Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




ዮሐንስ 16:16 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

16 “ጥቂት ጊዜ አለ፤ አታ​ዩ​ኝ​ምም፤ ደግ​ሞም ጥቂት ጊዜ አለ፤ እን​ደ​ገ​ናም ታዩ​ኛ​ላ​ችሁ፤ ወደ አብ እሄ​ዳ​ለ​ሁና።”

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

16 “ከጥቂት ጊዜ በኋላ አታዩኝም፤ ይሁን እንጂ ከጥቂት ጊዜ በኋላ ደግሞ ታዩኛላችሁ።”

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

16 “ከጥቂት ጊዜ በኋላ አታዩኝም፤ ከጥቂት ጊዜ በኋላ ደግሞ ታዩኛላችሁ፤ እኔ ወደ አብ እሄዳለሁና።”

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

16 “ከጥቂት ጊዜ በኋላ አታዩኝም፤ እንደገናም ከጥቂት ጊዜ በኋላ ታዩኛላችሁ።”

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

16 ጥቂት ጊዜ አለ፥ አታዩኝምም፤ ደሞም ጥቂት ጊዜ አለ፥ ታዩኛላችሁም፥ እኔ ወደ አብ እሄዳለሁና።”

See the chapter Copy




ዮሐንስ 16:16
19 Cross References  

ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም እን​ዲህ አላ​ቸው፥ “ጥቂት ቀን አብ​ሬ​አ​ችሁ እኖ​ራ​ለሁ፤ ከዚ​ህም በኋላ ወደ ላከኝ እሄ​ዳ​ለሁ።


ሕማ​ማ​ትን ከተ​ቀ​በለ በኋላ ብዙ ተአ​ም​ራት በማ​ሳ​የት አርባ ቀን ሙሉ እየ​ተ​ገ​ለ​ጠ​ላ​ቸው፥ ስለ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መን​ግ​ሥ​ትም እየ​ነ​ገ​ራ​ቸ​ውና እያ​ስ​ተ​ማ​ራ​ቸው ሕያው ሆኖ ራሱ​ን​ገ​ለ​ጠ​ላ​ቸው።


ከአብ ወጣሁ፤ ወደ ዓለ​ምም መጣሁ፤ ዳግ​መ​ኛም ዓለ​ምን እተ​ወ​ዋ​ለሁ፤ ወደ አብም እሄ​ዳ​ለሁ።”


እና​ን​ተም ዛሬ ታዝ​ና​ላ​ችሁ፤ እን​ደ​ገ​ናም አያ​ች​ኋ​ለሁ፤ ልባ​ች​ሁም ደስ ይለ​ዋል፤ ደስ​ታ​ች​ሁ​ንም የሚ​ወ​ስ​ድ​ባ​ችሁ የለም።


የእ​ም​ነ​ታ​ች​ን​ንም ራስና ፈጻ​ሚ​ውን ኢየ​ሱ​ስን እን​ከ​ተ​ለው፤ እርሱ ነው​ርን ንቆ፥ በፊ​ቱም ስላ​ለው ደስታ በመ​ስ​ቀል ታግሦ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዙፋን ቀኝ ተቀ​ም​ጦ​አ​ልና።


ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም፥ አብ ሁሉን በእጁ እንደ ሰጠው፥ ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እንደ ወጣ፥ ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም እን​ደ​ሚ​ሄድ ባወቀ ጊዜ፥


አሁን ግን ወደ ላከኝ ወደ አብ እሄ​ዳ​ለሁ፤ ከእ​ና​ንተ አንዱ እንኳ፦ ‘ወዴት ትሄ​ዳ​ለህ?’ ብሎ አይ​ጠ​ይ​ቀ​ኝም።


ልጆች ሆይ፥ ገና ጥቂት ጊዜ ከእ​ና​ንተ ጋር አለሁ፤ ትሹ​ኛ​ላ​ችሁ፤ ለአ​ይ​ሁ​ድም እኔ ወደ​ም​ሄ​ድ​በት እና​ንተ መም​ጣት አይ​ቻ​ላ​ች​ሁም እን​ዳ​ል​ኋ​ቸው፥ አሁ​ንም ለእ​ና​ንተ እነ​ግ​ራ​ች​ኋ​ለሁ።


ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም እን​ዲህ አላ​ቸው፥ “ ገና ለጥ​ቂት ጊዜ ብር​ሃን ከእ​ና​ንተ ጋር ነው፤ በጨ​ለማ የሚ​መ​ላ​ለስ የሚ​ሄ​ድ​በ​ትን አያ​ው​ቅ​ምና ጨለማ እን​ዳ​ያ​ገ​ኛ​ችሁ ብር​ሃን ሳለ​ላ​ችሁ ተመ​ላ​ለሱ፤


ጌታ ኢየሱስም ከእነርሱ ጋር ከተናገረ በኋላ ወደ ሰማይ ዐረገ፤ በእግዚአብሔርም ቀኝ ተቀመጠ።


አሁን ግን ወደ አንተ እመ​ጣ​ለሁ፤ በእ​ነ​ር​ሱም ደስ​ታዬ ፍጹም ይሆን ዘንድ ይህን በዓ​ለም እና​ገ​ራ​ለሁ።


አሁ​ንም አባት ሆይ፥ ዓለም ሳይ​ፈ​ጠር ከአ​ንተ ጋር በነ​በ​ረኝ ክብር በአ​ንተ ዘንድ አክ​ብ​ረኝ።


ስለ ጽድቅ፥ እኔ ወደ አብ እሄ​ዳ​ለ​ሁና፥ እን​ግ​ዲህ ወዲ​ህም አታ​ዩ​ኝ​ምና ነው።


Follow us:

Advertisements


Advertisements