ሽን ጥሪና ወደ​ዚህ ነይ” አላት።


Follow us:

Advertisements


Advertisements