Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




ዮሐንስ 11:11 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

11 ይህ​ንም ለደቀ መዛ​ሙ​ርቱ ነገ​ራ​ቸው፤ ከዚ​ህም በኋላ፥ “ወዳ​ጃ​ችን አል​ዓ​ዛር ተኝ​ቶ​አል፤ ነገር ግን ላነ​ቃው እሄ​ዳ​ለሁ” አላ​ቸው።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

11 ይህን ከነገራቸው በኋላ፣ “ወዳጃችን አልዓዛር ተኝቷል፤ እኔም ከእንቅልፉ ላስነሣው እሄዳለሁ” አላቸው።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

11 ይህንንም ከተናገረ በኋላ “ወዳጃችን አልዓዛር ተኝቶአል፤ ነገር ግን ከእንቅልፉ ላስነሣው እሄዳለሁ፤” አላቸው።

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

11 ኢየሱስ ይህን ካላቸው በኋላ፥ “ወዳጃችን አልዓዛር አንቀላፍቶአል፤ እኔ ግን ከእንቅልፉ ላስነሣው እሄዳለሁ” አለ።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

11 ከዚህም በኋላ፦ “ወዳጃችን አልዓዛር ተኝቶአል፤ ነገር ግን ከእንቅልፉ ላስነሣው እሄዳለሁ” አላቸው።

See the chapter Copy




ዮሐንስ 11:11
25 Cross References  

ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም ስለ ሞቱ ተና​ገረ፤ እነ​ርሱ ግን ስለ እን​ቅ​ልፍ መተ​ኛት መስ​ሎ​አ​ቸው ነበር።


የምንነቃም ብንሆን፥ የምናንቀላፋም ብንሆን፥ ከእርሱ ጋር አብረን በሕይወት እንኖር ዘንድ ስለ እኛ ሞተ።


እነሆ፥ አንድ ምሥ​ጢ​ርን እነ​ግ​ራ​ች​ኋ​ለሁ፥ ሁላ​ችን የም​ን​ሞት አይ​ደ​ለም።


በጕ​ል​በ​ቱም ተን​በ​ር​ክኮ፥ “አቤቱ፥ ይህን ኀጢ​አት አት​ቍ​ጠ​ር​ባ​ቸው” ብሎ በታ​ላቅ ድምፅ ጮኸ። ይህ​ንም ብሎ ሞተ፤ ሳው​ልም በእ​ስ​ጢ​ፋ​ኖስ ሞት ተባ​ባሪ ነበር።


መቃብሮችም ተከፈቱ፤ ተኝተው ከነበሩትም ከቅዱሳን ብዙ ሥጋዎች ተነሡ፤


“የተ​ኛህ ንቃ ከሙ​ታ​ንም ተለ​ይ​ተህ ተነሥ፤ ክር​ስ​ቶ​ስም ያበ​ራ​ል​ሃል” ብሎ​አ​ልና።


ገብቶም “ስለ ምን ትንጫጫላችሁ? ታለቅሳላችሁም? ብላቴናይቱ ተኝታለች እንጂ አልሞተችም፤” አላቸው።


“ብላቴናይቱ ተኝታለች እንጂ አልሞተችምና ፈቀቅ በሉ፤” አላቸው። በጣምም ሳቁበት።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም፥ ሰው ከባ​ል​ን​ጀ​ራው ጋር እን​ደ​ሚ​ነ​ጋ​ገር ፊት ለፊት ከሙሴ ጋር ይነ​ጋ​ገር ነበር። ሙሴም ወደ ሰፈሩ ይመ​ለስ ነበር፤ ነገር ግን አገ​ል​ጋዩ ብላ​ቴና የነዌ ልጅ ኢያሱ ከድ​ን​ኳኑ አይ​ወ​ጣም ነበር።


መጽሐፍም “አብርሃምም እግዚአብሔርን አመነ፤ ጽድቅም ሆኖ ተቈጠረለት፤” ያለው ተፈጸመ፤ የእግዚአብሔርም ወዳጅ ተባለ።


ለጽ​ድቅ ትጉ፤ አት​ሳቱ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን የማ​ያ​ው​ቁት ሰዎች አሉና፤ ነገር ግን እን​ድ​ታ​ፍሩ ይህን እላ​ች​ኋ​ለሁ፤


እን​ግ​ዲ​ያስ በክ​ር​ስ​ቶስ አም​ነው የሞቱ ጠፍ​ተ​ዋላ።


እኅ​ቶ​ቹም፥ “ጌታ​ችን ሆይ፥ እነሆ፥ የም​ት​ወ​ደው ታሞ​አል” ብለው ወደ ጌታ​ችን ኢየ​ሱስ ላኩ።


ሙሽራ ያለ​ችው ሙሽራ ነው፤ ቆሞ የሚ​ሰ​ማው የሙ​ሽ​ራው ሚዜ ግን በሙ​ሽ​ራው ቃል እጅግ ደስ ይለ​ዋል፤ የእኔ ደስታ አሁን ተፈ​ጸ​መች።


ባሪ​ያዬ እስ​ራ​ኤል፥ የመ​ረ​ጥ​ሁህ ያዕ​ቆብ፥ የወ​ዳጄ የአ​ብ​ር​ሃም ዘር ሆይ፥


አም​ላ​ካ​ችን ሆይ፥ በዚህ ምድር የነ​በ​ሩ​ትን አሕ​ዛብ ከሕ​ዝ​ብህ ከእ​ስ​ራ​ኤል ፊት ያሳ​ደ​ድህ፥ ለወ​ዳ​ጅ​ህም ለአ​ብ​ር​ሃም ዘር ለዘ​ለ​ዓ​ለም የሰ​ጠ​ሃት አንተ አይ​ደ​ለ​ህ​ምን?


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሙሴን አለው፥ “እነሆ፥ ከአ​ባ​ቶ​ችህ ጋር ታን​ቀ​ላ​ፋ​ለህ፤ ይህም ሕዝብ ይነ​ሣል፤ ይቀ​መ​ጥ​ባ​ትም ዘንድ በሚ​ሄ​ድ​ባት ምድር መካ​ከል ያሉ​ትን ሌሎ​ችን አማ​ል​ክት ተከ​ትሎ ያመ​ነ​ዝ​ራል፤ እኔ​ንም ይተ​ወ​ኛል፤ ከእ​ነ​ር​ሱም ጋር ያደ​ረ​ግ​ሁ​ትን ቃል ኪዳን ያፈ​ር​ሳሉ።


ግያ​ዝም በፊ​ታ​ቸው ይሄድ ነበር፤ ግያ​ዝም ቀድ​ሞ​አ​ቸው ደረሰ፤ በት​ሩ​ንም በሕ​ፃኑ ፊት ላይ አኖ​ረው፤ ነገር ግን ድምፅ ወይም መስ​ማት አል​ነ​በ​ረም፤ እር​ሱ​ንም ሊገ​ና​ኘው ተመ​ልሶ፥ “ሕፃኑ አል​ተ​ነ​ሣም” ብሎ ነገ​ረው።


በሌ​ሊት የሚ​ሄድ ግን ይሰ​ነ​ካ​ከ​ላል፤ በው​ስጡ የሚ​ያ​የው ብር​ሃን የለ​ምና።”


ደቀ መዛ​ሙ​ር​ቱም፥ “አቤቱ፥ ከተ​ኛስ ይነ​ቃል፤ ይድ​ና​ልም” አሉት።


Follow us:

Advertisements


Advertisements