Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




ኢዩኤል 3:13 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

13 መከሩ ደር​ሶ​አ​ልና ማጭድ ስደዱ፤ መጭ​መ​ቂ​ያ​ውም ሞል​ቶ​አ​ልና ኑ ርገጡ፤ ክፋ​ታ​ቸ​ውም በዝ​ቶ​አ​ልና መጭ​መ​ቂያ ሁሉ ፈስ​ሶ​አል።”

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

13 ማጭዱን ስደዱ፤ መከሩ ደርሷልና፤ ኑ ወይኑን ርገጡ፤ የወይን መጭመቂያው ሞልቶ፣ ከጕድጓዶቹም ተርፎ ፈስሷልና፤ ክፋታቸው እንደዚህ ታላቅ ነው።”

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

13 መከሩ ደርሶአልና ማጭድ ስደዱ፥ መጥመቂያውም ሞልቶአልና ኑ እርገጡ፥ ክፉታቸውም በዝቶአልና መጥመቂያ ሁሉ ፈርሶአል።

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

13 የእነርሱ ክፋት እጅግ በዝቶአል፤ የደረሰ መከር በማጭድ እንደሚታጨድ እጨዱአቸው፤ የወይን ዘለላ በመጥመቂያው ሞልቶ እንደሚረገጥ ርገጡአቸው፤”

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

13 መከሩ ደርሶአልና ማጭድ ስደዱ፥ መጥመቂያውም ሞልቶአልና ኑ እርገጡ፥ ክፉታቸውም በዝቶአልና መጥመቂያ ሁሉ ፈርሶአል።

See the chapter Copy




ኢዩኤል 3:13
14 Cross References  

ፍሬ ግን ሲበስል መከር ደርሶአልና ወዲያው ማጭድ ይልካል።”


ይሁዳ ሆይ! የሕ​ዝ​ቤን ምርኮ በም​መ​ል​ስ​በት ጊዜ ለአ​ንተ ደግሞ መከር ተወ​ስ​ኖ​ል​ሃል።”


መጭ​መ​ቂ​ያ​ውን ብቻ​ዬን ረግ​ጫ​ለሁ፤ ከአ​ሕ​ዛ​ብም አንድ ሰው ከእኔ ጋር አል​ነ​በ​ረም፤ በቍ​ጣ​ዬም ረገ​ጥ​ኋ​ቸው፤ በመ​ዓ​ቴም ወደ መሬት ጣል​ጥ​ህ​ዋ​ቸው፤ ደማ​ቸ​ው​ንም በም​ድር ላይ አፈ​ሰ​ስሁ፤ ልብ​ሴም ሁሉ በደም ታለለ።


እንክርዳዱም የክፉው ልጆች ናቸው፤ የዘራውም ጠላት ዲያብሎስ ነው፤ መከሩም የዓለም መጨረሻ ነው፤ አጫጆችም መላእክት ናቸው።


የእ​ስ​ራ​ኤል አም​ላክ የሠ​ራ​ዊት ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላ​ልና፥ “የባ​ቢ​ሎን ንጉሥ ቤት እንደ ተረ​ገጠ አው​ድማ ናት፤ ጥቂት ቈይታ የመ​ከር ጊዜ ይደ​ር​ስ​ባ​ታል።


ሳም​ኬት። እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ኀያ​ላ​ኖ​ችን ሁሉ ከመ​ካ​ከሌ አስ​ወ​ገ​ዳ​ቸው፤ ምር​ጦ​ችን ያደ​ቅቅ ዘንድ ጊዜን ጠራ​ብኝ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ድን​ግ​ሊ​ቱን የይ​ሁ​ዳን ልጅ በመ​ጭ​መ​ቂያ እን​ደ​ሚ​ጨ​መቅ ወይን ረገ​ጣት። ስለ​ዚ​ህም አለ​ቅ​ሳ​ለሁ።


“ሰባት ሳም​ን​ትም ትቈ​ጥ​ራ​ለህ፤ መከ​ሩን ማጨድ ከም​ት​ጀ​ም​ር​በት ቀን ጀምሮ ሰባት ሳም​ንት መቍ​ጠር ትጀ​ም​ራ​ለህ።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ለአ​ብ​ር​ሃም አለው፥ “የሰ​ዶ​ምና የገ​ሞራ ጩኸት በእኔ ዘንድ በዛ፤ ኀጢ​አ​ታ​ቸ​ውም እጅግ ከበ​ደች፤


በአ​ራ​ተ​ኛው ትው​ልድ ግን ወደ​ዚህ ይመ​ለ​ሳሉ፤ እስከ ዛሬ ድረስ የአ​ሞ​ራ​ው​ያን ኀጢ​አት አል​ተ​ፈ​ጸ​መ​ምና።”


የሰ​ዶም ሰዎች ግን ክፉ​ዎ​ችና በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት እጅግ ኀጢ​አ​ተ​ኞች ነበሩ።


አየሁም፤ እነሆም ነጭ ደመና በደመናውም ላይ የሰውን ልጅ የሚመስል ተቀምጦአል፤ በራሱም ላይ የወርቅ አክሊል በእጁም ስለታም ማጭድ ነበረው።


አሕዛብንም ይመታበት ዘንድ ስለታም ሰይፍ ከአፉ ይወጣል፤ እርሱም በብረት በትር ይገዛቸዋል፤ እርሱም ሁሉን የሚገዛ የእግዚአብሔርን የብርቱ ቍጣውን ወይን መጥመቂያ ይረግጣል።


አጫጅ የቆ​መ​ውን እህል ሰብ​ስቦ ዛላ​ውን እን​ደ​ሚ​ያ​ጭድ ይሆ​ናል፤ በሸ​ለቆ እሸ​ትን እን​ደ​ሚ​ሰ​በ​ስ​ብም እን​ዲሁ ይሆ​ናል።


Follow us:

Advertisements


Advertisements