Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




ኢዩኤል 2:21 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

21 “ምድር ሆይ! አት​ፍሪ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ታላቅ ነገር አድ​ር​ጎ​አ​ልና ፈጽሞ ደስ ይበ​ልሽ፤ ሐሤ​ትም አድ​ርጊ።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

21 ምድር ሆይ፤ አትፍሪ፤ ደስ ይበልሽ፤ ሐሤትም አድርጊ፤ በርግጥ እግዚአብሔር ታላቅ ነገር አድርጓል።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

21 ምድር ሆይ፥ ጌታ ታላቅ ነገር አድርጎአልና አትፍሪ፥ ደስም ይበልሽ፥ እልልም በዪ።

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

21 “ምድር ሆይ አትፍሪ፤ እግዚአብሔር ስላደረገልሽ ታላቅ ነገር ደስ ይበልሽ! ሐሤትም አድርጊ።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

21 ምድር ሆይ፥ እግዚአብሔር ታላቅ ነገር አድርጎአልና አትፍሪ፥ ደስም ይበልሽ፥ እልልም በዪ።

See the chapter Copy




ኢዩኤል 2:21
21 Cross References  

አታ​ፍ​ሪ​ምና አት​ፍሪ፤ አቷ​ረ​ጂ​ምና አት​ደ​ን​ግጪ፤ የዘ​ለ​ዓ​ለም እፍ​ረ​ት​ሽ​ንም ትረ​ሺ​ዋ​ለሽ፤ የመ​በ​ለ​ት​ነ​ት​ሽ​ንም ስድብ ከእ​ን​ግ​ዲህ ወዲህ አታ​ስ​ቢም።


እኔ ከአ​ንተ ጋር ነኝና አት​ፍራ፤ እኔ አም​ላ​ክህ ነኝና አት​ደ​ን​ግጥ፤ አበ​ረ​ታ​ሃ​ለሁ፤ እረ​ዳ​ህ​ማ​ለሁ፤ በጽ​ድ​ቄም ቀኝ ደግፌ እይ​ዝ​ሃ​ለሁ።


ወደ እኔ ጩኽ፥ እኔም እመ​ል​ስ​ል​ሃ​ለሁ፤ አን​ተም የማ​ታ​ው​ቀ​ውን ታላ​ቅና ኀይ​ለኛ ነገ​ርን እነ​ግ​ር​ሃ​ለሁ።


የተ​ጠ​ማው ምድረ በዳ ደስ ይለ​ዋል፤ በረ​ሃ​ውም ሐሤት ያደ​ር​ጋል፤ እንደ ጽጌ​ረ​ዳም ያብ​ባል።


አሁ​ንም ቁሙ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በዐ​ይ​ና​ችሁ ፊት የሚ​ያ​ደ​ር​ገ​ውን ይህን ታላቅ ነገር ተመ​ል​ከቱ።


እንዲሁ ዳግመኛ ለኢየሩሳሌምና ለይሁዳ ቤት በዚህ ወራት በጎነትን አደርግ ዘንድ አስቤአለሁ፣ አትፍሩ።


የሰ​ሜ​ን​ንም ሠራ​ዊት ከእ​ና​ንተ ዘንድ አር​ቃ​ለሁ፤ ወደ በረ​ሃና ወደ ምድረ በዳ እሰ​ደ​ዋ​ለሁ፤ ፊቱን ወደ መጀ​መ​ሪ​ያው ባሕር፥ ጀር​ባ​ው​ንም ወደ ኋለ​ኛው ባሕር አድ​ርጌ አሳ​ድ​ደ​ዋ​ለሁ፤ እር​ሱም ትዕ​ቢ​ትን አድ​ር​ጎ​አ​ልና ግማቱ ይወ​ጣል፤ ክር​ፋ​ቱም ይነ​ሣል።”


ብቻ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ፍሩ፤ ያደ​ረ​ገ​ላ​ች​ሁ​ንም ታላቅ ነገር አይ​ታ​ች​ኋ​ልና በፍ​ጹም ልባ​ችሁ በእ​ው​ነት አም​ል​ኩት፤


“እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሰውን በም​ድር ላይ ከፈ​ጠ​ረው ጀምሮ፥ ከሰ​ማይ ዳር እስከ ሰማይ ዳርቻ ድረስ ከቶ እን​ዲህ ያለ ታላቅ ነገር ሆኖ፥ ወይም እንደ እርሱ ያለ ተሰ​ምቶ እንደ ሆነ ከአ​ንተ በፊት የነ​በ​ረ​ውን የቀ​ደ​መ​ውን ዘመን ጠይቅ።


አቤቱ፥ አም​ላ​ካ​ችን ሆይ፥ አንተ ሰማ​ሃ​ቸው፤ አቤቱ፥ አንተ ማር​ሃ​ቸው፥ በሥ​ራ​ቸው ሁሉ ግን ትበ​ቀ​ላ​ቸ​ዋ​ለህ።


ከዚ​ህም ነገር በኋላ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቃል በራ​እይ ወደ አብ​ራም መጣ፤ እን​ዲህ ሲል፥ “አብ​ራም ሆይ፥ አት​ፍራ፤ እኔ ጋሻ እሆ​ን​ሃ​ለሁ፤ ዋጋ​ህም በእኔ ዘንድ እጅግ ብዙ ነው።”


በዚ​ያም ቀን እን​ዲህ ይሆ​ናል፥ ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፤ ለሰ​ማይ እመ​ል​ሳ​ለሁ፤ ሰማ​ይም ለም​ድር ይመ​ል​ሳል፤


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በእ​ስ​ራ​ኤል ላይ ምሕ​ረ​ትን አድ​ር​ጎ​አ​ልና ሰማ​ያት ደስ ይበ​ላ​ቸው፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ያዕ​ቆ​ብን ተቤ​ዥ​ቶ​አ​ልና፥ በእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ዘንድ ይከ​በ​ራ​ልና የም​ድር መሠ​ረ​ቶች መለ​ከ​ትን ይንፉ፤ ተራ​ሮ​ችና ኮረ​ብ​ቶች በው​ስ​ጣ​ቸው ያሉ ዛፎች ሁሉ፥ እልል ይበሉ።


እና​ን​ተም በደ​ስታ ትወ​ጣ​ላ​ችሁ፤ በሐ​ሤ​ትም ትማ​ራ​ላ​ችሁ፤ ተራ​ሮ​ችና ኮረ​ብ​ቶች በደ​ስታ ሊቀ​በ​ሏ​ችሁ ይዘ​ላሉ፤ የሜ​ዳም ዛፎች ሁሉ በቅ​ር​ን​ጫ​ፎ​ቻ​ቸው ያጨ​በ​ጭ​ባሉ።


የም​ስ​ጋ​ናው ስም ለዓ​ለ​ምና ለዘ​ለ​ዓ​ለም ይባ​ረክ፤ ምስ​ጋ​ና​ውም ምድ​ርን ሁሉ ይምላ። ይሁን፤ ይሁን።


ብዙ መብል ትበ​ላ​ላ​ችሁ፤ ትጠ​ግ​ቡ​ማ​ላ​ችሁ፤ ከእ​ና​ን​ተም ጋር ተአ​ም​ራ​ትን የሠ​ራ​ውን የአ​ም​ላ​ካ​ች​ሁን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ስም ታመ​ሰ​ግ​ና​ላ​ችሁ፤ ሕዝ​ቤም ለዘ​ለ​ዓ​ለም አያ​ፍ​ርም።


Follow us:

Advertisements


Advertisements