Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




ዮሐንስ 15:22 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

22 ባል​መ​ጣ​ሁና ባል​ነ​ገ​ር​ኋ​ቸ​ውስ ኖሮ ኀጢ​አት ባል​ሆ​ነ​ባ​ቸ​ውም ነበር፤ አሁን ግን ለኀ​ጢ​አ​ታ​ቸው ምክ​ን​ያት የላ​ቸ​ውም።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

22 መጥቼ ባልነግራቸው ኖሮ ኀጢአት ባልሆነባቸው ነበር፤ አሁን ግን ለኀጢአታቸው የሚሰጡት ምክንያት የላቸውም።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

22 እኔ መጥቼ ባልነገራቸው ኖሮ ኃጢአት ባልሆነባቸውም ነበር፤ አሁን ግን ለኀጢአታቸው ሰበብ የላቸውም።

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

22 እኔ መጥቼ ባልነግራቸው ኖሮ ኃጢአት ባልሆነባቸውም ነበር፤ አሁን ግን ለኃጢአታቸው ምክንያት የላቸውም።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

22 እኔ መጥቼ ባልነገርኋቸውስ ኃጢአት ባልሆነባቸውም ነበር፤ አሁን ግን ለኃጢአታቸው ምክንያት የላቸውም።

See the chapter Copy




ዮሐንስ 15:22
17 Cross References  

ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም፥ “ዕዉ​ሮ​ችስ ብት​ሆኑ ኀጢ​ኣት ባል​ሆ​ነ​ባ​ች​ሁም ነበር፤ አሁን ግን እና​ያ​ለን ትላ​ላ​ችሁ፤ አታ​ዩ​ምም፤ ስለ​ዚ​ህም ኀጢ​ኣ​ታ​ችሁ ጸንቶ ይኖ​ራል” አላ​ቸው።


እንግዲህ በጎ ለማድረግ አውቆ ለማይሠራው ኀጢአት ነው።


የቀ​ድ​ሞ​ው​ንስ ያለ ማወቅ ዘመን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አሳ​ል​ፎ​ታል፤ ዛሬ ግን በመ​ላው ዓለም ንስሓ እን​ዲ​ገቡ ሰውን ሁሉ አዝ​ዞ​አል።


የማ​ይ​ታ​የው የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ባሕ​ርይ እር​ሱም የዘ​ለ​ዓ​ለም ኀይ​ሉና ጌት​ነቱ ከዓ​ለም ፍጥ​ረት ጀምሮ የፈ​ጠ​ረ​ውን ፍጥ​ረት በማ​ሰ​ብና በመ​መ​ር​መር ይታ​ወ​ቃል፤ መልስ የሚ​ሰ​ጡ​በ​ትን ምክ​ን​ያት እን​ዳ​ያ​ገኙ።


የሚ​ክ​ደ​ኝን፥ ቃሌ​ንም የማ​ይ​ቀ​በ​ለ​ውን ግን የሚ​ፈ​ር​ድ​በት አለ፤ እኔ የተ​ና​ገ​ር​ሁት ቃል እርሱ በመ​ጨ​ረ​ሻ​ዪቱ ቀን ይፈ​ር​ድ​በ​ታል።


አርነት ወጥታችሁ እንደ እግዚአብሔር ባሪያዎች ሁኑ እንጂ ያ አርነት ለክፋት መሸፈኛ እንዲሆን አታድርጉ።


አንተ ሰው ሆይ፥ እው​ነት ለሚ​ፈ​ር​ደው ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ምን ትመ​ል​ስ​ለ​ታ​ለህ? በወ​ን​ድ​ምህ ላይ የም​ት​ጠ​ላ​ውን ያን ሥራ አንተ ራስህ ከሠ​ራ​ኸው በራ​ስህ የም​ት​ፈ​ርድ አይ​ደ​ለ​ምን? አንተ ራስህ ያን ሥራ ትሠ​ራ​ዋ​ለ​ህና።


የዚያ አገ​ል​ጋይ ጌታ ባል​ጠ​ረ​ጠ​ረው ዕለት፥ ባላ​ወ​ቀ​ውም ሰዓት መጥቶ ከሁ​ለት ይሰ​ነ​ጥ​ቀ​ዋል፤ ዕድ​ሉ​ንም ከማ​ይ​ታ​መኑ ጋር ያደ​ር​ገ​ዋል።


“እነ​ርሱ ዐመ​ፀኛ ቤት ናቸ​ውና ቢሰሙ ወይም ቢፈሩ አንተ በመ​ካ​ከ​ላ​ቸው ነቢይ እንደ ሆንህ ያው​ቃሉ።


ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም፥ “ከሰ​ማይ ካል​ተ​ሰ​ጠህ በቀር በእኔ ላይ አን​ዳች ሥል​ጣን የለ​ህም፤ ስለ​ዚህ ለአ​ንተ አሳ​ልፎ የሰ​ጠኝ ሰው ታላቅ ኀጢ​ኣት አለ​በት” አለው።


እኔን የሚ​ጠላ አባ​ቴን ይጠ​ላል።


ሌላ ያል​ሠ​ራ​ውን ሥራ በመ​ካ​ከ​ላ​ቸው ባል​ሠራ ኖሮ ኀጢ​አት ባል​ሆ​ነ​ባ​ቸ​ውም ነበር፤ አሁን ግን እኔ​ንም አባ​ቴ​ንም አይ​ተ​ዋል፤ ጠል​ተ​ው​ማል።


ስለ ኀጢ​ኣት፥ በእኔ አላ​መ​ኑ​ምና ነው፤


Follow us:

Advertisements


Advertisements