Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




ዮሐንስ 1:38 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

38 ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም ዘወር ብሎ ሲከ​ተ​ሉት አየና፥ “ምን ትሻ​ላ​ችሁ?” አላ​ቸው።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

38 ኢየሱስም ዘወር ብሎ ሲከተሉት አየና፣ “ምን ትፈልጋላችሁ?” ብሎ ጠየቃቸው። እነርሱም፣ “ረቢ፣ የት ትኖራለህ?” አሉት፤ “ረቢ” ማለት መምህር ማለት ነው።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

38 ኢየሱስም መለስ ብሎ ሲከተሉትም አይቶ “ምን ትፈልጋላችሁ?” አላቸው። እነርሱም “ረቢ!፥ (ሲተረጎም ‘መምህር ሆይ’ ማለት ነው) የምትኖረው የት ነው?” አሉት፤

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

38 ኢየሱስ መለስ ብሎ ሲከተሉት አየና “ምን ትፈልጋላችሁ?” አላቸው። እነርሱም “ረቢ! የምትኖረው የት ነው?” አሉት። (ረቢ ማለት መምህር ማለት ነው)

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

38 ኢየሱስም ዘወር ብሎ ሲከተሉትም አይቶ፦ ምን ትፈልጋላችሁ? አላቸው።

See the chapter Copy




ዮሐንስ 1:38
30 Cross References  

ከዚ​ህም በኋላ እን​ደ​ገና፥ “ማንን ትሻ​ላ​ችሁ?” ብሎ ጠየ​ቃ​ቸው፤ እነ​ር​ሱም፥ “የና​ዝ​ሬ​ቱን ኢየ​ሱ​ስን” አሉት።


እር​ሱም በሌ​ሊት ወደ ጌታ​ችን ኢየ​ሱስ መጥቶ እን​ዲህ አለው፥ “መም​ህር ሆይ፥ ልታ​ስ​ተ​ምር ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዘንድ እንደ መጣህ እና​ው​ቃ​ለን፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከእ​ርሱ ጋር ከሆነ በቀር አንተ የም​ታ​ደ​ር​ገ​ውን ይህን ተአ​ምር ሊያ​ደ​ርግ የሚ​ችል የለ​ምና።”


ናት​ና​ኤ​ልም፥ “በየት ታው​ቀ​ኛ​ለህ?” አለው፤ ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም መልሶ፥ “ገና ፊል​ጶስ ሳይ​ጠ​ራህ በበ​ለስ ዛፍ ሥር ሳለህ አይ​ች​ሃ​ለሁ” አለው።


የሚሰማኝ ሰው ብፁዕ ነው፥ መንገዴን የሚጠብቅ ብፁዕ ነው፥ ዕለት ዕለት በቤቴ መግቢያ የሚተጋ፥ የደጄንም መድረክ የሚጠብቅ።


እንደ ሥራ​ቸ​ውና እንደ ዐሳ​ባ​ቸው ክፋት ስጣ​ቸው፤ እንደ እጃ​ቸ​ውም ሥራ ክፈ​ላ​ቸው፤ ፍዳ​ቸ​ውን በራ​ሳ​ቸው ላይ መልስ።


ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም የሚ​ደ​ር​ስ​በ​ትን ሁሉ ዐውቆ ወደ እነ​ርሱ ወደ ውጭ ወጣና፥ “ማንን ትሻ​ላ​ችሁ?” አላ​ቸው።


በባ​ሕሩ ዳርም ባገ​ኙት ጊዜ፥ “መም​ህር ሆይ፥ ወደ​ዚህ መቼ መጣህ?” አሉት።


ወደ ዮሐ​ን​ስም ሄደው፥ “መም​ህር ሆይ፥ በዮ​ር​ዳ​ኖስ ማዶ ካንተ ጋር የነ​በ​ረው፥ አን​ተም የመ​ሰ​ከ​ር​ህ​ለት እርሱ እነሆ፥ ያጠ​ም​ቃል፤ ሁሉም ወደ እርሱ ይሄ​ዳል” አሉት።


አሁ​ንም ስለ ላካ​ች​ሁ​ብኝ ሳል​ጠ​ራ​ጠር ወደ እና​ንተ መጣሁ፤ በምን ምክ​ን​ያት እንደ ጠራ​ች​ሁኝ እጠ​ይ​ቃ​ች​ኋ​ለሁ።”


