Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




ዮሐንስ 1:27 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

27 ከእኔ በኋላ የሚ​መ​ጣው፥ ከእኔ በፊት የነ​በ​ረው፥ የጫ​ማ​ውን ጠፍር ልፈታ እንኳ የማ​ይ​ገ​ባኝ ነው።”

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

27 ከእኔ በኋላ የሚመጣው፣ እኔ የጫማውን ማሰሪያ መፍታት የማይገባኝ እርሱ ነው።”

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

27 ከእኔ በኋላ የሚመጣው እርሱ ነው፤ እኔ የጫማውን ጠፍር ልፈታ የተገበሁ አይደለሁም” አላቸው።

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

27 እርሱ ከእኔ በኋላ የሚመጣ ነው፤ እኔ የጫማውን ማሰሪያ ለመፍታት እንኳ የበቃሁ አይደለሁም።”

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

27 እኔ የጫማውን ጠፍር ልፈታ የማይገባኝ፥ ከእኔ በኋላ የሚመጣው ከእኔ ይልቅ የሚከብር ይህ ነው አላቸው።

See the chapter Copy




ዮሐንስ 1:27
9 Cross References  

ከእኔ በፊት የነ​በረ ሰው ከእኔ በኋላ ይመ​ጣል ብዬ ስለ እርሱ የነ​ገ​ር​ኋ​ችሁ ይህ ነው፤ እርሱ ከእኔ አስ​ቀ​ድሞ ነበ​ርና።


ዮሐ​ን​ስም መልሶ ሁሉ​ንም እን​ዲህ አላ​ቸው፥ “እኔ በውኃ አጠ​ም​ቃ​ች​ኋ​ለሁ፤ ግን የሚ​በ​ል​ጠኝ የጫ​ማ​ውን ማሰ​ሪያ እንኳ ልፈ​ታ​ለት የማ​ይ​ገ​ባኝ ይመ​ጣል፤ እርሱ በመ​ን​ፈስ ቅዱስ፥ በእ​ሳ​ትም ያጠ​ም​ቃ​ች​ኋል።


“ተጎንብሼ የጫማውን ጠፍር መፍታት የማይገባኝ ከእኔ የሚበረታ በኋላዬ ይመጣል።


እኔስ “ለንስሐ በውሃ አጠምቃችኋለሁ፤ ጫማውን እሸከም ዘንድ የማይገባኝ ከእኔ በኋላ የሚመጣው ግን ከእኔ ይልቅ ይበረታል፤ እርሱ በመንፈስ ቅዱስ በእሳትም ያጠምቃችኋል፤


ምስ​ክሩ ዮሐ​ንስ ስለ እርሱ ድም​ፁን ከፍ አድ​ርጎ ተና​ገረ፤ እን​ዲ​ህም አለ፥ “እኔ ስለ እርሱ ከእኔ በፊት የነ​በረ ከእኔ በኋላ ይመ​ጣል ያል​ኋ​ችሁ ሰው ይህ ነው፥ እርሱ ከእኔ አስ​ቀ​ድሞ ነበ​ረና።”


ጳው​ሎ​ስም፥ “ዮሐ​ንስ ከእ​ርሱ በኋላ በሚ​መ​ጣው በኢ​የ​ሱስ ክር​ስ​ቶስ እን​ዲ​ያ​ምኑ እየ​ሰ​በከ የን​ስሓ ጥም​ቀ​ትን አጠ​መቀ” አላ​ቸው።


አንተ፦ አብ​ራ​ምን ባለ​ጠጋ አደ​ረ​ግ​ሁት እን​ዳ​ትል፥ ከአ​ንተ ገን​ዘብ ሁሉ ፈት​ልም ቢሆን፥ የጫማ ማዘ​ቢ​ያም ቢሆን እን​ዳ​ል​ወ​ስድ፥


ብዙ​ዎ​ችም ወደ እርሱ ሄደው፥ “ዮሐ​ንስ ምንም ያደ​ረ​ገው ተአ​ም​ራት የለም፤ ነገር ግን ዮሐ​ንስ ስለ​ዚህ ሰው የተ​ና​ገ​ረው ሁሉ እው​ነት ሆነ” አሉ።


ዮሐ​ን​ስም መል​እ​ክ​ቱን ሲፈ​ጽም እን​ዲህ አላ​ቸው፦ ‘እኔን ለምን ትጠ​ራ​ጠ​ሩ​ኛ​ላ​ችሁ? እር​ሱን አይ​ደ​ለ​ሁም፤ የጫ​ማ​ውን ማዘ​ቢያ ከእ​ግሩ ልፈታ የማ​ይ​ገ​ባኝ ከእኔ በኋላ እነሆ፥ ይመ​ጣል።’


Follow us:

Advertisements


Advertisements