Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




ዮሐንስ 11:54 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

54 ከዚ​ያም ወዲያ ጌታ​ችን ኢየ​ሱስ በአ​ይ​ሁድ መካ​ከል በግ​ልጥ አል​ተ​መ​ላ​ለ​ሰም፤ ነገር ግን ለም​ድረ በዳ አቅ​ራ​ቢያ ወደ ሆነች ምድር፥ ኤፍ​ሬም ወደ​ም​ት​ባል ከተማ ሄደ፤ በዚ​ያም ከደቀ መዛ​ሙ​ርቱ ጋር ተቀ​መጠ።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

54 ስለዚህ ኢየሱስ ከዚያ ወዲያ በአይሁድ መካከል በይፋ አልተመላለሰም፤ ነገር ግን በምድረ በዳ አጠገብ ወደምትገኝ ኤፍሬም ወደ ተባለች መንደር ገለል አለ፤ በዚያም ከደቀ መዛሙርቱ ጋራ ሰነበተ።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

54 ከዚያ ወዲያም ኢየሱስ በአይሁድ መካከል ተገልጦ አልተመላለሰም፤ ነገር ግን ከዚያ በምድረ በዳ አጠገብ ወዳለች ምድር፥ ኤፍሬም ወደምትባል ከተማ ሄደ፤ በዚያም ከደቀ መዛሙርቱ ጋር ተቀመጠ።

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

54 ከዚያን ወዲያ ኢየሱስ በአይሁድ መካከል በግልጥ አልተመላለሰም፤ ነገር ግን ከዚያ ወጥቶ በበረሓ አጠገብ ወዳለችው ኤፍሬም ወደምትባለው ከተማ ሄደ፤ እዚያ ከደቀ መዛሙርቱ ጋር ቈየ።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

54 ከዚያ ወዲያም ኢየሱስ በአይሁድ መካከል ተገልጦ አልተመላለሰም፤ ነገር ግን ከዚያ በምድረ በዳ አጠገብ ወዳለች ምድር፥ ኤፍሬም ወደምትባል ከተማ ሄደ፤ በዚያም ከደቀ መዛሙርቱ ጋር ተቀመጠ።

See the chapter Copy




ዮሐንስ 11:54
9 Cross References  

ከዚህ በኋ​ላም ጌታ​ችን ኢየ​ሱስ በገ​ሊላ ይመ​ላ​ለስ ነበረ፤ ወደ ይሁዳ ምድ​ርም ሊሄድ አል​ወ​ደ​ደም፤ አይ​ሁድ ሊገ​ድ​ሉት ይሹ ነበ​ርና።


ሊገ​ለጥ ወድዶ ሳለ በስ​ውር አን​ዳች ነገር የሚ​ያ​ደ​ርግ ማንም የለ​ምና፤ አንተ ግን ይህን የም​ታ​ደ​ርግ ከሆነ ራስ​ህን ለዓ​ለም ግለጥ።


አብ​ያም ኢዮ​ር​ብ​ዓ​ምን ተከ​ትሎ አሳ​ደ​ደው፤ ከእ​ር​ሱም ከተ​ሞ​ቹን ቤቴ​ል​ንና መን​ደ​ሮ​ች​ዋን፥ ይሳ​ና​ንና መን​ደ​ሮ​ች​ዋን፥ ዔፍ​ሮ​ን​ንና መን​ደ​ሮ​ች​ዋን ወሰደ።


ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም መልሶ እን​ዲህ አለው፥ “እኔ ለዓ​ለም በግ​ልጥ ተና​ገ​ርሁ፤ አይ​ሁድ ሁሉ በሚ​ሰ​በ​ሰ​ቡ​በት በም​ኵ​ራ​ብም፥ በቤተ መቅ​ደ​ስም ሁል​ጊዜ አስ​ተ​ማ​ርሁ፤ በስ​ው​ርም የተ​ና​ገ​ር​ሁት አን​ዳች ነገር የለም።


ዳግ​መ​ኛም ቀድሞ ዮሐ​ንስ ያጠ​ም​ቅ​በት ወደ ነበ​ረው ስፍራ ወደ ዮር​ዳ​ኖስ ማዶ ሄደ፤ በዚ​ያም ተቀ​መጠ።


ነገር ግን፥ አይ​ሁ​ድን በመ​ፍ​ራት የእ​ር​ሱን ነገር ገልጦ የተ​ና​ገረ አል​ነ​በ​ረም።


ወን​ድ​ሞቹ ለበ​ዓል ከወጡ በኋላ፥ እር​ሱም ያን​ጊዜ በግ​ልጥ ሳይ​ሆን ተሰ​ውሮ ወጣ።


ከሁ​ለት ዓመ​ትም በኋላ አቤ​ሴ​ሎም በኤ​ፍ​ሬም አቅ​ራ​ቢያ ባለ​ችው በቤ​ላ​ሶር በጎ​ቹን በሚ​ያ​ሸ​ል​ት​በት ጊዜ አቤ​ሴ​ሎም የን​ጉ​ሡን ልጆች ሁሉ ጠራ።


Follow us:

Advertisements


Advertisements