እነ​ር​ሱም ከገ​ሊላ፥ የቤተ ሳይዳ ሰው ወደ ሆነው ወደ ፊል​ጶስ ሄደው፥ “አቤቱ፥ ጌታ ኢየ​ሱ​ስን ልና​የው እን​ወ​ድ​ዳ​ለን” ብለው ለመ​ኑት።


ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም ወደ​ዚያ በደ​ረሰ ጊዜ አሻ​ቅቦ አየ​ውና፥ “ዘኬ​ዎስ ሆይ፥ ፈጥ​ነህ ውረድ፤ ዛሬ በቤ​ትህ እውል ዘንድ አለ​ኝና” አለው።


ጴጥ​ሮ​ስም ወደ እነ​ዚያ ሰዎች ወረ​ደና፥ “እነሆ፥ የም​ት​ፈ​ል​ጉኝ እኔ ነኝ፤ ለምን መጥ​ታ​ች​ኋል?” አላ​ቸው።


ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም ዘወር ብሎ ጴጥ​ሮ​ስን አየው፤ ጴጥ​ሮ​ስም፥ “ዛሬ ዶሮ ሳይ​ጮኽ ሦስት ጊዜ ትክ​ደ​ኛ​ለህ” ያለ​ውን የጌ​ታ​ች​ንን ቃል ዐሰበ።


ተነ​ሥ​ቶም ወደ አባቱ ሄደ፤ አባ​ቱም ከሩቅ አየ​ውና ራራ​ለት፤ ሮጦም አን​ገ​ቱን አቅፎ ሳመው።


ከዚ​ህም በኋላ ብዙ ሰዎች አብ​ረ​ውት ሲሄዱ መለስ ብሎ እን​ዲህ አላ​ቸው።


ማር​ያም የም​ት​ባል እኅ​ትም ነበ​ረ​ቻት፤ እር​ስ​ዋም ከጌ​ታ​ችን ኢየ​ሱስ እግር አጠ​ገብ ተቀ​ምጣ ትም​ህ​ር​ቱን ትሰማ ነበር።


ያም አጋ​ን​ንት የወ​ጡ​ለት ሰው ከእ​ርሱ ጋር ይሄድ ዘንድ ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስን ማለ​ደው፤


ከጠቢባን ጋር የሚሄድ ጠቢብ ይሆናል፤ ከአላዋቂዎች ጋር የሚሄድ ግን አላዋቂ ይሆናል።


እርስዋ ለሚመረኰዛት ሁሉ የሕይወት ዛፍ ናት፥ የሚታመኑባትም በእግዚአብሔር እንደ ጸና ሰው ናቸው።


ሩትም፦ ወደምትሄጅበት እሄዳለሁና፥ በምታድሪበትም አድራለሁና እንድተውሽ ከአንቺም ዘንድ እንድመለስ አታስቸግሪኝ፣ ሕዝብሽ ሕዝቤ፥ አምላክሽም አምላኬ ይሆናል፣


ሚስ​ቶ​ችህ የተ​መ​ሰ​ገኑ ናቸው፤ በፊ​ትህ ሁል​ጊዜ የሚ​ቆሙ፥ ጥበ​ብ​ህን የሚ​ሰሙ እነ​ዚህ አገ​ል​ጋ​ዮ​ች​ህም ምስ​ጉ​ኖች ናቸው።


አቤቱ፥ አንተ ለዘ​ለ​ዓ​ለም ትኖ​ራ​ለህ፤ ዙፋ​ን​ህም ከት​ው​ልድ እስከ ትው​ልድ ነው።


ሁለቱ ደቀ መዛ​ሙ​ር​ቱም እን​ዲህ ሲል ሰም​ተው ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስን ተከ​ተ​ሉት።


እነ​ር​ሱም፥ “ረቢ፥ ትር​ጓ​ሜ​ውም መም​ህር ሆይ፥ ማለት ነው፤ ወዴት ትኖ​ራ​ለህ?” አሉት።


በዚ​ህም ጊዜ ደቀ መዛ​ሙ​ርቱ፥ “መም​ህር ሆይ፥ እህል ብላ” ብለው ለመ​ኑት።


Follow us:

Advertisements


Advertisements