Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




ዮሐንስ 2:22 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

22 ከሙ​ታን በተ​ነሣ ጊዜም ደቀ መዛ​ሙ​ርቱ ስለ​ዚህ እንደ ነገ​ራ​ቸው ዐሰቡ፤ በመ​ጻ​ሕ​ፍት ቃልና ጌታ​ችን ኢየ​ሱስ በነ​ገ​ራ​ቸ​ውም ነገር አመኑ።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

22 ከሙታንም ከተነሣ በኋላ፣ ደቀ መዛሙርቱ ምን እንደ ተናገረ አስታወሱ፤ መጻሕፍትንና ኢየሱስ ያለውንም ቃል አመኑ።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

22 ስለዚህ ከሙታን ከተነሣ በኋላ ደቀመዛሙርቱ ይህን እንደ ተናገረ አሰቡና መጽሐፍንና ኢየሱስ የተናገረውን ቃል አመኑ።

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

22 ስለዚህ ኢየሱስ ከሞት በተነሣ ጊዜ ደቀ መዛሙርቱ ይህን ተናግሮ እንደ ነበረ አስታወሱ፤ በዚህ ምክንያት በቅዱስ መጽሐፍ የተጻፈውንና ኢየሱስ የተናገረውን ቃል አመኑ።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

22 ስለዚህ ከሙታን ከተነሣ በኋላ ደቀ መዛሙርቱ ይህን እንደ ተናገረ አሰቡና መጽሐፍንና ኢየሱስ የተናገረውን ቃል አመኑ።

See the chapter Copy




ዮሐንስ 2:22
13 Cross References  

ደቀ መዛ​ሙ​ር​ቱም አስ​ቀ​ድ​መው ይህን ነገር አላ​ወ​ቁም፤ ነገር ግን ጌታ​ችን ኢየ​ሱስ ከከ​በረ በኋላ በዚያ ጊዜ ይህ ነገር ስለ እርሱ እንደ ተጻፈ፥ ይህ​ንም እንደ አደ​ረ​ጉ​ለት ትዝ አላ​ቸው።


ነገር ግን ጊዜው ሲደ​ርስ እኔ እንደ ነገ​ር​ኋ​ችሁ ታስቡ ዘንድ ይህን ነገ​ር​ኋ​ችሁ። አስ​ቀ​ድሜ ግን ይህን አል​ነ​ገ​ር​ክ​ኋ​ች​ሁም ነበር፤ ከእ​ና​ንተ ጋር ነበ​ር​ሁና።


ነገር ግን አብ በስሜ የሚ​ል​ከው የእ​ው​ነት መን​ፈስ ጰራ​ቅ​ሊ​ጦስ እርሱ ሁሉን ያስ​ተ​ም​ራ​ች​ኋል፤ እኔ የነ​ገ​ር​ኋ​ች​ሁ​ንም ሁሉ ያሳ​ስ​ባ​ች​ኋል።


አን​ጀ​ታ​ቸ​ውን ቋጠሩ፥ አፋ​ቸ​ውም ትዕ​ቢ​ትን ተና​ገረ።


ደቀ መዛ​ሙ​ር​ቱም፥ “የቤ​ትህ ቅናት በላኝ” የሚል ቃል ተጽፎ እን​ዳለ ዐሰቡ።


‘ዮሐ​ንስ በውኃ አጠ​መቀ፤ እና​ንተ ግን፤ በመ​ን​ፈስ ቅዱስ ትጠ​መ​ቃ​ላ​ችሁ’ ያለ​ውን የጌ​ታ​ች​ንን ቃል ዐሰ​ብሁ።


ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም በቃና ዘገ​ሊላ ያደ​ረ​ገው የተ​አ​ም​ራት መጀ​መ​ሪያ ይህ ነው፤ ክብ​ሩ​ንም ገለጠ፤ ደቀ መዛ​ሙ​ር​ቱም አመ​ኑ​በት።


እር​ሱም፥ “በሙሴ ኦሪት፥ በነ​ቢ​ያ​ትና በመ​ዝ​ሙ​ርም ስለ እኔ የተ​ነ​ገ​ረው ይፈ​ጸም ዘንድ እን​ዳ​ለው፥ ከእ​ና​ንተ ጋር ሳለሁ የነ​ገ​ር​ኋ​ችሁ ነገሬ ይህ ነው” አላ​ቸው።


ክር​ስ​ቶስ እን​ዲህ ይሞት ዘንድ ወደ ክብ​ሩም ይመ​ለስ ዘንድ ያለው አይ​ደ​ለ​ምን?”


ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስና ደቀ መዛ​ሙ​ር​ቱም ወደ ሰርጉ ታደሙ።


በሁ​ለ​ተ​ኛው መዝ​ሙር፦ ‘አንተ ልጄ ነህ፤ እኔ ዛሬ ወለ​ድ​ሁህ’ እን​ዳለ ኢየ​ሱ​ስን አስ​ነ​ሥቶ ተስ​ፋ​ውን ለእኛ ለል​ጆ​ቻ​ቸው ፈጽ​ሞ​አል።


Follow us:

Advertisements


Advertisements