Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




ኤርምያስ 9:17 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

17 እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ እን​ዲ​መጡ አል​ቃ​ሾች ሴቶ​ችን ጥሩ፤ ወደ ብል​ሃ​ተ​ኞች ሴቶ​ችም ላኩ፤ መጥ​ተ​ውም ይን​ገ​ሩ​አ​ችሁ፤

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

17 የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ “እንግዲህ፤ አልቃሽ ሴቶች ጥሩ፤ ሥልጡን ሙሾ አውራጆች አስመጡ፤

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

17 የሠራዊት ጌታ እንዲህ ይላል፦ “አስተውሉ፥ እንዲመጡም አልቃሾች ሴቶችን ጥሩ፤ እንዲመጡም ወደ ብልሃተኞች ሴቶች ላኩ፤

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

17 የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “አሁንም አስቡ፥ አልቃሾችን በአንድነት ሰብስቡ፤ ሙሾ የሚያወጡ ሴቶችንም ጥሩ።”

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

17 እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ እንዲመጡ አልቃሾች ሴቶችን ጥሩ፥ እንዲመጡም ወደ ብልሃተኞች ሴቶች ላኩ፥

See the chapter Copy




ኤርምያስ 9:17
12 Cross References  

ከፍ ያለ​ውን ተመ​ል​ክ​ተው ደግሞ ሲፈሩ፥ ድን​ጋ​ጤም በመ​ን​ገድ ላይ ሲሆን፤ ለው​ዝም ሲያ​ብብ፥ አን​በ​ጣም እንደ ሸክም ሲከ​ብድ፥ ፍሬም ሳይ​በ​ተን፤ ሰው ወደ ዘለ​ዓ​ለም ቤቱ ሲሄድ፥ አል​ቃ​ሾ​ችም በአ​ደ​ባ​ባይ ሲዞሩ፤


ኤር​ም​ያ​ስም ለን​ጉሡ ለኢ​ዮ​ስ​ያስ የል​ቅሶ ግጥም ገጠ​መ​ለት፤ እስከ ዛሬም ድረስ ወን​ዶ​ችና ሴቶች መዘ​ም​ራን ሁሉ በል​ቅሶ ግጥ​ማ​ቸው ስለ ኢዮ​ስ​ያስ ይና​ገሩ ነበር፤ ይህም በእ​ስ​ራ​ኤል ሁሉ ዘንድ ወግ ሆኖ በል​ቅሶ ግጥም ተጽ​ፎ​አል።


ወደ ምኵራቡ አለቃ ቤትም መጥቶ ሰዎች ሲንጫጩና ሲያለቅሱ ዋይታም ሲያበዙ አየ፤


ነገር ግን ሌዋ​ታ​ንን ለመ​ግ​ደል የተ​ዘ​ጋጀ ያችን ቀን የሚ​ረ​ግም ይር​ገ​ማት።


ኢየሱስም ወደ መኰንኑ ቤት በደረሰ ጊዜ፥ እምቢልተኞችንና የሚንጫጫውን ሕዝብ አይቶ


“እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የቍ​ጣ​ውን ትው​ልድ ጥሎ​አ​ልና፥ ትቶ​ታ​ል​ምና ጠጕ​ር​ሽን ቈር​ጠሽ፥ ጣዪው፤ በከ​ን​ፈ​ሮ​ች​ሽም ሙሾ አው​ርጂ።


ሄ። እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እንደ ጠላት ሆነ​ብኝ፤ እስ​ራ​ኤ​ልን አሰ​ጠመ። አዳ​ራ​ሾ​ች​ዋን ሁሉ ዋጠ፤ አን​ባ​ዎ​ች​ዋ​ንም አጠፋ። በይ​ሁ​ዳም ሴት ልጅ ውር​ደ​ት​ንና ጕስ​ቍ​ል​ናን አበዛ።


“አንተ የሰው ልጅ ሆይ! ስለ ጢሮስ ሙሾ አድ​ርግ።


ይኸ​ውም ሙሾ ነው፤ ሙሾን ያሞ​ሹ​ለ​ታል፤ የአ​ሕ​ዛብ ሴቶች ልጆች ያሞ​ሹ​ለ​ታል፤ ስለ ግብ​ፅና ስለ ኀይ​ልዋ ሁሉ ያሞ​ሹ​ለ​ታል፥” ይላል ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።


የእ​ስ​ራ​ኤል ቤት ሆይ! በእ​ና​ንተ ላይ ለሙሾ የማ​ነ​ሣ​ውን ይህን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቃል ስሙ።


በዚያ ቀን በምሳሌ ይመስሉባችኋል፥ በጽኑ ልቅሶም ያለቅሱላችኋል፥ እነርሱም፦ ፈጽመን ጠፍተናል፥ የሕዝቤን እድል ፈንታ ይሰፍራል፥ እርሱንም የሚከለክል የለም፥ እርሻችንን ለዓመፀኞች ይከፍላል ይላሉ።


Follow us:

Advertisements


Advertisements