Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




ዮሐንስ 19:41 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

41 በዚ​ያም በተ​ሰ​ቀ​ለ​በት ቦታ የአ​ት​ክ​ልት ስፍራ ነበር፤ በዚያ የአ​ት​ክ​ልት ስፍራ ውስ​ጥም በው​ስጡ ሰው ያል​ተ​ቀ​በ​ረ​በት አዲስ መቃ​ብር ነበር።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

41 ኢየሱስ በተሰቀለበት ቦታም የአትክልት ስፍራ ነበር፤ በአትክልቱም ስፍራ ማንም ያልተቀበረበት አዲስ መቃብር ነበር።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

41 በተሰቀለበትም ስፍራ የአትክልት ቦታ ነበረ፤ በአትክልቱም ቦታ ማንም ገና ያልተቀበረበት አዲስ መቃብር ነበረ።

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

41 ኢየሱስ ተሰቅሎ በነበረበት ቦታ አንድ የአትክልት ስፍራ ነበረ፤ በዚያም የአትክልት ስፍራ ውስጥ ማንም ያልተቀበረበት አዲስ መቃብር ነበር።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

41 በተሰቀለበትም ስፍራ አትክልት ነበረ፥ በአትክልቱም ማንም ገና ያልተቀበረበት አዲስ መቃብር ነበረ።

See the chapter Copy




ዮሐንስ 19:41
7 Cross References  

ሥጋ​ው​ንም አው​ርዶ በበ​ፍታ ገነ​ዘው፤ ማንም ባል​ተ​ቀ​በ​ረ​በት፥ ከድ​ን​ጋ​ይም በተ​ፈ​ለ​ፈለ መቃ​ብር ቀበ​ረው፤ ታላቅ ድን​ጋ​ይም አን​ከ​ባ​ልሎ መቃ​ብ​ሩን ገጥሞ ሄደ።


ከዐለት በወቀረው በአዲሱ መቃብርም አኖረው፤ በመቃብሩም ደጃፍ ታላቅ ድንጋይ አንከባሎ ሄደ።


ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም፥ “አንቺ ሴት፥ ምን ያስ​ለ​ቅ​ስ​ሻል? ማን​ንስ ትሺ​ያ​ለሽ?” አላት፤ እር​ስዋ ግን የአ​ት​ክ​ልት ቦታ ጠባቂ መስ​ሎ​አት፥ “ጌታዬ፥ አንተ ወስ​ደ​ኸው እንደ ሆነ ሄጄ ወደ እኔ እን​ዳ​መ​ጣ​ውና ሽቱ እን​ድ​ቀ​ባው ወዴት እንደ አኖ​ር​ኸው ንገ​ረኝ” አለ​ችው።


መቃ​ብር በዚያ ያስ​ወ​ቀ​ርህ፥ ከፍ ባለው ስፍራ መቃ​ብር ያሠ​ራህ፥ በድ​ን​ጋ​ይም ውስጥ ለራ​ስህ መኖ​ርያ ያሳ​ነ​ጽህ ወደ​ዚህ ለምን መጣህ? ለም​ንስ በዚህ ተደ​ፋ​ፈ​ርህ?


አገ​ል​ጋ​ዮ​ቹም በድ​ኑን በሰ​ረ​ገ​ላው አድ​ር​ገው ከመ​ጊዶ ወደ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም አመ​ጡት፤ በመ​ቃ​ብ​ሩም ቀበ​ሩት። የሀ​ገ​ሩም ሰዎች የኢ​ዮ​ስ​ያ​ስን ልጅ ዮአ​ክ​ስን ወሰ​ዱት። ቀብ​ተ​ውም በአ​ባቱ ፋንታ አነ​ገ​ሡት።


ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስ​ንም በዚያ ቀበ​ሩት፤ ለአ​ይ​ሁድ የመ​ሰ​ና​ዳት ቀን ነበ​ርና፤ መቃ​ብ​ሩም ለሰ​ቀ​ሉ​በት ቦታ ቅርብ ነበር።


Follow us:

Advertisements


Advertisements