Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




ዮሐንስ 2:15 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

15 የገ​መ​ድም ጅራፍ አበጀ፤ በጎ​ች​ንና በሬ​ዎ​ችን፥ ሁሉ​ንም ከቤተ መቅ​ደስ አስ​ወጣ፤ የለ​ዋ​ጮ​ች​ንም ገን​ዘብ በተነ፤ ገበ​ታ​ዎ​ቻ​ቸ​ው​ንም ገለ​በጠ።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

15 የገመድ ጅራፍ አበጅቶ በጎችንና ከብቶችን ሁሉ ከቤተ መቅደሱ ግቢ አስወጣ፤ የገንዘብ ለዋጮችን ሳንቲም በተነ፤ ጠረጴዛዎቻቸውንም ገለበጠ።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

15 የገመድም ጅራፍ አበጅቶ ሁሉን በጎችንም በሬዎችንም ከመቅደስ አወጣቸው፤ የለዋጮችንም ገንዘብ በተነ፤ ገበታዎቻቸውንም ገለበጠ፤

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

15 በዚህ ጊዜ የገመድ ጅራፍ አበጀና ሰዎችን ሁሉ፥ ከበጎችና ከበሬዎች ጋር ከቤተ መቅደስ አስወጣቸው፤ የገንዘብ ለዋጮችንም ገንዘብ በተነ፤ ጠረጴዛዎቻቸውንም ገለባበጠ።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

15 የገመድም ጅራፍ አበጅቶ ሁሉን በጎችንም በሬዎችንም ከመቅደስ አወጣቸው፥ የለዋጮችንም ገንዘብ አፈሰሰ ገበታዎቻቸውንም ገለበጠ፥

See the chapter Copy




ዮሐንስ 2:15
7 Cross References  

የጦር ዕቃ​ችን ሥጋዊ አይ​ደ​ለ​ምና፥ ጽኑ ምሽ​ግን በሚ​ያ​ፈ​ርስ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ኀይል ነው እንጂ።


ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም፥ “እኔ ነኝ” ባላ​ቸው ጊዜ፤ ወደ ኋላ​ቸው ተመ​ል​ሰው በም​ድር ላይ ወደቁ።


መልሶም፦ ለዘሩባቤል የተባለው የእግዚአብሔር ቃል ይህ ነው፦ በመንፈሴ እንጂ በኃይልና በብርታት አይደለም፥ ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር።


ኢየሱስም ወደ መቅደስ ገባና በመቅደስ የሚሸጡትንና የሚገዙትን ሁሉ አስወጣ፤ የገንዘብ ለዋጮችንም ገበታዎች የርግብ ሻጮችንም ወንበሮች ገለበጠና


በቤተ መቅ​ደ​ስም በሬ​ዎ​ች​ንና በጎ​ችን፥ ርግ​ቦ​ች​ንም የሚ​ሸ​ጡ​ትን፥ ገን​ዘብ ለዋ​ጮ​ች​ንም ተቀ​ም​ጠው አገኘ።


ርግብ ሻጮ​ች​ንም፥ “ይህን ከዚህ አውጡ፤ የአ​ባ​ቴን ቤት የን​ግድ ቤት አታ​ድ​ርጉ” አላ​ቸው።


ወታ​ደ​ሮ​ችም ወዲ​ያ​ውኑ ተነ​ሥ​ተው የታ​ን​ኳ​ዪ​ቱን ገመድ ቈር​ጠው ትወ​ድቅ ዘንድ ተዉ​አት።


Follow us:

Advertisements


Advertisements