Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




ዮሐንስ 2:18 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

18 አይ​ሁ​ድም መል​ሰው፥ “ይህን የም​ታ​ደ​ርግ ምን ምል​ክት ታሳ​ያ​ለህ?” አሉት።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

18 አይሁድም፣ “ይህን ሁሉ ለማድረግ ሥልጣን እንዳለህ የሚያረጋግጥ ምን ታምራዊ ምልክት ታሳየናለህ?” አሉት።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

18 ስለዚህ አይሁድ መልሰው “ይህንን ስለ ማድረግህ ምን ምልክት ታሳየናለህ?” አሉት።

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

18 ከዚህ በኋላ የአይሁድ ባለሥልጣኖች ኢየሱስን፦ “አንተ ይህን ለማድረግ ሥልጣን እንዳለህ ምን ተአምር ታሳየናለህ?” አሉት።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

18 ስለዚህ አይሁድ መልሰው፦ ይህን ስለምታደርግ ምን ምልክት ታሳየናለህ? አሉት።

See the chapter Copy




ዮሐንስ 2:18
14 Cross References  

እነ​ር​ሱም እን​ዲህ አሉት፥ “የም​ት​ሠ​ራ​ውን አይ​ተን በአ​ንተ እና​ምን ዘንድ ምን ተአ​ም​ራት ታደ​ር​ጋ​ለህ?


“በኢ​የ​ሱስ ስም ለማ​ንም እን​ዳ​ታ​ስ​ተ​ምሩ ከል​ክ​ለ​ና​ችሁ አል​ነ​በ​ረ​ምን? እነሆ፥ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌ​ምን በት​ም​ህ​ር​ታ​ችሁ ሞላ​ች​ኋት፤ የዚ​ያ​ንም ሰው ደም በእኛ ላይ ታመ​ጡ​ብን ዘንድ ትሻ​ላ​ች​ሁን?” አላ​ቸው።


በአ​ደ​ባ​ባ​ይም አቆ​ሙና፥ “እና​ንተ ይህን በማን ስምና በማን ኀይል አደ​ረ​ጋ​ች​ሁት?” ብለው መረ​መ​ሩ​አ​ቸው።


“እን​ኪ​ያስ ክር​ስ​ቶ​ስን ካል​ሆ​ንህ፥ ኤል​ያ​ስ​ንም ካል​ሆ​ንህ፥ ነቢ​ይ​ንም ካል​ሆ​ንህ ለምን ታጠ​ም​ቃ​ለህ?” ብለው ጠየ​ቁት።


ብዙ ሰዎ​ችም ተሰ​ብ​ስ​በው ሳሉ እን​ዲህ ይላ​ቸው ጀመረ ፥ “ይቺ ትው​ልድ ክፉ ናት፤ ምል​ክ​ትም ትሻ​ለች፤ ነገር ግን ከነ​ቢዩ ከዮ​ናስ ምል​ክት በቀር ምል​ክት አይ​ሰ​ጣ​ትም።


ፈሪሳውያንም ወጡና ሊፈትኑት ከሰማይ ምልክት ከእርሱ ፈልገው ከእርሱ ጋር ይከራከሩ ጀመር።


ወደ መቅደስም ገብቶ ሲያስተምር የካህናት አለቆችና የሕዝብ ሽማግሎች ወደ እርሱ ቀረቡና “በምን ሥልጣን እነዚህን ታደርጋለህ? ይህንስ ሥልጣን ማን ሰጠህ?” አሉት።


“ፈር​ዖን፦ ተአ​ም​ራ​ት​ንና ድን​ቅን አሳ​ዩኝ ሲላ​ችሁ፥ ወን​ድ​ምህ አሮ​ንን፦ ‘በት​ር​ህን ወስ​ደህ በፈ​ር​ዖ​ንና በሹ​ሞቹ ፊት ጣላት’ በለው፤ እባ​ብም ትሆ​ና​ለች።”


በዚ​ያም ቀን፦ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የተ​ና​ገ​ረው ቃል ይህ ነው፤ “እነሆ፥ መሠ​ዊ​ያው ይሰ​ነ​ጠ​ቃል፤ በው​ስ​ጡም ያለው ስብ ይፈ​ስ​ሳል” ብሎ ምል​ክት ሰጠ።


አይ​ሁድ፥ “አንተ ማን ነህ?” ብለው ይጠ​ይ​ቁት ዘንድ ካህ​ና​ት​ንና ሌዋ​ው​ያ​ንን ከኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም በላኩ ጊዜ የዮ​ሐ​ንስ ምስ​ክ​ር​ነት ይህ ነው።


Follow us:

Advertisements


Advertisements