Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




ዮሐንስ 3:23 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

23 ዮሐ​ን​ስም በዮ​ር​ዳ​ኖስ ማዶ በሳ​ሌም አቅ​ራ​ቢያ በሄ​ኖን ያጠ​ምቅ ነበር፤ በዚያ ብዙ ውኃ ነበ​ርና፤ ብዙ ሰዎ​ችም ወደ እርሱ እየ​መጡ ያጠ​ም​ቃ​ቸው ነበር።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

23 በዚህ ጊዜ ዮሐንስም በሳሌም አቅራቢያ ሄኖን በተባለ ስፍራ ብዙ ውሃ ስለ ነበረ ያጠምቅ ነበር፤ ሰዎችም ለመጠመቅ ይመጡ ነበር።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

23 ዮሐንስም ደግሞ በሳሌም አቅራቢያ በሄኖን፥ በዚያ ብዙ ውሃ ነበርና፥ ያጠምቅ ነበር፤ እየመጡም ይጠመቁ ነበር፤

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

23 በዚያኑ ጊዜ ዮሐንስም ብዙ ውሃ ስለ ነበረበት በሳሌም አቅራቢያ ሄኖን በተባለ ስፍራ ያጠምቅ ነበር፤ ሰዎችም እየመጡ ይጠመቁ ነበር።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

23 ዮሐንስም ደግሞ በሳሌም አቅራቢያ በሄኖን በዚያ ብዙ ውኃ ነበርና ያጠምቅ ነበር፥

See the chapter Copy




ዮሐንስ 3:23
13 Cross References  

ዮሐ​ን​ስም ሊያ​ጠ​ም​ቃ​ቸው የመ​ጡ​ትን ሰዎች እን​ዲህ አላ​ቸው፥ “እና​ንት የእ​ፉ​ኝት ልጆች፥ ከሚ​መ​ጣው መቅ​ሠ​ፍት ታመ​ልጡ ዘንድ ማን ነገ​ራ​ችሁ?


እነ​ሆም የእ​ስ​ራ​ኤል አም​ላክ ክብር ከም​ሥ​ራቅ መን​ገድ መጣ፤ ድም​ፁም እንደ ብዙ ውኆች ይተ​ምም ነበር፤ ከክ​ብ​ሩም የተ​ነሣ ምድር ታበራ ነበር።


“እና​ትህ በውኃ አጠ​ገብ እንደ ተተ​ከ​ለች እንደ ወይን ግን​ድና እንደ ጽጌ​ረዳ ነበ​ረች፤ ከው​ኃም ብዛት የተ​ነሣ የም​ታ​ፈ​ራና የም​ት​ሰፋ ሆነች።


አንቺ በብዙ ውኃ አጠ​ገብ የተ​ቀ​መ​ጥሽ፥ በመ​ዝ​ገ​ብም የበ​ለ​ጠ​ግሽ ሆይ! እንደ ስስ​ትሽ መጠን ፍጻ​ሜሽ ደር​ሶ​አል።


ወደ ተራ​ራ​ማ​ውም ወደ ኤፍ​ሬም ሀገር ሄዱ፤ በሲ​ልካ ምድ​ርም አለፉ፤ አላ​ገ​ኙ​አ​ቸ​ው​ምም፤ በፋ​ስ​ቂም ምድር አለፉ፤ በዚ​ያም አል​ነ​በ​ሩም፤ በኢ​ያ​ሚ​ንም ምድር አለፉ፤ አላ​ገ​ኙ​አ​ቸ​ው​ምም።


ያዕ​ቆ​ብም ከሁ​ለቱ ወን​ዞች መካ​ከል በተ​መ​ለሰ ጊዜ በከ​ነ​ዓን ምድር ወዳ​ለ​ችው ወደ ሰቂ​ሞን ከተማ ወደ ሴሎም መጣ፤ በከ​ተ​ማ​ዪ​ቱም ፊት ለፊት ሰፈረ።


እንደ ብዙ ሕዝብም ድምፅ፥ እንደ ብዙ ውሃዎችም ድምፅ፥ እንደ ብርቱም ነጐድጓድ ድምፅ ያለ ድምፅ እንዲህ ሲል ሰማሁ፤ “ሃሌ ሉያ! ሁሉን የሚገዛ ጌታ አምላካችን ነግሦአልና።


እንደ ብዙ ውሃም ድምፅና እንደ ታላቅ ነጐድጓድ ድምፅ ያለ ከሰማይ ድምፅን ሰማሁ፤ ደርዳሪዎችም በገና እንደሚደረድሩ ያለ ድምፅ ሰማሁ።


እግሮቹም በእቶን የነጠረ የጋለ ናስ ይመስሉ ነበር፤ ድምፁም እንደ ብዙ ውሃዎች ድምፅ ነበረ።


ከዚ​ህም በኋላ ጌታ​ችን ኢየ​ሱስ ከደቀ መዛ​ሙ​ርቱ ጋር ወደ ይሁዳ ምድር ሄደ፤ በዚ​ያም እያ​ጠ​መቀ አብ​ሮ​አ​ቸው ተቀ​መጠ።


ዮሐ​ንስ ገና ወደ ወኅኒ ቤት አል​ገ​ባም ነበ​ርና።


Follow us:

Advertisements


Advertisements