Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




ዮሐንስ 13:21 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

21 ይህ​ንም ተና​ግሮ ጌታ​ችን ኢየ​ሱስ በልቡ አዘነ፤ መሰ​ከረ፤ እን​ዲ​ህም አለ፥ “እው​ነት እው​ነት እላ​ች​ኋ​ለሁ፤ ከእ​ና​ንተ አንዱ አሳ​ልፎ ይሰ​ጠ​ኛል።”

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

21 ይህን ካለ በኋላም ኢየሱስ በመንፈሱ ታውኮ፤ “እውነት እላችኋለሁ፤ ከእናንተ አንዱ አሳልፎ ይሰጠኛል” ሲል መሰከረ።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

21 ኢየሱስ ይህን ብሎ በመንፈሱ ተረበሸ፤ እንዲህም ሲል መሰከረ፦ “እውነት እውነት እላችኋለሁ፤ ከእናንተ አንዱ አሳልፎ ይሰጠኛል” አለ።

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

21 ኢየሱስ ይህን ካለ በኋላ በመንፈሱ ተጨነቀና “እውነት፥ እውነት እላችኋለሁ፤ ከእናንተ አንዱ አሳልፎ ይሰጠኛል” ሲል ገልጦ ተናገረ።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

21 ኢየሱስ ይህን ብሎ በመንፈሱ ታወከ መስክሮም፦ “እውነት እውነት እላችኋለሁ፥ ከእናንተ አንዱ አሳልፎ ይሰጠኛል” አለ።

See the chapter Copy




ዮሐንስ 13:21
17 Cross References  

ሲበሉም “እውነት እላችኋለሁ፤ ከእናንተ አንዱ እኔን አሳልፎ ይሰጣል፤” አለ።


ነገር ግን ይህን የም​ና​ገር ስለ ሁላ​ችሁ አይ​ደ​ለም፤ የመ​ረ​ጥ​ኋ​ቸው እነ​ማን እንደ ሆኑ እኔ አው​ቃ​ለሁ፤ ነገር ግን መጽ​ሐፍ ‘እን​ጀ​ራ​ዬን የሚ​መ​ገብ ተረ​ከ​ዙን በእኔ ላይ አነሣ’ ያለው ይፈ​ጸም ዘንድ ነው።


ተቀምጠውም ሲበሉ ኢየሱስ “እውነት እላችኋለሁ፥ ከእናንተ አንዱ፥ እርሱም ከእኔ ጋር የሚበላው አሳልፎ ይሰጠኛል፤” አለ።


“አሁ​ንስ ነፍሴ ታወ​ከች፤ ግን ምን እላ​ለሁ? አባት ሆይ፥ ከዚች ሰዓት ነፍ​ሴን አድ​ናት፤ ነገር ግን ስለ​ዚህ ነገር ለዚች ሰዓት ደር​ሻ​ለሁ።


ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም እር​ስዋ ስታ​ለ​ቅስ፥ ከእ​ር​ስዋ ጋር የመጡ አይ​ሁ​ድም ሲያ​ለ​ቅሱ ባየ ጊዜ በልቡ አዘነ፤ በራ​ሱም ታወከ።


ከእኛ ዘንድ ወጡ፥ ዳሩ ግን ከእኛ ወገን አልነበሩም፤ ከእኛ ወገንስ ቢሆኑ ከእኛ ጋር ጸንተው በኖሩ ነበር፤ ነገር ግን ሁሉ ከእኛ ወገን እንዳልሆኑ ይገለጡ ዘንድ ወጡ።


ጳው​ሎ​ስም በአ​ቴና ሆኖ ሲጠ​ብ​ቃ​ቸው ከተ​ማው ሁሉ ጣዖት ሲያ​መ​ልኩ ባየ ጊዜ ልቡ​ናው ተበ​ሳጨ።


ራት ሲበ​ሉም አሳ​ልፎ ይሰ​ጠው ዘንድ በስ​ም​ዖን ልጅ በአ​ስ​ቆ​ሮቱ ሰው በይ​ሁዳ ልብ ሰይ​ጣን አደረ።


ዳግ​መ​ኛም ጌታ​ችን ኢየ​ሱስ በልቡ አዘነ፤ ወደ መቃ​ብ​ሩም ሄደ፤ መቃ​ብ​ሩም ዋሻ ነበር፤ በላ​ዩም ታላቅ ድን​ጋይ ተገ​ጥ​ሞ​በት ነበር።


ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም እን​ባ​ውን አፈ​ሰሰ።


ስለ ልባቸውም ድንዛዜ አዝኖ ዙሪያውን እየተመለከተ በቍጣ አያቸው፤ ሰውየውንም “እጅህን ዘርጋ፤” አለው። ዘረጋትም፤ እጁም ዳነች።


“ነፍሴ እስከ ሞት ድረስ እጅግ አዘነች፤ በዚህ ቆዩ፤ ከእኔም ጋር ትጉ፤” አላቸው።


ደቀ መዛ​ሙ​ር​ቱም ይህን ስለ ማን እንደ ተና​ገረ ተጠ​ራ​ጥ​ረው እርስ በር​ሳ​ቸው ተያዩ፤


Follow us:

Advertisements


Advertisements