Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




ዮሐንስ 3:22 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

22 ከዚ​ህም በኋላ ጌታ​ችን ኢየ​ሱስ ከደቀ መዛ​ሙ​ርቱ ጋር ወደ ይሁዳ ምድር ሄደ፤ በዚ​ያም እያ​ጠ​መቀ አብ​ሮ​አ​ቸው ተቀ​መጠ።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

22 ከዚህ በኋላ ኢየሱስና ደቀ መዛሙርቱ ወደ ይሁዳ አገር ሄዱ፤ እዚያም ከእነርሱ ጋራ ጥቂት ተቀመጠ፤ አጠመቀም።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

22 ከዚህ በኋላ ኢየሱስ ከደቀ መዛሙርቱ ጋር ወደ ይሁዳ አገር መጣ፤ በዚያም ከእነርሱ ጋር ተቀምጦ ያጠምቅ ነበር።

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

22 ከዚህ በኋላ ኢየሱስ ከደቀ መዛሙርቱ ጋር ወደ ይሁዳ ምድር ሄደ፤ በዚያም እያጠመቀ ከእነርሱ ጋር ለጥቂት ጊዜ ቈየ።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

22 ከዚህ በኋላ ኢየሱስ ከደቀ መዛሙርቱ ጋር ወደ ይሁዳ አገር መጣ፥ በዚያም ከእነርሱ ጋር ተቀምጦ ያጠምቅ ነበር።

See the chapter Copy




ዮሐንስ 3:22
6 Cross References  

ወደ ዮሐ​ን​ስም ሄደው፥ “መም​ህር ሆይ፥ በዮ​ር​ዳ​ኖስ ማዶ ካንተ ጋር የነ​በ​ረው፥ አን​ተም የመ​ሰ​ከ​ር​ህ​ለት እርሱ እነሆ፥ ያጠ​ም​ቃል፤ ሁሉም ወደ እርሱ ይሄ​ዳል” አሉት።


ወን​ድ​ሞ​ቹም ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስን እን​ዲህ አሉት- “ደቀ መዛ​ሙ​ር​ትህ የም​ት​ሠ​ራ​ውን ሥራ​ህን እን​ዲ​ያዩ ከዚህ ወጥ​ተህ ወደ ይሁዳ ሀገር ሂድ።


የአ​ይ​ሁ​ድም የፋ​ሲ​ካ​ቸው በዓል ቀርቦ ነበር፤ ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም ወደ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም ወጣ።


ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስና ደቀ መዛ​ሙ​ር​ቱም ወደ ሰርጉ ታደሙ።


ዮሐ​ን​ስም በዮ​ር​ዳ​ኖስ ማዶ በሳ​ሌም አቅ​ራ​ቢያ በሄ​ኖን ያጠ​ምቅ ነበር፤ በዚያ ብዙ ውኃ ነበ​ርና፤ ብዙ ሰዎ​ችም ወደ እርሱ እየ​መጡ ያጠ​ም​ቃ​ቸው ነበር።


Follow us:

Advertisements


Advertisements