Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




ዮሐንስ 2:10 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

10 አሳ​ዳ​ሪ​ውም ሙሽ​ራ​ውን ጠርቶ፥ “ሰው ሁሉ መል​ካ​ሙን የወ​ይን ጠጅ አስ​ቀ​ድሞ ያጠ​ጣል፤ ከጠ​ገቡ በኋ​ላም ተር​ታ​ውን ያመ​ጣል፤ አንተ ግን መል​ካ​ሙን የወ​ይን ጠጅ እስ​ካ​ሁን አቈ​የህ” አለው።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

10 “ሰው ሁሉ በመጀመሪያ የሚያቀርበው ጥሩውን የወይን ጠጅ ነው፤ እንግዶቹም ብዙ ከጠጡ በኋላ መናኛውን የወይን ጠጅ ያቀርባል፤ አንተ ግን ጥሩውን የወይን ጠጅ እስከ አሁን አቈይተሃል” አለው።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

10 “ሰው ሁሉ አስቀድሞ መልካሙን የወይን ጠጅ ያቀርባል፤ ከሰከሩም በኋላ መናኛውን፤ አንተ ግን መልካሙን የወይን ጠጅ እስከ አሁን አቆይተሃል፤” አለው።

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

10 “ሰው ሁሉ አስቀድሞ የሚያቀርበው ጥሩውን የወይን ጠጅ ነው፤ ተጋባዦቹ ከጠጡ በኋላ መናኛውን ያቀርባል፤ አንተ ግን ጥሩውን የወይን ጠጅ እስከ አሁን አቈየህ።”

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

10 ሰው ሁሉ አስቀድሞ መልካሙን የወይን ጠጅ ያቀርባል፥ ከሰከሩም በኋላ መናኛውን፤ አንተስ መልካሙን የወይን ጠጅ እስከ አሁን አቆይተሃል አለው።

See the chapter Copy




ዮሐንስ 2:10
15 Cross References  

አብ​ር​ሃም ግን እን​ዲህ አለው፦ ‘ልጄ ሆይ፥ አንተ በሕ​ይ​ወ​ትህ ተድ​ላና ደስታ እን​ዳ​ደ​ረ​ግህ፥ አል​ዓ​ዛ​ርም እን​ዲሁ ሁል​ጊዜ በች​ጋር እንደ ነበረ ዐስብ፤ አሁን ግን እን​ዲሁ እርሱ በዚህ ፈጽሞ ተድ​ላና ደስታ ያደ​ር​ጋል፤ አንተ ግን መከራ ትቀ​በ​ላ​ለህ።


በፊ​ቱም ከአ​ለው መብል ፈን​ታ​ቸ​ውን አቀ​ረ​በ​ላ​ቸው፤ የብ​ን​ያ​ምም ፈንታ ከሁሉ አም​ስት እጅ የሚ​በ​ልጥ ነበረ። እነ​ር​ሱም በሉ፤ ጠጡም፤ ከእ​ር​ሱም ጋር ደስ አላ​ቸው።


እኅቴ ሙሽ​ሪት ሆይ፥ ወደ ገነቴ ገባሁ፥ ከር​ቤ​ዬን ከሽ​ቱዬ ጋር ለቀ​ምሁ፥ እን​ጀ​ራ​ዬን ከማሬ ጋር በላሁ፥ የወ​ይን ጠጄን ከወ​ተቴ ጋር ጠጣሁ። ባል​ን​ጀ​ሮች በሉ፥ ጠገ​ቡም፤ የወ​ን​ድ​ሞች ልጆች ጠጡ፥ ሰከ​ሩም፥ ልባ​ቸው የጠፋ ነውና።


የቀ​ባ​ኋ​ቸ​ውን አት​ዳ​ስሱ፥ በነ​ቢ​ያ​ቴም ላይ ክፉ አታ​ድ​ርጉ።


ባልንጀሮቹን ባሮች ሊመታ ቢጀምር፥ ከሰካሮችም ጋር ቢበላና ቢጠጣ፥


ነገር ግን ያ ክፉ አገ​ል​ጋይ በልቡ፦ ጌታዬ ቶሎ አይ​መ​ጣም ቢል፥ በጌ​ታው ቤት ያሉ​ት​ንም ወን​ዶ​ች​ንና ሴቶ​ችን አገ​ል​ጋ​ዮች ሊደ​በ​ድ​ብና ሊያ​ጕ​ላላ ቢጀ​ምር፥ ከሰ​ካ​ራ​ሞ​ችም ጋር ቢበ​ላና ቢጠጣ፥ ቢሰ​ክ​ርም፥


ለእ​ና​ንተ እንደ መሰ​ላ​ችሁ እነ​ዚህ የሰ​ከሩ አይ​ደ​ሉም፤ ከቀኑ ገና ሦስ​ተኛ ሰዓት ነውና።


ወደ ምግብ ትሽ​ቀ​ዳ​ደ​ማ​ላ​ችሁ፤ የተ​ራቡ በአ​ጠ​ገ​ባ​ችሁ እያሉ እና​ንተ ትበ​ላ​ላ​ችሁ፤ ትጠ​ግ​ባ​ላ​ችሁ፤ ትሰ​ክ​ራ​ላ​ች​ሁም።


መዳ​ራት ነውና ወይን በመ​ጠ​ጣት አት​ስ​ከሩ፤ መን​ፈስ ቅዱ​ስን ተመሉ እንጂ።


የሚያንቀላፉ በሌሊት ያንቀላፋሉና፤ የሚሰክሩም በሌሊት ይሰክራሉና፤


የምድርም ነገሥታት ከእርስዋ ጋር ሴሰኑ፤ በምድርም የሚኖሩ ከዝሙትዋ ወይን ጠጅ ሰከሩ፤” ብሎ ተናገረኝ።


ሴቲቱም በቅዱሳን ደምና በኢየሱስ ምስክሮች ደም ሰክራ አየኋት። ባየኋትም ጊዜ እጅግ ታላቅ ድንቅ አደነቅሁ።


Follow us:

Advertisements


Advertisements