Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




ዮሐንስ 10:29 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

29 እነ​ር​ሱን የሰ​ጠኝ አባቴ እርሱ ከሁሉ ይበ​ል​ጣ​ልና፤ ከአ​ባ​ቴም እጅ መን​ጠቅ የሚ​ችል የለም።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

29 እነርሱን የሰጠኝ አባቴ ከሁሉ ይበልጣል፤ ከአባቴም እጅ ማንም ሊነጥቃቸው አይችልም።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

29 የሰጠኝ አባቴ ከሁሉ ይበልጣል፤ ከአባቴም እጅ ሊነጥቃቸው ማንም አይችልም።

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

29 እነርሱን ለእኔ የሰጠኝ አባቴ ከሁሉ ይበልጣል። ከአባቴ እጅ እነርሱን ነጥቆ መውሰድ የሚችል ማንም የለም።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

29 የሰጠኝ አባቴ ከሁሉ ይበልጣል፥ ከአባቴም እጅ ሊነጥቃቸው ማንም አይችልም።

See the chapter Copy




ዮሐንስ 10:29
12 Cross References  

አብ የሚ​ሰ​ጠኝ ሁሉ ወደ እኔ ይመ​ጣል፤ ወደ እኔ የሚ​መ​ጣ​ው​ንም ከቶ ወደ ውጭ አላ​ወ​ጣ​ውም።


እኔ ስለ እነ​ርሱ እለ​ም​ና​ለሁ፤ የም​ለ​ም​ንህ ስለ ዓለም አይ​ደ​ለም፤ ስለ ሰጠ​ኸኝ ነው እንጂ፤ ያንተ ናቸ​ውና።


ሥጋ በለ​በ​ሰው ሁሉ ላይ ሥል​ጣ​ንን እንደ ሰጠ​ኸው መጠን ለሰ​ጠ​ኸው ሁሉ የዘ​ለ​ዓ​ለም ሕይ​ወ​ትን ይሰ​ጣ​ቸው ዘንድ።


እኔ እን​ደ​ም​ሄድ ወደ እና​ን​ተም እን​ደ​ም​መ​ለስ የነ​ገ​ር​ኋ​ች​ሁን ሰም​ታ​ች​ኋል፤ ብት​ወ​ዱ​ኝስ ወደ አብ በመ​ሄዴ ደስ ባላ​ችሁ ነበር፤ እርሱ አብ ይበ​ል​ጠ​ኛ​ልና።


“ከዓ​ለም ለይ​ተህ ለሰ​ጠ​ኸኝ ሰዎች ስም​ህን ገለ​ጥሁ፤ ያንተ ነበሩ፤ እነ​ር​ሱ​ንም ለእኔ ሰጥ​ተ​ኸ​ኛል፤ ቃል​ህ​ንም ጠበቁ።


እን​ግ​ዲህ በዓ​ለም አል​ኖ​ርም፤ እነ​ርሱ ግን በዓ​ለም ይኖ​ራሉ፤ እኔም ወደ አንተ እመ​ጣ​ለሁ፤ ቅዱስ አባት ሆይ፥ እነ​ዚ​ህን የሰ​ጠ​ኸ​ኝን እንደ እኛ አንድ ይሆኑ ዘንድ በስ​ምህ ጠብ​ቃ​ቸው፤


እኔ ታላቅ ንጉሥ ነኝና፥ ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር፥ ስሜም በአሕዛብ ዘንድ የተፈራ ነውና በመንጋው ውስጥ ተባት እያለው ለጌታ ተስሎ ነውረኛውን የሚሠዋ ሸንጋይ ሰው ርጉም ይሁን።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ግብ​ፃ​ው​ያን ከሚ​መ​ኩ​ባ​ቸ​ውና ከሚ​ገ​ዙ​ላ​ቸው አማ​ል​ክት ሁሉ እን​ዲ​በ​ልጥ አሁን ዐወ​ቅሁ” አለ።


ማዳን በማ​ይ​ችሉ በአ​ለ​ቆ​ችና በሰው ልጆች አት​ታ​መኑ።


እኔም የዘ​ለ​ዓ​ለም ሕይ​ወ​ትን እሰ​ጣ​ቸ​ዋ​ለሁ፤ ለዘ​ለ​ዓ​ለ​ሙም አይ​ጠ​ፉም፤ ከእ​ጄም የሚ​ነ​ጥ​ቃ​ቸው የለም።


እኔና አብ አንድ ነን።”


Follow us:

Advertisements


Advertisements