Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




ዮሐንስ 18:22 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

22 ይህ​ንም ባለ​ጊዜ ከቆ​ሙት ሎሌ​ዎች አንዱ፥ “ለሊቀ ካህ​ናቱ እን​ዲህ ትመ​ል​ስ​ለ​ታ​ለ​ህን?” ብሎ ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስን በጥፊ መታው።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

22 ኢየሱስ ይህን በተናገረ ጊዜ፣ አጠገቡ ቆመው ከነበሩት ጠባቂዎች አንዱ፣ “ለሊቀ ካህናቱ የምትመልሰው እንዲህ ነውን?” ብሎ በጥፊ መታው።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

22 ይህንን ባለ ጊዜ በዚያ ቆመው ከነበሩት ሎሌዎች አንዱ “ለሊቀ ካህናቱ እንዲህ ትመልሳለህን?” ብሎ ኢየሱስን በጥፊ መታው።

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

22 ኢየሱስ ይህን በተናገረ ጊዜ እዚያ ቆመው ከነበሩት የዘብ ኀላፊዎች አንዱ፥ “ለካህናት አለቃው የምትመልሰው እንዲህ ነውን?” ብሎ ኢየሱስን በጥፊ መታው።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

22 ይህንም ሲል በዚያ ቆሞ የነበረው ከሎሌዎች አንዱ፦ “ለሊቀ ካህናቱ እንዲህ ትመልሳለህን?” ብሎ ኢየሱስን በጥፊ መታው።

See the chapter Copy




ዮሐንስ 18:22
12 Cross References  

ወደ እር​ሱም እየ​መጡ፥ “የአ​ይ​ሁድ ንጉሥ ሆይ፥ ሰላም ለአ​ንተ ይሁን” ይሉት ነበር፤ በጥ​ፊም ይመ​ቱት ነበር።


አንዳንዶችም ይተፉበት ፊቱንም ሸፍነው ይጐስሙትና “ትንቢት ተናገር፤” ይሉት ጀመር፤ ሎሌዎችም በጥፊ እየመቱ ወሰዱት።


ይሁ​ዳም ከካ​ህ​ናት አለ​ቆ​ችና ከፈ​ሪ​ሳ​ው​ያን ወታ​ደ​ሮ​ችን ተቀ​በለ፤ ሎሌ​ዎ​ቻ​ቸ​ው​ንም በረ​ዳ​ት​ነት ወሰደ፤ ፋኖ​ስና የችቦ መብ​ራት፥ የጦር መሣ​ሪ​ያም ይዞ ወደ​ዚያ ሄደ።


የጭፍሮች ሴት ልጅ ሆይ፥ ጭፍሮችሽን አሁን ሰብስቢ፥ ከብቦ አስጨንቆናል፥ የእስራኤልን ፈራጅ ጕንጩን በበትር ይመታሉ።


ጳስ​ኮ​ርም ነቢ​ዩን ኤር​ም​ያ​ስን ገረ​ፈው፤ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ቤት በነ​በ​ረው በላ​ይ​ኛው በብ​ን​ያም በር ባለው አዘ​ቅት ውስጥ ጣለው።


በቍ​ጣው ጣለኝ፤ ጥር​ሶ​ቹ​ንም አፋ​ጨ​ብኝ፤ ፍላ​ጻ​ዎ​ቹ​ንም በእኔ ላይ ፈተነ።


እን​ግ​ዲህ እኔን ለምን ትጠ​ይ​ቀ​ኛ​ለህ? የተ​ና​ገ​ር​ሁ​ትን የሰ​ሙ​ኝን ጠይ​ቃ​ቸው፤ እኔም የተ​ና​ገ​ር​ሁ​ትን እነሆ፥ እነ​ርሱ ያው​ቃሉ።”


Follow us:

Advertisements


Advertisements