Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




ዮሐንስ 12:21 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

21 እነ​ር​ሱም ከገ​ሊላ፥ የቤተ ሳይዳ ሰው ወደ ሆነው ወደ ፊል​ጶስ ሄደው፥ “አቤቱ፥ ጌታ ኢየ​ሱ​ስን ልና​የው እን​ወ​ድ​ዳ​ለን” ብለው ለመ​ኑት።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

21 እነርሱም በገሊላ ከምትገኘው ከቤተ ሳይዳ ወደ ሆነው ሰው፣ ወደ ፊልጶስ መጥተው፣ “ጌታ ሆይ፤ እባክህን ኢየሱስን ለማየት እንፈልጋለን” አሉት።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

21 እነርሱም ከገሊላ ቤተሳይዳ ወደሚሆን ወደ ፊልጶስ መጥተው “ጌታ ሆይ! ኢየሱስን ልናይ እንወዳለን፤” ብለው ለመኑት።

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

21 እነርሱም ከገሊላ የቤተ ሳይዳ ሰው ወደ ሆነው ወደ ፊልጶስ ቀርበው፥ “ጌታዬ ሆይ፥ ኢየሱስን ማየት እንፈልጋለን” አሉት።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

21 እነርሱም ከገሊላ ቤተ ሳይዳ ወደሚሆን ወደ ፊልጶስ መጥተው፦ “ጌታ ሆይ፥ ኢየሱስን ልናይ እንወዳለን” ብለው ለመኑት።

See the chapter Copy




ዮሐንስ 12:21
13 Cross References  

የአ​ባቴ ፈቃዱ ይህ ነው፤ ወል​ድን አይቶ የሚ​ያ​ም​ን​በት ሁሉ የዘ​ለ​ዓ​ለም ሕይ​ወ​ትን እን​ዲ​ያ​ገኝ ነው፤ እኔም በመ​ጨ​ረ​ሻ​ዪቱ ቀን አስ​ነ​ሣ​ዋ​ለሁ።”


“ወዮልሽ ኮራዚ! ወዮልሽ ቤተ ሳይዳ! በእናንተ የተደረገው ተአምራት በጢሮስና በሲዶና ተደርጎ ቢሆን፥ ማቅ ለብሰው አመድም ነስንሰው ከብዙ ጊዜ በፊት ንስሐ በገቡ ነበርና።


ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም ናት​ና​ኤ​ልን ወደ እርሱ ሲመጣ ባየው ጊዜ ስለ እርሱ “እነሆ፥ በልቡ ተን​ኰል የሌ​ለ​በት እው​ነ​ተኛ እስ​ራ​ኤ​ላዊ ይህ ነው” አለ።


Follow us:

Advertisements


Advertisements